ለዱንያ እና ለአኺራ ሁሉን አቀፍ ዱዓዎች

በዚህ ዓለም እና በአኺራ መልካምን ሁሉ የሚለምኑ አጫጭር ዱዓዎች።

1 አንድ ጊዜ

اللَّهُمَّ رَبَّنَا آتِنَا فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً، وَفِي الآخِرَةِ حَسَنَةً، وَقِنَا عَذَابَ النَّارِ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአነስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጅግ አብዝተው ያደርጉት የነበረው ዱዓ 'አልላሁመ ረበና አቲና ፊ ዱንያ ሐሰነተን ወፊል አኺረቲ ሐሰነተን ወቂና ዓዛበን-ናር' የሚለውን ነበር።" (ትርጉሙም: ጌታችን አላህ ሆይ! በዱንያ መልካሙን ስጠን፤ በመጨረሻው ዓለምም መልካሙን ስጠን። ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን።) ማለት ነው።

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጠቅላይ የሆኑ ዱዓዎችን ማድረግ ያበዙ ነበር። ከነርሱም መካከል: "አልላሁመ ረበና አቲና ፊ ዱንያ ሐሰነተን ወፊል አኺረቲ ሐሰነተን ወቂና ዓዛበን-ናር" የሚለው ነበር።" (ትርጉሙም: ጌታችን አላህ ሆይ! በዱንያ መልካሙን ስጠን፤ በመጨረሻው አለምም መልካሙን ስጠን። ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን።) ማለት ነው። ይህ ዱዓ ጣፋጭ፣ ሰፊና ሐላል የሆነ ሲሳይን፣ መልካም ሚስትን፣ የአይን ማረፊያ የሆነ ልጅን፣ እረፍትን፣ ጠቃሚ ዕውቀትን፣ መልካም ስራንና የመሳሰሉትን ተወዳጅና ፍቁድ የሆኑ ተፈላጊዎችን ባጠቃላይ የዱንያ መልካም ነገሮችን እንዲሁም በቀብር ውስጥ፣ በሒሳብ መቆሚያ ስፍራና በእሳት ውስጥ ከሚያጋጥም ቅጣቶች ሰላም መሆንን፣ የአላህን ውዴታ ማግኘት፣ ዘውታሪ ፀጋ መጎናፀፍን፣ አዛኝ ወደሆነው ጌታ መቅረብን የመሰሉ የመጨረሻው አለም መልካም ነገሮችንም የሚያጠቃልል ዱዓ ነው።

ጥቅሞች

  • ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመከተል ጠቅላይ የሆኑ ዱዓዎችን ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  • የተሟላ ዱዓ የሚባለው ሰውዬው በዱዓው ውስጥ ዱንያዊም አኺራዊም መልካም ጉዳዮችን የሰበሰበ እንደሆነ ነው።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

2 አንድ ጊዜ

اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ مِنْ الْخَيْرِ كُلِّهِ، عَاجِلِهِ وَآجِلِهِ، مَا عَلِمْتُ مِنْهُ وَمَا لَمْ أَعْلَمْ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ الشَّرِّ كُلِّهِ، عَاجِلِهِ وَآجِلِهِ، مَا عَلِمْتُ مِنْهُ وَمَا لَمْ أَعْلَمْ، اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ مِنْ خَيْرِ مَا سَأَلَكَ عَبْدُكَ وَنَبِيُّكَ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا عَاذَ بِهِ عَبْدُكَ وَنَبِيُّكَ، اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْجَنَّةَ، وَمَا قَرَّبَ إِلَيْهَا مِنْ قَوْلٍ أَوْ عَمَلٍ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ النَّارِ، وَمَا قَرَّبَ إِلَيْهَا مِنْ قَوْلٍ أَوْ عَمَلٍ، وَأَسْأَلُكَ أَنْ تَجْعَلَ كُلَّ قَضَاءٍ قَضَيْتَهُ لِي خَيْرًا

