ከአዛን በኋላ የሚባል ዱዓ

አዛን ሲባል የሚባለው እና ካለቀ በኋላ የሚደረገው ዱዓ።

1 አንድ ጊዜ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "(የአዛንን) ጥሪ በሰማችሁ ጊዜ ሙአዚኑ (አዛን አድራጊው) እንደሚለው በሉ።"

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙአዚንን በምንሰማ ጊዜ ለርሱ ጥሪ መልስ በመስጠት ላይ አነሳሱ (አበረታቱ)። ምላሹም በየአንዳንዱ አረፍተ ነገር ሙአዚኑ የሚለውን በማለት ነው። ተክቢራው በሚያደርግ ጊዜ እኛም ከርሱ በኋላ ተክቢራ እናደርጋለን፣ ሁለቱን የምስክር ቃላት (ሸሀደተይንን) በሚል ጊዜ እኛም ከርሱ በኋላ እንላለን፣ (ሐይየ ዐለስ-ሶላህና ሐይየ ዐለል ፈላሕ) የሚሉት ሁለቱ አረፍተ ነገሮች ግን ይለያሉ። ከነርሱ በኃላ የምንለው "ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ" (ብልሃትም ሆነ ኃይል ከአላህ ውጪ የለም) ነውና።

ጥቅሞች

  • የሐዲሱ ጥቅል መልዕክት ስለሚያስፈርድ አዛን ባዮች ከበዙ የመጀመሪያው ሙአዚን አዛን ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለተኛውንም ሙአዚን አዛን ተከትሎ ለጥሪው መልስ ይሰጣል።
  • መፀዳጃ ቤት ውስጥ ወይም እየተፀዳዳ እስካልሆነ ድረስ በማንኛውም ሁኔታ ላይ ቢሆን ለሙአዚን ጥሪ መልስ መሰጠት አለበት።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

2 አንድ ጊዜ

ትርጉም እና ምንጭ

ከዑመር ቢን ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ 'አዛን ባዩ: 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) ያለ ጊዜ አንዳችሁ ከልቡ 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' ካለ፤ ከዚያም አዛን ባዩ: 'አሽሀዱ አንላ ኢላሃ ኢለሏህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ እመሰክራለሁ።) ያለ ጊዜም 'አሽሀዱ አንላ ኢላሃ ኢለሏህ' ካለ፤ ከዚያም አዛን ባዩ: 'አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ' (ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ።) ያለ ጊዜም 'አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ' ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'ሐይየ ዐለስ-ሶላህ' (ኑ ወደ ሶላት) ባለ ጊዜም 'ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ' (ብልሀትም ሆነ ኃይል በአላህ ካልሆነ በቀር የለም።) ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'ሐይየ ዐለል ፈላሕ' (ኑ ወደ ስኬት!) ባለ ጊዜም 'ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ' (ብልሃትም ሆነ ኃይል በአላህ ካልሆነ በቀር የለም።) ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) ያለ ጊዜም 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'ላ ኢላሀ ኢለሏህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም።) ያለ ጊዜም 'ላ ኢላሀ ኢለሏህ' ካለ ጀነት ገባ።

ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

አዛን ማለት የሶላት ወቅት መግባቱን ለሰዎች ማሳወቂያ ነው። የአዛን ቃላቶች የኢማንን መሰረተ ሀሳቦች የጠቀለሉ ቃላቶች ናቸው።

በዚህ ሐዲሥ ውስጥ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አዛን በሚሰማ ወቅት የተደነገገውን ገለፁ። እሱም አዛን ሰሚው አዛን ባዩ እንደሚለው ማለቱ ነው። አዛን ባዩ 'አላሁ አክበር' ያለ ጊዜ ሰሚውም 'አላሁ አክበር' ይላል በዚህ መልኩ አዛን ባዩ ያለውን በማለት ይቀጥላል። 'ሐይየ ዐለስ-ሶላህ' እና 'ሐይየ ዐለል ፈላሕ' በሚልበት ጊዜ ግን ሰሚው 'ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ ' ይበል።

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እነዚህን ቃላቶች ከልቡ አጥርቶ ከአዛን ባዩ ጋር የመላለሰ ሰው ጀነት እንደሚገባ ገለፁ።

