ዱዓ መቼ ተቀባይነት ያገኛል? ጊዜያት እና ምክንያቶች

ዱዓ ተቀባይነት እንደሚያገኝ በይበልጥ የሚከጀልባቸው ጊዜያት እና ሁኔታዎች።

1 አንድ ጊዜ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሳለ ነው። (ስለዚህም) ዱዓእን አብዙ!"

ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሳለ መሆኑን ገለፁ። ይህም ሰጋጅ ከሰውነቱ የላቀና የተከበረው አካሉን ለአላህ በሱጁድ ለመዋደቅ፣ ለመዋረድና ለመተናነስ ሲል መሬት ላይ የሚደፋ በመሆኑ ነው።

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሱጁድ ውስጥ ዱዓእ እንድናበዛም አዘዙን። በዚህም ንግግራዊም ድርጊታዊም መተናነስ ይሰባሰባሉ።

ጥቅሞች

  • አምልኮ ባሪያውን ወደ አላህ መቃረብን ትጨምርለታለች።
  • ሱጁድ ዱዓእ ተቀባይነት ከሚያገኝበት ስፍራዎች መካከል አንዱ ስለሆነ ሱጁድ ውስጥ ዱዓእ ማብዛት እንደሚወደድ ተረድተናል።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

2 አንድ ጊዜ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአቡ ኡማማ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዐምር ቢን ዐበሳህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ እንደሰማቸው ነገረኝ: "ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው በመጨረሻው የሌሊቱ አጋማሽ ነው። በዚህ ወቅት አላህን ከሚያወሱ መሆን ከቻልክ ሁን!"»

አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጥራት የተገባው ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው በመጨረሻው የሌሊቱ ሲሶ በመሆኑ አንተ አማኝ ሆይ! በዚህ ወቅት ከሚያመልኩት፣ ከሚሰግዱ፣ ከሚያወሱ፣ በወንጀላቸው ከሚፀፀቱ ሰዎች መካከል ለመሆን ከተሳካልህና ከቻልክ በዚህ ወቅት አጅር መሸመትና መታገል የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ተናገሩ።

ጥቅሞች

  • አንድ ሙስሊም በሌሊቱ የመጨረሻ ወቅት ላይ ዚክር እንዲያደርግ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • ዚክር ለማለት፣ ዱዓ ለማድረግና ለመስገድ አንዱ ወቅት ከአንዱ እንደሚበላለጥ እንረዳለን።
  • "ጌታ ወደ ባሪያው እጅግ ቅርብ የሚሆነው" በሚለው ሐዲሥና "አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሆኖ ነው።" በሚለው ሐዲሥ መካከል ባለው ልዩነት ሚረክ እንዲህ ብለዋል: እዛኛው ላይ የተፈለገው ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው የሌሊቱ አጋማሽ ላይ ሲሆን እዚህኛው ላይ የተፈለገው ደግሞ አንድ ባሪያ ካሉት ሁኔታዎች መካከል ወደ ጌታ የሚቀርበው በሱጁድ ሁኔታው መሆኑን ለመግለፅ ነው።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

3 አንድ ጊዜ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባል ዱዓ አይመለስም (ተቀባይነቱ ጥርጥር የለውም)።"»

አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባል ዱዓ ያለውን ደረጃና እርሱ ለተቀባይነት የተገባና የማይመለስ ስለሆነ በዚህ ወቅት አላህን እንድንማፀን ገለፁ።

