ትምህርት 3 ከ4
ሙስሊም እንዴት መናገርና ጎረቤቶቹን እንዴት መያዝ አለበት?
ከቁርኣን
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا يَسۡخَرۡ قَوۡمٞ مِّن قَوۡمٍ عَسَىٰٓ أَن يَكُونُواْ خَيۡرٗا مِّنۡهُمۡ وَلَا نِسَآءٞ مِّن نِّسَآءٍ عَسَىٰٓ أَن يَكُنَّ خَيۡرٗا مِّنۡهُنَّۖ وَلَا تَلۡمِزُوٓاْ أَنفُسَكُمۡ وَلَا تَنَابَزُواْ بِٱلۡأَلۡقَٰبِۖ بِئۡسَ ٱلِٱسۡمُ ٱلۡفُسُوقُ بَعۡدَ ٱلۡإِيمَٰنِۚ وَمَن لَّمۡ يَتُبۡ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ ﴿١١﴾ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱجۡتَنِبُواْ كَثِيرٗا مِّنَ ٱلظَّنِّ إِنَّ بَعۡضَ ٱلظَّنِّ إِثۡمٞۖ وَلَا تَجَسَّسُواْ وَلَا يَغۡتَب بَّعۡضُكُم بَعۡضًاۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمۡ أَن يَأۡكُلَ لَحۡمَ أَخِيهِ مَيۡتٗا فَكَرِهۡتُمُوهُۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ تَوَّابٞ رَّحِيمٞ ﴿١٢﴾
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወንዶች ከወንዶች አይቀልዱ፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ ሴቶችም ከሴቶች (አይሳለቁ)፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ ነፍሶቻችሁንም አታነውሩ፡፡ በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ፡፡ ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ከፋ፡፡ ያልተጸጸተም ሰው እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከጥርጣሬ ብዙውን ራቁ፤ ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጢአት ነውና፡፡ ነውርንም አትከታተሉ፡፡ ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ፡፡ አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? (መብላቱን) ጠላችሁትም፤ (ሐሜቱንም ጥሉት)፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡
ከሱና
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል! በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ጎረቤቱን ያክብር! በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳውን ያክብር!"
ማብራሪያ
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአላህ እና በሚመለስበትና በስራው የሚመነዳበት በሆነው በመጨረሻው ቀን ያመነ ባሪያ ኢማኑ እነዚህን ጉዳዮችን በመፈፀም ላይ እንደሚያነሳሳው ገለፁ:
የመጀመሪያው: መልካም መናገር ነው። በዚህ ውስጥ ሱብሓነላህ ማለት፣ ላኢላሃኢለላህ ማለት፣ በመልካም ማዘዝ፣ ከመጥፎ መከልከል፣ በተጣሉ ሰዎች መካከል ማስማማት የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ። ይህንን ካልፈፀመ ዝምታን ያዘውትር፣ ክፋቱን ይቆጥብ፣ ምላሱን ይጠብቅ።
ሁለተኛ: ጉረቤትን ማክበር፡ ይህም እነሱን ባለማወክና ለነርሱ በጎ በማድረግ ነው።
ሶስተኛ: ለመዘየር የመጣን እንግዳ መልካም በማናገር፣ ምግብ በማብላትና ይህን በመሳሰሉት ማክበር ነው።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው። ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።"
ማብራሪያ
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እስልምናው የተሟላ ሙስሊም የሚባለው ሙስሊሞች ከምላሱ ሰላም የሆኑበት ሰው እንደሆነ ተናገሩ። ስለዚህም አይሰድባቸውምም፤ አይረግማቸውምም፤ አያማቸውምም፤ በሙስሊሞች መካከል በምላስ ከሚመጡ ማናቸውም የክፋት አይነት በየትኛውም ሊጎዳቸው አይሮጥም። ከእጁም ሙስሊሞች ሰላም የሆኑበት ነው። ስለዚህም በነርሱ ላይ ወሰን አያልፍም፤ ያለ አግባብ ገንዘባቸውን አይወስድምም በሌሎች መሰል ሁኔታዎችም ሙስሊሞችን አይጎዳም። ሙሃጂር ማለት: አላህ ክልክል ያደረገውን የተወ ነው።
ከኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "(ጎረቤቴን) ያስወርሰዋል ብዬ እስከማስብ ድረስ ጂብሪል በጎረቤት (ሐቅ ዙሪያ) እኔን ከማዘዝ አልተወገደም።"
ማብራሪያ
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጂብሪል ለጎረቤታቸው ትኩረት እንዲቸሩ፣ ሐቁን እንዲጠብቁ፣ እንዳያውኩት፣ ለርሱ በጎ እንዲውሉ፣ በሚያደርስባቸው ጉዳት እንዲታገሱ ከማዘዝና ከመደጋገም እንዳልተወገደ ተናገሩ። ይህም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከጎረቤት ሀቅ ክብደትና ጂብሪል ይህን ትእዛዝ ከመደጋገሙ የተነሳ ከሞቱ በኋላ ትተውት የሚያልፉትን ገንዘባቸውን ለጎረቤታቸው እንዲሰጡ የሚያዝ ወሕይ ሊወርድ ይሆን ብለው እስኪያስቡ ደረሱ። ጎረቤት ሲባልም ሙስሊምም ሆነ ካፊር፣ ዘመድም ሆነ ባዳ ማንኛውም ለቤት ቅርብ የሆነ ማለት ነው።