የአዛን ቃላቶች ትርጉም: "አላሁ አክበር" ማለት ጥራት የተገባው አላህ ከሁሉም ነገር እጅግ ታላቅና የላቀ ነው ማለት ነው።

"አሽሀዱ አንላ ኢላሀ ኢለሏህ" ማለት ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም ማለት ነው።

"አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ" ማለት ሙሐመድ አላህ የላካቸው የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውንና እሳቸውን መታዘዝም ግዴታ መሆኑን በምላሴና በልቤ እርግጠኛ ሆኜ እመሰክራለሁ ማለት ነው።

"ሐይየ ዐለስ-ሶላህ" ማለት ወደ ሶላት ኑ! ማለት ሲሆን ሰሚው የሚለው "ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ" ማለት ደግሞ የአላህን ትእዛዝ ለመተግበር ከሚከለክሉ ነገሮች ለመዳን የሚያስችል ብልሀትም፤ ለመተግበር የሚያስችል ሀይልም፤ በማንኛውም ነገር ላይም ችሎታ የለም በአላህ መግጠም ቢሆን እንጂ ማለት ነው።

"ሐይየ ዐለል ፈላሕ" ማለት ወደ ስኬት መንገድ ኑ! ማለት ነው። ስኬቱም ጀነትን ማግኘትና ከእሳት መዳን ነው።

ጥቅሞች

  • ከሁለቱ "ሀይየዐለተይን" ("ሐይየ ዐለስ-ሶላህ" እና "ሐይየ ዐለል ፈላሕ") ውጪ የአዛን ባይን ጥሪ በሚለው አምሳያ መመለስ፤ በሁለቱ "ሐይዐለተይን" ወቅት ደግሞ "ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላሂ" በማለት መመለስ ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

3 አንድ ጊዜ

أَشْهَدُ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُهُ وَرَسُولُهُ، رَضِيتُ بِاللهِ رَبًّا وَبِمُحَمَّدٍ رَسُولًا، وَبِالْإِسْلَامِ دِينًا

ትርጉም እና ምንጭ

ከሰዕድ ቢን አቢ ወቃስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አዛን ሲባል የሰማ ጊዜ: 'አሽሃዱ አን ላኢላሃ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ ወአነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ ረዲቱ ቢላሂ ረበን ወቢሙሐመደን ረሱለን ወቢል ኢስላሚ ዲና' ያለ ሰው ወንጀሉ ይማራል።" (ትርጉሙም: ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። ብቸኛና አጋር የሌለው ነው። ሙሐመድም የአላህ ባሪያውና መልክተኛው ናቸው ብዬ እመሰክራለሁ፤ በአላህ ጌትነት፣ በሙሐመድ መልክተኝነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት ወድጃለሁ።)

ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: አዛን አድራጊውን የሰማ ጊዜ እንዲህ ያለ ሰው: "አሽሃዱ አን ላኢላሃ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ" ማለትም: ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለና ከርሱ ውጪ የሚመለኩ ሁሉ ከንቱ እንደሆኑ አረጋግጣለሁ፣ አውቃለሁ፣ እናገራለሁ። "ወአነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ" ማለትም: እርሳቸው ባሪያ ናቸውና አይመለኩም፣ መልክተኛ ናቸውና አይስተባበሉም። "ረዲቱ ቢላሂ ረበን" ማለትም: በአላህ ጌትነት፣ ተመላኪነትና በስሞቹና በባህሪያቱ ወድጃለሁ። ማለት ነው። "ወቢሙሐመደን ረሱላ" ማለትም ረሱል በተላኩበት ነገር ሁሉና ባደረሱን ነገር ወድጃለሁ። ማለት ነው። "በእስልምናም" ማለትም: ትእዛዛትም ሆኑ ክልከላዎች በሁሉም የኢስላም ህግጋት "ዲና" ማለትም በማመንና በመመራት ወድጃለሁ። ማለት ነው። "ወንጀሉ ይማራል።" ማለትም ትናንሽ ወንጀሎቹን ይማሩለታል።