ጥቅሞች

  • ይህ ወቅት ዱዓ ለማድረግ ያለውን በላጭነት እንረዳለን።
  • አንድ ዱዓ አድራጊ የዱዓን ስነስርዓቶች ካሟላ፣ ዱዓ ለማድረግ በላጩን ወቅትና ስፍራ ካለመ፣ አላህን ከማመፅ ከራቀ፣ ነፍሱ አምታታችና አጠራጣሪ ነገር ውስጥ እንዳትገባ ከተጠነቀቀ፣ በአላህ ላይ ያለውን እሳቤ ካሳመረ በአላህ ፈቃድ ዱዓው ተቀባይነት ለማግኘት የተገባ ነው።
  • ስለዱዓ ተቀባይነት ማግኘት አልሙናዊ እንዲህ ብለዋል: «ማለትም የዱዓ መስፈርቶችን፣ ማዕዘናቶችንና ስነስርዓቶች ካሟላ በኋላ ከለመነው እንጂ ያጓደለው ነገር ካለ በመስተጓጎሉ ከነፍሱ በቀር ማንንም አይውቀስ።»
  • የዱዓ ተቀባይነት ማግኘት: ወይ የለመነው በፍጥነት ትገኝለታለች ወይም በለመነው አምሳያ ጉዳት ዞር ይደረግለታል ወይም በመጪው አለም ለርሱ ድልብ ይደረግለታል። ይህም እንደአላህ ጥበብና እዝነት የሚወሰን ነው።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

4 አንድ ጊዜ

ትርጉም እና ምንጭ

ከኡሙ ደርዳ እና ከአቡ ደርዳእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ይሉ ነበር: «አንድ ሙስሊም ሰው ለወንድሙ ከሩቅ (በሌለበት) የሚያደርግለት ዱዓ ተቀባይነት አለው። ከጭንቅላቱ በላይ የተወከለ መልአክ አለ። ለወንድሙ መልካም ነገርን ዱዓ ባደረገለት ቁጥር ለዚህ ጉዳይ የተወከለው መልአክም "አሚን ላንተም ተመሳሳዩ አለህ።" ይለዋል።»

ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙስሊም የሆነ ሰው ለሙስሊም ወንድሙ ከሩቅ ‐ ዱዓ የሚደረግለት ሰው በሌለበት ‐ የሚያደርገው ዱዓ ተቀባይነት እንዳለው ተናገሩ። ይህም የኢኽላስ ጥግ የደረሰ ዱዓ ስለሆነ ነው። ዱዓ አድራጊው ጭንቅላት ዘንድም የተወከለ መልአክ እንዳለና ለወንድሙ መልካም ነገርን ዱዓ ባደረገ ቁጥር ለዚህ ጉዳይ የተወከለው መልአክ "አሚን ላንተም ዱዓ ያደረግከውን አምሳያ ይስጥህ።" እንደሚልም ተናገሩ።

ጥቅሞች

  • አማኞች በዱዓ እንኳን ቢሆን እርስ በርሳቸው መልካም እንዲዋዋሉ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • ከሩቅ ዱዓ ማድረግ እውነተኛ ኢማንና ወንድማማችነት እንዳለ ፍንትው አድርጎ ያሳያል።
  • ዱዓ ማድረግን ከሩቅ በሚለው መገደቡ ጥግ ለደረሰ ኢኽላስና ተመስጦ ምቹ ስለሆነ ነው።
  • ዱዓ ተቀባይነት ከሚያገኝባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ አንድ ሙስሊም ለወንድሙ ከሩቅ ዱዓ ማድረጉ ነው።
  • ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ከሩቅ በሌለበት ለሙስሊም ወንድም ዱዓ ማድረግ ያለውን ደረጃ እንረዳለን። ዱዓውን ያደረገው ለበርካታ የሙስሊም ጀመዓዎች ቢሆንም ይህን ደረጃ ያገኛል። ለሙስሊሞች ባጠቃላይም ቢያደርግም የሐዲሡ ግልፅ መልዕክት እንደሚያሳየው አሁንም ይህን ደረጃ ያገኛል። አንዳንድ ቀደምቶች ለራሳቸው ዱዓ ማድረግ በሚፈልጉበት ወቅት ዱዓቸው ተቀባይነት እንዲያገኝና የዱዓውን ተመሳሳዩን ስለሚያስገኝላቸው ያቺን ለራሳቸው የፈለጓትን ነገር ለሙስሊም ወንድማቸው ዱዓ ያደርጉ ነበር።"
  • አንዱ የመልአኮች ተግባር ተገልጿል። ከመልአኮች መካከል አላህ ለዚህ ሥራ የወከለው አለ።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

