ወደ መስጊድ ሲገቡ እና ሲወጡ ዱዓ

በመስጊድ በር ላይ፣ ሲገቡ እና ሲወጡ የሚባሉ ቃላት።

1 አንድ ጊዜ

أعوذ بالله العظيم، وبوجهه الكريم، وسلطانه القديم، من الشيطان الرَّجِيم

ትርጉም እና ምንጭ

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዐስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንደተላለፈው: እርሳቸው መስጂድ በሚገቡ ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር: "አዑዙ በላሂል ዐዚም ወቢወጅሂሂል ከሪም ወሱልጧኒሂል ቀዲም ሚነሽ-ሸይጧኒ ረጂም" "የሚሉት ይህን ብቻ ነውን? " ተብሎ ተጠየቀ። "አዎን" አልኩኝ። "ይህን ያለ ጊዜም ሸይጧን 'የቀረውን የቀኑን ክፍል ከኔ ተጠበቀ።' ይላል።" ትርጉሙም "ታላቅ በሆነው አላህ፣ በተከበረው ፊቱ፣ መጀመሪያም በሌለው ስልጣኑ ከተረገመው ሰይጣን እጠበቃለሁ።"

አቡዳውድ ዘግበውታል። ደረጃ: ሐሰን ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መስጂድ በሚገቡ ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር: (አዑዙ ቢላሂል ዐዚም) በአላህና በባህሪያቱ እከለላለሁ፣ እጠበቃለሁም። (ወቢወጅሂሂል ከሪም) ሰጪና ቸር በሆነው፤ (ወሱልጧኒሂ) ከፍጡራኖች መካከል በፈለገው ላይ ባለው አሸናፊነቱ፣ በችሎታውና በበላይነቱ (አልቀዲም) የመጀመሪያና ዘላለማዊ በሆነው፤ (ሚነሽ-ሸይጧኒ ረጂም) ከአላህ እዝነት የተባረረና የራቀ ከሆነው ሰይጣን እጠበቃለሁ። ማለትም: አላህ ሆይ! ከሰይጣን ጉትጎታ፣ ከማጥመሙ፣ ከእርምጃዎቹ፣ ውስጣችን ላይ ከሚፈጥረው ውልታና ማጥመም ጠብቀኝ ማለት ነው። ይህም የጥመት ምክንያትና ለመሀይምነትና መጥመም የሚያነሳሳው (ጠንሳሽ) እርሱ ስለሆነ ነው። ለዐብደላህ ቢን ዐምርም "ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያሉት ይህን ብቻ ነውን?" ተብሎ ተጠየቀ። እርሱም "አዎን" አለ።

መስጂድ የሚገባ ሰው ይህን ዱዓ ካለም ሰይጣን እንዲህ ይላል: ይህ መስጂድ የገባው ሰው ነፍሱን በአጠቃላይ ወቅቱ ቀኑንም ምሽቱንም ከኔ ጠብቋታል።

ጥቅሞች

  • መስጂድ በሚገባ ወቅት በዚህ ዚክር ዱዓ የማድረግን ትሩፋት እንረዳለን። ይህ ዚክር ተናጋሪውን የተቀረውን ቀኑን ከሰይጣን ይጠብቀዋልና።
  • ከሰይጣን መጠንቀቅ እንደሚገባ እንረዳለን። ሰይጣንም ሙስሊምን ለማጥመምና ለማሳሳት የሚጠባበቅ መሆኑን እነረዳለን።
  • የሰው ልጅ በቀልቡ ባለው በአላህ የማመን፣ ይህን ዱዓ ማለትና ይህን ዱዓ ተከትሎ በተገባው ቃል (ምንዳ) እንደማመኑ ልክ ከሰይጣን ማጥመምና ማሳሳት ጥበቃን ያገኛል።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

2 አንድ ጊዜ

اللَّهُمَّ افْتَحْ لِي أَبْوَابَ رَحْمَتِكَ
اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ مِنْ فَضْلِكَ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአቡ ሑመይድ ወይም አቡ ኡሰይድ እንደተዘገበው እንዲህ አለ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ: 'አልላሁምመፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲከ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ለኔ የእዝነትህን በሮች ክፈትልኝ) ይበል። የወጣ ጊዜም ‘አልላሁምመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! እኔ ከትሩፋትህ እጠይቅሀለሁ።) ይበል።›"

ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መስጂድ በሚገባ ወቅት የሚባለውን ዱዓ ለኡመታቸው ጠቆሙ። (አልላሁምመ ኢፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲክ) (አላህ ሆይ! ለኔ የእዝነትህን በሮች ክፈትልኝ) የእዝነትን ምክንያቶች ለርሱ እንዲያመቻችለት አላህን ይጠይቃል። ከመስጂድ ለመውጣት የፈለገ ጊዜም (አልላሁምመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ) (አላህ ሆይ! እኔ ከትሩፋትህ እጠይቅሀለሁ።) ይበል። አላህን ከችሮታውና ከሐላል ሲሳዩ ተጨማሪ ፀጋዎቹን ይጠይቃል።

ጥቅሞች

  • ወደ መስጂድ በሚገባ ወቅትና ከመስጂድ በሚወጣ ወቅት ይህን ዱዓ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  • ሲገባ እዝነትን በመጠየቅ ላይ ሲወጣ ደግሞ ችሮታን በመጠየቅ ላይ የተገደበው: መስጂድ የሚገባ ሰው ወደ አላህና ወደ ጀነት በሚያቃርበው ነገሮች ላይ ነው የሚጠመደው ስለዚህ ከቦታው ጋር የሚስማማው እዝነትን መጠየቅ ነው። የወጣ ጊዜ ደግሞ ከሲሳይ የአላህን ችሮታ ለመፈለግ በምድር ላይ ስለሚሯሯጥ ከቦታው ጋር የሚስማማው ችሮታ መወሳቱ ነው።
  • እነዚህ ዚክሮች የሚባሉት መስጂድ መግባትና መውጣት ሲፈለግ እንደሆነ እንረዳለን።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

ጥያቄዎች

በዚህ ገጽ ላይ ምን አለ?

የመስጊድ ዱዓ: እያንዳንዳቸው በዐረብኛ፣ ከትርጉማቸው፣ ከመጡበት ሐዲስ፣ ከደረጃቸው እና ከማብራሪያ ጋር።

ትርጉሞቹ ከየት ናቸው?

ከHadeethEnc.com፣ የተተረጎሙ የነቢዩ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ። እያንዳንዱ ሐዲስ እነሱ እንዳሳተሙት፣ ከምንጩ እና ከደረጃው ጋር እንዲሁም ወደ ዋናው የሚወስድ ማስፈንጠሪያ ይዞ ይቀርባል።

የዕለት ማስታወሻ ማግኘት እችላለሁ?

አዎ። ለAndroid የሆነው ነፃው የQabas መተግበሪያ የጠዋት እና የማታ ዚክርን በየቀኑ ያስታውስዎታል፣ ተመሳሳይ ቆጣሪም አለው።