ጥቅሞች

  • ይህን ዱዓ አዛን በሚሰሙ ጊዜ መደጋገም ወንጀልን ያስምራል።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

4 አንድ ጊዜ

اللَّهُمَّ رَبَّ هَذِهِ الدَّعْوَةِ التَّامَّةِ، وَالصَّلاَةِ القَائِمَةِ، آتِ مُحَمَّدًا الوَسِيلَةَ وَالفَضِيلَةَ، وَابْعَثْهُ مَقَامًا مَحْمُودًا الَّذِي وَعَدْتَهُ

ትርጉም እና ምንጭ

ከጃቢር ቢን ዐብዲላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አዛን በሚሰማ ጊዜ ‹አልላሁመ ረበ ሀዚሂ አድደዕወቲ አትታመቲ ወስሰላቲል ቃኢመህ አቲ ሙሐመደኒል ወሲለተ ወልፈዲለተ ወብዐሥሁ መቃመን መሕሙደኒለዚ ወዐድተህ› ያለ ሰው የትንሳኤ ቀን ምልጃዬ ትፀድቅለታለች።" ትርጉሙም "የዚህ የተሟላ ጥሪና የምትቆመው ሶላት ጌታ የሆንከው አላህ ሆይ! ለሙሐመድ ወሲላና ፈዲላን ስጣቸው፤ ቃል የገባህላቸውን ምስጉን ስፍራም ስጣቸው።" ማለት ነው።

ቡኻሪ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አዛን ባይን በሚሰማ ጊዜ አዛኑን ካጠናቀቀ በኋላ እንዲህ የሚል ሰውን ገለፁ።

(የዚህ የተሟላ ጥሪ ጌታ የሆንከው አላህ ሆይ!) የተሟላ ጥሪ የተባለው ወደ አላህ አምልኮና ወደ ሶላት የሚጠራበት የሆነው የአዛን ጥሪ ነው። (የተሟላ) ማለት መልዕክቱና የተውሒድ ጥሪው የተሟላ የሆነው ማለት ነው። (የቆመችው ሶላትም ጌታ) ማለት ዘውታሪ የሆነችው ሶላት ማለት ነው። (ለሙሐመድ ወሲላን ስጥ) ማለት ለነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ካልሆነ በቀር ለማንም የማትገባ የሆነችው ጀነት ውስጥ ያለች ከፍተኛዋን ደረጃ ስጣቸው፤ (ፈዲላንም) ማለት ከፍጡራን ደረጃዎች በላይ ከፍ ያለች ደረጃንም ስጣቸው። (ምስጉኑን ስፍራም ስጣቸው) ማለት እዛ ቦታ የቆመ ምስጉን የሚሆንበት ስፍራ ነው። እርሱም የትንሳኤ ቀን ያለው ትልቁ ምልጃ ነው። (ቃል የገባህላቸው የሆነውን) ማለት {ጌታህ ምስጉን በሆነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል።} በሚለው ቃልህ ለነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንድትሆን ቃል የገባኸውን ስፍራ ስጣቸው ማለት ነው።

ይህን ዱዓ የለመነም ሰው የትንሳኤ ቀን የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምልጃ ይረጋገጥለታልም ይፀድቅለታልም።