ትርጉም እና ምንጭ

የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህን ዱዓ አስተማሯት: "አልላሁመ ኢኒ አስአሉከ ሚነል ኸይሪ ኩሊህ፣ ዓጂሊሂ ወአጂሊህ፣ ማ ዓሊምቱ ሚንሁ ወማለም አዕለም፣ ወአዑዙ ቢከ ሚነ ሸሪ ኩሊህ፣ ዓጂሊሂ ወአጂሊህ ማዓሊምቱ ሚንሁ ወማለም አዕለም። አላሁመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ኸይሪ ማሰአለከ ዐብዱከ ወነቢዩከ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማዓዘ ቢሂ ዐብዱከ ወነቢዩክ፣ አላሁመ ኢኒ አስአሉከል ጀነተ ወማ ቀረበ ኢለይሃ ሚን ቀውሊን አው ዓመሊን፣ ወአስአሉከ አንተጅዐለ ኩለ ቀዷኢን ቀደይተሁ ሊ ኸይራ" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ቅርቡንም የዘገየውንም፣ ከርሱ ያወቅኩትንም ያላወቅኩትንም ሁሉንም እጠይቅሃለሁ፤ ከመጥፎ ነገርም ቅርቡንም የዘገየውንም፣ ከርሱ ያወቅኩትንም ያላወቅኩትንም ከሁሉም መጥፎ ነገር ባንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! ባሪያህና ነቢይህ የጠየቀህን መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ፣ ባሪያህና ነቢይህ ከተጠበቁት መጥፎ ነገርም ባንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! ጀነትንና ወደርሷ የሚያቃርብን ንግግር ወይም ተግባር እጠይቅሃለሁ። ከእሳትና ወደርሷ ከሚያቀርቡ ንግግሮችና ተግባሮች ባንተ እጠበቃለሁ። ለኔ የወሰንከውን ሁሉንም ውሳኔዎች መልካም እንድታደርግልኝም እጠይቅሃለሁ።" ማለት ነው።

رواه ابن ماجه وأحمد ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዓኢሻን (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና ጠቅላይ ዱዓዎችን አስተማሯት። እነርሱም እነዚህ አራት ዱዓዎች ናቸው:

የመጀመሪያው: ሁሉንም መልካም ነገር የጠቀለለ ዱዓ ነው (አላህ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ሁሉንም እጠይቅሃለሁ) አጠቃላዩን (ቅርቡንም) ወቅቱ የቀረበውን (የዘገየውንም) መምጫ ወቅቱ የራቀውንም (ከርሱ ያወቅኩትንም) ካሳወቅከኝም (ያላወቅኩትንም) ከአንተ እውቀት ብቻ ከሆነውም እጠይቅሃለሁ። በዚህም ነገሮችን አዋቂና ውስጠ አዋቂ ወደሆነው አላህ ብቻ ማስጠጋት አለበት። ይህንን ዱዓ ላደረገ ሙስሊም አሏህ በላጩንና የተሻለውን ይመርጥለታል። (ከመጥፎ ነገርም ቅርቡንም የዘገየውንም፣ ከርሱ ያወቅኩትንም ያላወቅኩትንም ከሁሉም ነገር)

(መጠበቂያዬ) መጠጊያዬ አንተው ነህ።

ሁለተኛው ዱዓ: አንድ ሙስሊም በዱዓው ወሰን ከማለፍ ጥበቃን የሚጠይቅበት ነው። (ባሪያህና ነቢይህ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የጠየቁህን መልካም ነገር) (አላህ ሆይ እኔ እጠይቅሃለሁ) ከአንተ እፈልጋለሁ። (ባሪያህና ነቢይህ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከተጠበቁት መጥፎ ነገርም) (ባንተ እጠበቃለሁ) እጠጋለሁ። በዚህ ዱዓ ጠያቂው ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የለመኑትን የዱዓ አይነቶች ሳይቆጥር እርሳቸው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህን ከለመኑትና ከርሱ ከፈለጉት የተሻለውን እንዲሰጠው እየጠየቀ ነው።