5 አንድ ጊዜ

ትርጉም እና ምንጭ

ከኑዕማን ቢን በሺር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: 'ዱዓእ እሱ አምልኮ ነው።' ከዚያም {ጌታችሁም አለ "ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና። እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ።"} [ጋፊር: 60] የሚለውን አነበቡ።"

አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዱዓእ አምልኮ እንደሆነ ተናገሩ። በዱንያና በአኺራዊ ጉዳዮች የሚጠቅመውን ነገር እንዲሰጠውና የሚጎዳውን ነገር እንዲከላከልለት አላህ የሚጠየቅበት ልመናዊ ዱዓም ይሁን፤ ማንኛውም ውጫዊና ውስጣዊ ንግግርም ተግባርም አላህ የሚወዳቸውና የሚያስደስተው ልባዊ፣ አካላዊና ገንዘባዊ አምልኮዎችን የሚያደርጉበት አምልኳዊ ዱዓእም ቢሆን ያው ነው። እነዚህ የዱዓእ አይነቶችም ለአላህ ብቻ ጥርት ተደርገው መፈፀማቸው ግዴታ ነው።

ከዚያም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለዚህ ንግግራቸው የአላህን ንግግር ማስረጃ አደረጉ። አላህ እንዲህ ብሏል፦ {ጌታችሁም አለ "ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና። እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ።"}

ጥቅሞች

  • ዱዓእ የአምልኮ መሰረት በመሆኑ ከአላህ ውጪ ለሆነ መስጠት አይፈቀድም።
  • ዱዓእ እውነተኛ ባርነትን፣ የጌታን መብቃቃትና ችሎታ እውቅና መስጠትን እና የባሪያን ወደ አላህ ፈላጊነቱን ሰብስቦ የያዘ ነው።
  • ከአላህ አምልኮ በመኩራትና ዱዓእን በመተው ፍዳ ዙሪያ ብርቱ ዛቻ መምጣቱን እንረዳለን። አላህን ከመለመን የሚኮሩ ሰዎች ጀሀነም የተናነሱና የተዋረዱ ሆነው ይገባሉ።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

6 አንድ ጊዜ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ የተከበረ አንዳችም ነገር የለም።"

ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል። ደረጃ: ሐሰን ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከአምልኮዎች መካከል ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ እጅግ በላጭ የሆነ አምልኮ አንድም እንደሌለ ገለፁ። ምክንያቱም ዱዓእ የአላህን መብቃቃት፣ የባሪያን ደካማነትና ፈላጊነት እውቅና መስጠትን ውስጡ ስለያዘ ነው።

ጥቅሞች

  • የዱዓእን ትሩፋት እንረዳለን። አላህን የለመነ ሰው አላህን እያላቀ ነው። የሌለው አይከጀልምና ጥራት የተገባው አምላክ እጅግ የተብቃቃ መሆኑን እየመሰከረ ነው። ደንቆሮ አይለመንምና እጅግ ሰሚ መሆኑን፣ ስስታም አይለመንምና ቸር መሆኑን፣ ልበደረቅ አይለመንምና አዛኝ መሆኑን፣ ደካማ አይለመንምና ቻይ መሆኑን፣ ሩቅ ያለ አይሰማምና ቅርብ መሆኑን እና ሌሎችም የልቅናና የምሉዕነት መገለጫዎችን ለአሏህ እያረጋገጠ ነው።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