ጥቅሞች

  • ይህን ዱዓ ከሙአዚን ኋላ የሚለውን ከደጋገሙ በኋላ ሲያጠናቅቅ ማለቱ የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን። አዛን ያልሰማ ሰው ግን ይህን ዱዓ አይልም።
  • ወሲላን፣ ፈዲላን፣ ምስጉን ስፍራንና በፍጡራን መካከል ፍርድ እንዲካሄድ ትልቁን ምልጃ ለነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መሰጠቱ የርሳቸውን ደረጃ ያሳየናል።
  • "የትንሳኤ ቀን ምልጃዬ ትፀድቅለታለች።" ከሚለው ንግግራቸው መልክተኛው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንደሚያማልዱ እናፀድቃለን።
  • የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምልጃ ከኡመታቸው ትላልቅ ወንጀል ለሰሩት እሳት እንዳይገቡ እና እሳት ለገቡት ደግሞ እንዲወጡ ማማለድ ነው። ወይም ወደ ጀነት ያለሒሳብ እንዲገቡ ማማለድ እና ጀነት የገቡትም ደረጃቸው ከፍ እንዲል ማማለድ ነው።
  • ጢቢይ እንዲህ ብለዋል: «የተሟላች ጥሪ የተባለችው ከመጀመሪያው የአዛን ክፍል "ሙሐመደን ረሱሉሏህ" እስከሚለው ድረስ ያለው ነው። ሶላትን የሚያቋቁሙ በሚለው ውስጥ የቆመች የተባለችው ሶላት ደግሞ "ሐየዐለህ" ናት። ሶላት በማለት የተፈለገው ዱዓ፤ የቆመችው በማለት የተፈለገው ደግሞ ዘውታሪ ሊሆንም ያስመቻል። በአንድ ነገር የዘወተረ ጊዜ ቆመ እንደሚባለው ማለት ነው። በዚህም መሰረት "የቆመችው ሶላት" የሚለው የተሟላች ጥሪ ለሚለው መግለጫ ነው። ሶላት በማለት የተፈለገው አሁን አዛን እየተጠራላት ያለችው ሶላት ለማለት ተፈልጎ ሊሆንም ይችላል። ቃሉ በግልፅ የሚያስረዳውም ይህንኑ ነው።»
  • ሙሀለብ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ በሶላት ወቅቶች ዱዓ ማድረግ ላይ ያነሳሳል። በአዛን ወቅት ዱዓ ማድረግ ተቀባይነት ያገኛል ተብሎ ተስፋ የሚደረግበት ወቅት ነውና።"

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

5 አንድ ጊዜ

ትርጉም እና ምንጭ

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል፦ "አዛን ባዩን የሰማችሁ ጊዜ የሚለውን አምሳያ በሉ። ከዚያም በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ። እነሆ በኔ ላይ አንዲትን ሶላት ያወረደ በርሱ ምክንያት አላህ በርሱ ላይ አስር ሶለዋት ያወርድለታል። ከዚያም ለኔ ከአላህ ወሲላን ጠይቁልኝ። እርሷም ጀነት ውስጥ ያለች ደረጃ ናት። ከአላህ ባሮች መካከል ለአንድ ባሪያ እንጂ ለሌላ አትገባም። እርሱም እኔ እሆናለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ወሲላን ለኔ የጠየቀልኝ ሰው ለርሱ ምልጃዬ ትፀናለታለች።"

ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሶላት አዛን የሚያደርግን ሰው የሰማ ከ"ሐይየዐለተይን" ውጪ ከኋላው አስከትሎ (ሙአዚኑ) የሚለውን አምሳያ እንዲል ጠቆሙ። ከ"ሐይየዐለተይን" በኋላ ግን "ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ" ይላል። አዛኑ ከተጠናቀቀ በኋላም በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ ሶላትን ያወርዳል። እነሆ በርሳቸው ላይ አንዲትን ሶላት ያወረደ በርሱ ምክንያት አላህ በርሱ ላይ አስር ሶላት ያወርድበታልና። አላህ በባሪያው ላይ ሶላት አወረደ ማለት መላኢኮች ዘንድ ባሪያውን ማወደሱ ነው።

ቀጥለውም አላህ ወሲላን ለሳቸው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲሰጣቸው እንድንጠይቅ አዘዙ። እርሷም በጀነት ውስጥ የምትገኝ ከፍተኛዋ ደረጃ ናት። ይህቺ ስፍራም ከሁሉም የአላህ ባሮች መካከል ለአንድ ባሪያ እንጂ ለሌላ ለማንም አትሰጥም አትበጅምም (አትገባም)። ያ ባሪያ እኔ እሆናለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በዚህ መልኩ የተናገሩት ለመተናነስ ብለው ነው እንጂ ይህቺ ከፍተኛ ደረጃ ለአንድ ባሪያ እንጂ ለማንም የማትሆን ከሆነች ያ አንድ ባሪያ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንጂ ማንም አይሆንም። እሳቸው ከፍጡራን ሁሉ በላጩ ፍጡር ናቸውና።