ሶስተኛው ዱዓ: ጀነት መግባትና ከእሳት መራቅን መፈለግ ነው። ይህም የሁሉም ሙስሊም ፍላጎትና የስራው ግብ ነው። (አላህ ሆይ! ጀነትን) በርሷ መጎናፀፍን (ወደርሷ የሚያቃርብን ንግግር ወይም ተግባርን እጠይቅሃለሁ።) የሚያስደስትህን መልካም ስራ እጠይቅሃለሁ። (ከእሳትም በአንተ እጠበቃለሁ።) በአንተ እዝነት ካልሆነ በቀር ከፀያፍ ተግባር መጠበቂያ የለምና። (ወደርሷ ከሚያቃርብ ንግግር ወይም ተግባርም በአንተ እጠበቃለሁ።) ከሚያስቆጣህ ወንጀል በአንተ እጠበቃለሁ ማለት ነው።

አራተኛው ዱዓ: በአላህ ውሳኔ የመውደድ ዱዓ ነው። (ለኔ የወሰንከውን ሁሉንም ውሳኔዎች መልካም እንድታደርግልኝ እጠይቅሃለሁ።) አላህ ለኔ የወሰነውን ነገር ሁሉ ለኔ መልካም እንዲያደርግልኝ እጠይቃለሁ። ይህም በአላህ ፍርድ የመውደድ ዱዓ ነው።

ጥቅሞች

  • ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዓኢሻን እንዳስተማሯት አንድ ሰው ለቤተሰቦቹ ጠቃሚ የሆኑን የዲንና የዱንያ ጉዳዮችን ማስተማር እንደሚገባው እንረዳለን።
  • ለአንድ ሙስሊም በላጩ ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የመጡ ዱዓዎችን መሸምደድ ነው። ይህም ጠቅላይ ከሆኑ ዱዓዎች መካከል አንዱ ስለሆነ ነው።
  • ዑለማዎች ስለዚህ ሐዲሥ እንዲህ ብለዋል: ይህ ሐዲሥ መልካምን በመጠየቅና ከመጥፎ በመጠበቅ ረገድ ጠቅላይ ሐዲሥ ነው። ይህ ሐዲሥ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከተሰጣቸው ጠቅላይ ንግግር መካከልም ነው።
  • ከአላህ እዝነት ቀጥሎ ጀነት ከሚያስገቡ ምክንያቶች መካከል መልካም ተግባራትና ንግግሮች ይጠቀሳሉ።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

3 አንድ ጊዜ

اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْعَافِيَةَ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي دِينِي وَدُنْيَايَ وَأَهْلِي وَمَالِي، اللَّهُمَّ اسْتُرْ عَوْرَتِي -أَو: عَوْرَاتِي- وَآمِنْ رَوْعَاتِي، اللَّهُمَّ احْفَظْنِي مِنْ بَيْنِ يَدَيَّ، وَمِنْ خَلْفِي، وَعَنْ يَمِينِي، وَعَنْ شِمَالِي، وَمِنْ فَوْقِي، وَأَعُوذُ بِعَظَمَتِكَ أَنْ أُغْتَالَ مِنْ تَحْتِي

ትርጉም እና ምንጭ

ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሚያመሹና በሚያነጉ ጊዜ እነዚህን ዱዓዎች ከማድረግ አይተዉም ነበር። "አላሁመ ኢኒ አስአሉከልዓፊያተ ፊድ-ዱንያ ወልአኺረቲ፣ አላሁመ ኢኒ አስአሉከል ዐፍወ ወልዓፊየተ ፊ ዲኒ ወዱንያየ ወአህሊ ወማሊ፣ አላሁም ስቱር ዐውረቲ -አው ዓውራቲ- ወአሚን ረውዓቲ፣ አሏሁም ሕፈዝኒ ሚን በይኒ የደየ፣ ወሚን ኸልፊ፣ ወዓን የሚኒ፣ ወዓን ሺማሊ፣ ወሚን ፈውቂ፣ ወአዑዙ ቢአዞመቲክ 'አን ኡግታለ ሚን ተሕቲ"» ትርጉሙም (አላህ ሆይ! በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፤ አላህ ሆይ በዱንያዬ፣ በመጪው አለሜ፣ በቤተሰቤና ገንዘቤ ይቅርታህንና ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፤ አላህ ሆይ ነውሬን ወይም ነውሮቼን ሸሽግልኝ፣ ከፍርሃቴም ደህንነትን ስጠኝ፤ አላህ ሆይ! ከፊት ለፊቴም፣ ከኋላዬም፣ ከቀኜም፣ ከግራዬም፣ ከበላዬም ጠብቀኝ! ከበታቼ ድንገታዊ ጥቃት ከሚደርስብኝም በልቅናህ እጠበቃለሁ።) ማለት ነው።