7 አንድ ጊዜ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አላህ መልካም (ጥሩ) ነውና ከመልካም (ከጥሩ) በቀር አይቀበልም። አላህ መልክተኞችን ባዘዘበት ነገር አማኞችንም አዟል። አላህ እንዲህ ብሏል: {እናንተ መልክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ብሉ። በጎ ስራንም ስሩ። እኔ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነኝ።} እንዲህም ብሏል: {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከነዚያ ከሰጠናችሁ ጣፋጮችን ብሉ።}" ቀጥለውም ጉዞ የሚያረዝም፣ ፀግሩ የተንጨባረረ፣ ፊቱንና ልብሱን አቧራ ያለበሰው አንድ ሰውዬ አወሱ። እጁን ወደ ሰማይ እየዘረጋ: "ጌታዬ ሆይ! ጌታዬ ሆይ! እያለ ይለምናል። ምግቡ ሐራም ነው። መጠጡ ሐራም ነው። ልብሱ ሐራም ነው። በሐራም ነው የተገነባው። እንዴት ለርሱ ዱዓው ተቀባይነት ይኖረዋል?" አሉ።»

ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ መልካም፣ ከጉድለትና ነውር የጠራና የፀዳ፣ በምሉዕነት የሚገለፅ መሆኑን ተናገሩ፤ ከተግባርም፣ ከንግግርና ከእምነትም መልካም የሆነውን እንጂ እንደማይቀበል ተናገሩ። እርሱም ለአላህ ጥርት ተደርጎ የተሰራና የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መመሪያ የተከተለ ስራ ነው። በዚህ ካልሆነ በቀርም ወደ አላህ መቃረብ አይገባም። ለአንድ አማኝ ስራው መልካም ከሚሆንበት ትላልቅ ነገሮች መካከል ምግቡ መልካም መሆኑ ነው። ይህም የተፈቀደውን መመገቡ ነው። በዚህም ስራው ይፀዳል። ስለዚህም የተፈቀደን በመብላትና መልካም በመስራት አላህ መልክተኞችን እንዳዘዘው ሁሉ አማኞችንም አዘዘ። አላህ እንዲህ አለ: {እናንተ መልክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ብሉ። በጎ ስራንም ስሩ። እኔ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነኝ።} እንዲህም አለ: {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከነዚያ ከሰጠናችሁ ጣፋጮችን ብሉ።}

ቀጥለው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምንም ያህል ተቀባይነትን የሚያስገኙ ግልፅ ሰበቦችን ቢፈፅም ስራን የሚያበላሽና ተቀባይነቱን የሚያሳጣ ከሆነው ሐራም ምግብ ከመብላት አስጠነቀቁ። ለዱዓ ተቀባይነትን ያስገኛሉ ከተባሉት ግልፅ ሰበቦች መካከልም:

የመጀመሪያ: እንደ ሐጅ፣ ጂሃድ፣ ዝምድናን መቀጠልና ከዚህም ውጪ ላሉ ነገሮች ለአምልኳዊ አላማዎች ጉዞን ማርዘም ነው።

ሁለተኛው: ባለማበጠር ምክንያት የፀጉሩ መበታተንና በአፈር (በአቧራ) ምክንያት የልብሱ ቀለምና የሰውነት መልኩ መለወጡ ነው። ይህም አስገዳጅ ችግር የገጠመው መሆኑ ነው።

ሶስተኛው: ወደ ሰማይ ዱዓ በማድረግ እጁን ከፍ ያደርጋል።

አራተኛው: ጌታዬ ሆይ! ጌታዬ ሆይ! እያለ ወደ አላህ በስሞቹ ይቃረባል፣ በዚህም ችክ ይላል።

ከነዚህ ለዱዓ ተቀባይነትን ከሚያስገኙ ምክንያቶች ጋር ሆኖም ግን ዱዓው አልተሰማም። ይህም ምግቡ፣ መጠጡና ልብሱ ሐራም ስለሆነና በሐራም ስለተገነባ ነው። ባህሪው ይህ የሆነ ሰው ተቀባይነት ማግኘቱም ሩቅ ነው። አላህስ እንዴት ዱዓውን ይቀበለዋል?