ቀጥለው ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወሲላን ከአሏህ የለመነ ሰው የርሳቸውን ምልጃ እንደሚያገኝ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ።

ጥቅሞች

  • የሙአዚንን ጥሪ በመመለስ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • ለሙአዚን ከመለስን በኋላ በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ ሶላት የማውረድን ትሩፋት እንረዳለን።
  • ሶላት ካወረድንባቸው በኋላ ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወሲላን በመጠየቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • የወሲላ ምንነትና ጉዳዩዋ ከፍ ያለ መሆኑ መገለፁ። ለአንድ ባሪያ እንጂ አትበጅምና (አትገባም)።
  • በዚህች ከፍተኛ ደረጃ በመነጠላቸው የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ደረጃ መገለፁ።
  • ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአሏህ ወሲላን የጠየቀላቸው ሰው የርሳቸው ምልጃ ትፀድቅለታለች።
  • ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህቺ ደረጃ የርሳቸው ከመሆኗም ጋር ኡመታቸው ዱዓ እንዲያደርጉላቸው መፈለጋቸው ትህትናቸውን ይገልፃል።
  • መልካም ስራ በአስር መባዛቱ የአላህ ትሩፋትና እዝነት ስፋቱን ያስረዳናል።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

6 አንድ ጊዜ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባል ዱዓ አይመለስም (ተቀባይነቱ ጥርጥር የለውም)።"»

አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባል ዱዓ ያለውን ደረጃና እርሱ ለተቀባይነት የተገባና የማይመለስ ስለሆነ በዚህ ወቅት አላህን እንድንማፀን ገለፁ።

ጥቅሞች

  • ይህ ወቅት ዱዓ ለማድረግ ያለውን በላጭነት እንረዳለን።
  • አንድ ዱዓ አድራጊ የዱዓን ስነስርዓቶች ካሟላ፣ ዱዓ ለማድረግ በላጩን ወቅትና ስፍራ ካለመ፣ አላህን ከማመፅ ከራቀ፣ ነፍሱ አምታታችና አጠራጣሪ ነገር ውስጥ እንዳትገባ ከተጠነቀቀ፣ በአላህ ላይ ያለውን እሳቤ ካሳመረ በአላህ ፈቃድ ዱዓው ተቀባይነት ለማግኘት የተገባ ነው።
  • ስለዱዓ ተቀባይነት ማግኘት አልሙናዊ እንዲህ ብለዋል: «ማለትም የዱዓ መስፈርቶችን፣ ማዕዘናቶችንና ስነስርዓቶች ካሟላ በኋላ ከለመነው እንጂ ያጓደለው ነገር ካለ በመስተጓጎሉ ከነፍሱ በቀር ማንንም አይውቀስ።»
  • የዱዓ ተቀባይነት ማግኘት: ወይ የለመነው በፍጥነት ትገኝለታለች ወይም በለመነው አምሳያ ጉዳት ዞር ይደረግለታል ወይም በመጪው አለም ለርሱ ድልብ ይደረግለታል። ይህም እንደአላህ ጥበብና እዝነት የሚወሰን ነው።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

ጥያቄዎች

በዚህ ገጽ ላይ ምን አለ?

ከአዛን በኋላ ዱዓ: እያንዳንዳቸው በዐረብኛ፣ ከትርጉማቸው፣ ከመጡበት ሐዲስ፣ ከደረጃቸው እና ከማብራሪያ ጋር።

ትርጉሞቹ ከየት ናቸው?

ከHadeethEnc.com፣ የተተረጎሙ የነቢዩ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ። እያንዳንዱ ሐዲስ እነሱ እንዳሳተሙት፣ ከምንጩ እና ከደረጃው ጋር እንዲሁም ወደ ዋናው የሚወስድ ማስፈንጠሪያ ይዞ ይቀርባል።

የዕለት ማስታወሻ ማግኘት እችላለሁ?

አዎ። ለAndroid የሆነው ነፃው የQabas መተግበሪያ የጠዋት እና የማታ ዚክርን በየቀኑ ያስታውስዎታል፣ ተመሳሳይ ቆጣሪም አለው።