አቡዳውድ፣ ነሳኢ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሲመሽና ሲነጋ እነዚህን ዱዓዎች ከማድረግ አይተዉም ነበር።

(አላሁመ ኢኒ አስአሉከል ዓፊየተ) አላህ ሆይ! ከአለማዊ በሽታዎች፣ መከራዎችና ችግሮች፣ ከዲናዊ ፈተናዎችና ዝንባሌዎች ሰላም መሆንን (ፊድዱንያ ወልአኺረተ) በቅርቡም ሆነ በመጪው አለም እጠይቅሃለሁ።

(አልላሁመ ኢኒ አስአሉከል ዐፍው) አላህ ሆይ! ወንጀሎቼን ማበስ፣ ይቅር ማለትህን (ወልዓፊየተ) ከነውር መፅዳትን (ፊዲኒ) በሃይማኖቴ ከሽርክ፣ ከቢድዓና ከወንጀሎች፤ (ወዱንያየ) በዓለማዊ ህይወቴ ደግሞ ከመከራዎች፣ ከሚያውክና ከክፋቶች (ወአህሊ) በቤተሰቤ ላይ በባለቤቴ፣ በልጆቼና ቅርብ ዘመዶቼ (ወማሊ) በገንዘቤና በስራዬ ላይ ደህና መሆንን እጠይቅሃለሁ።

(አልላሁመስቱር ዐውራቲ) አላህ ሆይ! እኔ ላይ ያሉትን ነውሮች፣ ጉድለቶች፣ እንከኖችን ሸሽገኝ፤ ወንጀሌንም አብስ። (ወአሚን ረውዓቲ) ድንጋጤዬንና ፍርሃቴን ደህንነት ስጠው።

(አልላሁመሕፈዝኒ) አላህ ሆይ! የሚያውኩኝንና መከራዎችን ከኔ አስወግድልኝ። (ሚን በይኒ የደየ፣ ወሚን ኸልፊ፣ ወዓን የሚኒ፣ ወዓን ሺማሊ፣ ወሚን ፈውቂ) (ከፊት ለፊቴም፣ ከኋላዬም፣ ከቀኜም፣ ከግራዬም፣ ከበላዬም) በዚህም አላህ ከሁሉም አቅጣጫዎች እንዲጠብቃቸው ጠየቁ። መከራዎችና መአቶች ወደ ሰው የሚመጡትና የሚዞሩት ከነዚህ አቅጣጫዎች መካከል በአንዱ ነውና።

(ወአዑዙ ቢዐዞመቲከ አንኡግታል) በድንገት ከመያዝና ተዘናግቼ ከምጠፋ በልቅናህ እጠበቃለሁ። (ሚንተሕቲ) በመሬት መደርመስ ከመጥፋትም ባንተ እጠበቃለሁ።

ጥቅሞች

  • መልክተኛውን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በመከተል እነዚህን ቃላቶች መጠባበቅ እንደሚገባ እንረዳለን።
  • የሰው ልጅ የሃይማኖቱን ደህንነት አላህን እንዲጠይቅ እንደታዘዘው ሁሉ ለዓለማዊ ጉዳዩም እንዲጠይቅ ታዟል።
  • ጢቢይ እንዲህ ብለዋል: «ስድስቱን አቅጣጫዎች ማጠቃለላቸው የመከራዎች መምጣት በነርሱ በኩል ስለሆነ ነው። የታች አቅጣጫን አበክረው የጠቀሱት ከታች የሚመጣ መከራ አዋራጅ ስለሆነ ነው።»
  • ንጋት ላይ አዝካሮችን ለመቅራት በላጩ ወቅት: ጎህ ከወጣ ጀምሮ የቀኑ መጀመሪያ ላይ ፀሃይ እስክትወጣ ድረስና ከዐስር በኋላ ፀሃይ እስክትገባ ድረስ ነው። ከዚህ በኋላም ቢል ማለትም ረፋዱ ከፍ ካለ በኋላም ቢል ይበቃለታል። ከዙህር በኋላም ቢል ይበቃለታል። ከመግሪብ በኋላም ቢል ይበቃለታል። ይህም የዚክር ወቅት ነውና።
  • ዚክሩ መባል ያለበት በተለየ ወቅት እንደሆነ ማስረጃ ከጠቆመ የሱረቱል በቀራ መጨረሻ ሁለት አንቀጾችን ምሽት ላይ መቅራትን ይመስል ፀሃይ ከገባ በኋላ ምሽት ላይ ነው የሚፈፀመው።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