ጥቅሞች

  • አላህ ዐዘ ወጀል በዛቱ፣ በባህሪው፣ በድርጊቱና በህግጋቶቹ ምሉዕ መሆኑን እንረዳለን።
  • ስራን ለአላህ ዐዘ ወጀል በማጥራት ላይና ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በመከተል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • "አላህ መልክተኞችን ባዘዘው ነገር አማኞችንም አዟል።" ከሚለው የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ንግግር ለስራ የሚያነሳሳን አገላለፅ መጠቀም እንደሚገባ እንረዳለን። አንድ አማኝ ይህ ነገር መልክተኞችም የታዘዙት ነገር መሆኑን ሲያውቅ ለመተግበር ይበራታልም ይነሳሳልም።
  • ዱዓን ተቀባይነት ከሚያሳጡ ነገሮች መካከል ሐራም መብላት አንዱ ነው።
  • ዱዓ ተቀባይነት እንዲኖረው ከሚያደርጉ ሰበቦች መካከል አምስት ነገሮች ይገኛሉ: አንደኛ: ጉዞ ማርዘም ነው። በጉዞ ውስጥ ዱዓ ተቀባይነት ከሚያስገኙ ሰበቦች መካከል ትልቁ ሰበብ የሆነውን ስብር ማለትን አቅፏል። ሁለተኛ: በጭንቅ ሁኔታ ላይ መሆን። ሶስተኛ: እጆችን ወደ ሰማይ መዘርጋት። አራተኛ: የአላህን ጌትነት ደጋግሞ በማውሳት አላህ ላይ ችክ ማለት ሲሆን ይህም ዱዓ ተቀባይነት ያስገኛል ከሚባሉት መካከል ትልቁ ሰበብ ነው። አምስተኛ: ምግብና መጠጥን ማሳመር ናቸው።
  • መልካምና ሐላልን መብላት ለመልካም ስራ ከሚያግዙ ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው።
  • ቃዲ እንዲህ ብለዋል: "መልካም (ጥሩ) ማለት የቆሻሻ ተቃራኒ ነው። በዚህ ባህሪ የተገለፀው አሏህ ሲሆን የሚፈለገው እርሱ ከጉድለቶች የፀዳ መሆኑንና ከእንከኖች የጠራ መሆኑን ነው። በዚህ ባህሪ የተገለፀው በጥቅሉ ባሪያ ሲሆን ደግሞ ከውዳቂ ስነምግባርና ከፀያፍ ተግባራት የፀዳ መሆኑንና ከዚህ ተቃራኒ የሆነን ማንነት የተላበሰ መሆኑን የሚገልፅ ነው። ገንዘብ ሲገለፅበት ደግሞ ገንዘቡ ሐላል መሆኑንና ከምርጥ ገንዘብ መካከል እንደሆነ የሚገልፅ ነው።"

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

ጥያቄዎች

በዚህ ገጽ ላይ ምን አለ?

ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝበት ጊዜ: እያንዳንዳቸው በዐረብኛ፣ ከትርጉማቸው፣ ከመጡበት ሐዲስ፣ ከደረጃቸው እና ከማብራሪያ ጋር።

ትርጉሞቹ ከየት ናቸው?

ከHadeethEnc.com፣ የተተረጎሙ የነቢዩ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ። እያንዳንዱ ሐዲስ እነሱ እንዳሳተሙት፣ ከምንጩ እና ከደረጃው ጋር እንዲሁም ወደ ዋናው የሚወስድ ማስፈንጠሪያ ይዞ ይቀርባል።

የዕለት ማስታወሻ ማግኘት እችላለሁ?

አዎ። ለAndroid የሆነው ነፃው የQabas መተግበሪያ የጠዋት እና የማታ ዚክርን በየቀኑ ያስታውስዎታል፣ ተመሳሳይ ቆጣሪም አለው።