ትምህርት 2 ከ4
እስልምና ስለ ወላጆች ምን ይላል?
ከቁርኣን
۞ وَقَضَىٰ رَبُّكَ أَلَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّآ إِيَّاهُ وَبِٱلۡوَٰلِدَيۡنِ إِحۡسَٰنًاۚ إِمَّا يَبۡلُغَنَّ عِندَكَ ٱلۡكِبَرَ أَحَدُهُمَآ أَوۡ كِلَاهُمَا فَلَا تَقُل لَّهُمَآ أُفّٖ وَلَا تَنۡهَرۡهُمَا وَقُل لَّهُمَا قَوۡلٗا كَرِيمٗا ﴿٢٣﴾ وَٱخۡفِضۡ لَهُمَا جَنَاحَ ٱلذُّلِّ مِنَ ٱلرَّحۡمَةِ وَقُل رَّبِّ ٱرۡحَمۡهُمَا كَمَا رَبَّيَانِي صَغِيرٗا ﴿٢٤﴾
ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፡- እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ በወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ፡፡ በአንተ ዘንድ ኾነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ ፎህ አትበላቸው፡፡ አትገላምጣቸውም፡፡ ለእነርሱም መልካምን ቃል ተናገራቸው፡፡ ለሁለቱም ከእዝነትህ የመዋረድን ክንፍ ዝቅ አድርግላቸው፡፡ «ጌታዬ ሆይ! በሕፃንነቴ (በርኅራኄ) እንዳሳደጉኝ እዘንልላቸውም» በል፡፡
وَوَصَّيۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ بِوَٰلِدَيۡهِ حَمَلَتۡهُ أُمُّهُۥ وَهۡنًا عَلَىٰ وَهۡنٖ وَفِصَٰلُهُۥ فِي عَامَيۡنِ أَنِ ٱشۡكُرۡ لِي وَلِوَٰلِدَيۡكَ إِلَيَّ ٱلۡمَصِيرُ ﴿١٤﴾
ሰውንም በወላጆቹ (በጎ እንዲያደርግ) በጥብቅ አዘዝነው፡፡ እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው። ጡት መጣያው በሁለት አመት ውስጥነው። "ለእኔም ለወላጆችህም አመስግን" በማለት አዘዝነው። መመለሸው ወደ እኔ ብቻ ነው።
ከሱና
ከበህዝ ቢን ሐኪም ከአባቱ እንደተላለፈው: አባቱም ከአያቱ እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ: «"የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጎ ላደርግለት እጅግ የተገባው ማን ነው?" አልኳቸው። እርሳቸውም "እናትህ ከዚያም እናትህ ከዚያም እናትህ ከዚያም አባትህ ከዚያም ቅርብ የሆኑ ዘመዶችህ" አሉ።»
ማብራሪያ
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከሰዎች ሁሉ አስበልጠን በጎ ሊዋልለት፣ መልካም ሊሰራለት የሚገባው፣ ባማረ መልኩ ልንኗኗረው፣ ልንወዳጀውና ትስስራችንን ልናጠናክርለት የሚገባው በላጩ ሰው ማን እንደሆነ ገለፁ። እርሷም እናት ናት። ከሌሎች አካላቶች ሐቅ የእናት ሐቅ የበለጠ እንደሆነ ለማስገንዘብም ሶስት ጊዜ በመደጋገም አጽንዖት ሰጡት። ይህም የርሷ ደረጃ ከተቀሩት ሰዎች ባጠቃላይ እንደሚበልጥ ለመግለፅ ነው። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከእናት በመቀጠል በጎ ሊዋልለት የሚገባውን እንዲህ በማለት ገለፁ: ቀጥሎ አባት ቀጥሎ ቅርብ የሆኑ ዘመዶች አሉ። እጅግ ቅርብ በሆነ ቁጥር ሩቅ ከሆነው ዘመድ የበለጠ ዝምድናው ሊቀጠል ይገባል።