4 አንድ ጊዜ

ትርጉም እና ምንጭ

ከዓባስ ቢን ዐብዱል ሙጦሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ ሆይ! አላህን የምጠይቀው አንዳች ነገር አስተምሩኝ? አልኳቸው። እርሳቸውም "አላህ ደህና እንዲያደርግህ ጠይቀው" አሉኝ። ቀናትን ቆይቼ ከዚያም መጣሁና የአላህ መልክተኛ ሆይ! አላህን ዐዘ ወጀል የምጠይቀው አንዳች ነገር አስተምሩኝ? አልኳቸው። እርሳቸውም ለኔ "ዐባስ ሆይ! የአላህ መልክተኛ አጎት ሆይ! አላህን በዱንያና በመጪው አለም ደህንነትን ጠይቀው።" አሉኝ።»

ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል። ደረጃ: በሌላ ሰነድ ታግዞ ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አጎት የሆኑት ዐባስ ቢን ዐብዱል ሙጦሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህን የሚጠይቁበት ዱዓ እንዲያስተምሯቸው ፈልገው መጡ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ በዲንም፣ በዱንያና በመጪው አለምም ከሚያጋጥሙ መከራና ነውር ደህናና ሰላም እንዲያደርጋቸው እንዲጠይቁ አስተማሯቸው። ዓባስም እንዲህ አሉ: ከቀናት በኋላ በድጋሚ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህን የምጠይቅበት አስፈላጊ ዱዓ እንዲያስተምሩኝ ልጠይቅ ተመልሼ መጣሁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ውዴታን በማሳየት "ዓባስ ሆይ! የአላህ መልክተኛ አጎት ሆይ! በዱንያና በመጪው አለም ሁሉንም ጉዳት እንዲከላከልልህና ሁሉንም መልካምና ጠቃሚ ነገር እንዲሰጥህ አላህን ደህንነት እንዲሰጥህ ጠይቀው።" አሉት።

ጥቅሞች

  • ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሁለተኛ ጊዜ ዓባስ ሲጠይቃቸው ተመሳሳይ መልስ መስጠታቸው አንድ ባሪያ ጌታውን ከሚጠይቀው ነገሮች ምርጡ ደህንነት መሆኑን ይጠቁማል።
  • የዓፊያ (የደህንነት) ትሩፋት መገለፁን እንረዳለን። በዓፊያ ዱንያዊም አኺራዊም ጥቅሞች ይሰበሰባሉና።
  • ሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እውቀትና መልካም ነገር በመጨመር ላይ ያላቸውን ጥረት እንረዳለን።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

ጥያቄዎች

በዚህ ገጽ ላይ ምን አለ?

ሁሉን አቀፍ ዱዓዎች: እያንዳንዳቸው በዐረብኛ፣ ከትርጉማቸው፣ ከመጡበት ሐዲስ፣ ከደረጃቸው እና ከማብራሪያ ጋር።

ትርጉሞቹ ከየት ናቸው?

ከHadeethEnc.com፣ የተተረጎሙ የነቢዩ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ። እያንዳንዱ ሐዲስ እነሱ እንዳሳተሙት፣ ከምንጩ እና ከደረጃው ጋር እንዲሁም ወደ ዋናው የሚወስድ ማስፈንጠሪያ ይዞ ይቀርባል።

የዕለት ማስታወሻ ማግኘት እችላለሁ?

አዎ። ለAndroid የሆነው ነፃው የQabas መተግበሪያ የጠዋት እና የማታ ዚክርን በየቀኑ ያስታውስዎታል፣ ተመሳሳይ ቆጣሪም አለው።