የእንቅልፍ ዱዓ እና ከመተኛት በፊት የሚባሉ ዚክሮች

ነቢዩ ﷺ ወደ መኝታቸው ሲሄዱ ያሉት እና ያነበቡት።

1 አንድ ጊዜ

قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ ﴿١﴾ اللَّهُ الصَّمَدُ ﴿٢﴾ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ ﴿٣﴾ وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ ﴿٤﴾
قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ ﴿١﴾ مِن شَرِّ مَا خَلَقَ ﴿٢﴾ وَمِن شَرِّ غَاسِقٍ إِذَا وَقَبَ ﴿٣﴾ وَمِن شَرِّ النَّفَّاثَاتِ فِي الْعُقَدِ ﴿٤﴾ وَمِن شَرِّ حَاسِدٍ إِذَا حَسَدَ ﴿٥﴾
قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ النَّاسِ ﴿١﴾ مَلِكِ النَّاسِ ﴿٢﴾ إِلَهِ النَّاسِ ﴿٣﴾ مِن شَرِّ الْوَسْوَاسِ الْخَنَّاسِ ﴿٤﴾ الَّذِي يُوَسْوِسُ فِي صُدُورِ النَّاسِ ﴿٥﴾ مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ ﴿٦﴾

ትርጉም እና ምንጭ

ከምእመናን እናት ዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው፦ "ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁል ጊዜም በምሽት ወቅት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ መዳፋቸውን ይሰበስቡና ከዚያም ትንፋሻቸውን እየነፉበት {ቁል ሁወ አላሁ አሐድ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈለቅ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢ ናስ}ን ይቀሩበት ነበር። ከዚያም ከሰውነታቸው የቻሉትን በመዳፋቸው ያብሳሉ። (ሲያብሱም) ጭንቅላታቸውን፣ ፊታቸውንና ከሰውነታቸው የፊትለፊቱን በቅድሚያ ያብሳሉ። ይህንንም ሶስት ጊዜ ይፈፅሙታል።"

ቡኻሪ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መመሪያ መካከል ለመተኛት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ ልክ ዱዐ እንደሚያደርግ ሰው መዳፋቸውን ሰብስበው ከፍ ያደርጉት ነበር። በሱም ላይ ከትንሽ ምራቅ ጋር በመቀላቀል ቀለል ያለ መንፋት በአፋቸው እየነፉበት ሶስት ምእራፎች ያነቡበታል። {ሱረቱል ኢኽላስ}ን፣ {ሰረቱል ፈለቅ}ን፣ {ሱረቱ አንናስ}ን ከዚያም የቻሉትን ያህል የሰውነታቸውን ክፍል ከጭንቅላታቸው፣ ከፊታቸውና ከሰውነታቸው የፊትለፊት ክፍል በመጀመር በመዳፋቸው ያብሱታል። ይህንንም ድርጊት ሦስት ጊዜ ይደጋግሙታል።

ጥቅሞች

  • ከመተኛት በፊት የኢኽላስን ምእራፍና ሙዐወዘተይንን መቅራትና ምራቅ የቀላቀለን ትንፋሽ በመንፋት የተቻለውን ያህል የሰውነትን ክፍል ማበስ እንደሚወደድ እንረዳለን።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

2 አንድ ጊዜ

آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنْزِلَ إِلَيْهِ مِنْ رَبِّهِ وَالْمُؤْمِنُونَ كُلٌّ آمَنَ بِاللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِنْ رُسُلِهِ وَقَالُوا سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا غُفْرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيْكَ الْمَصِيرُ ﴿٢٨٥﴾ لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا لَهَا مَا كَسَبَتْ وَعَلَيْهَا مَا اكْتَسَبَتْ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَا إِنْ نَسِينَا أَوْ أَخْطَأْنَا رَبَّنَا وَلَا تَحْمِلْ عَلَيْنَا إِصْرًا كَمَا حَمَلْتَهُ عَلَى الَّذِينَ مِنْ قَبْلِنَا رَبَّنَا وَلَا تُحَمِّلْنَا مَا لَا طَاقَةَ لَنَا بِهِ وَاعْفُ عَنَّا وَاغْفِرْ لَنَا وَارْحَمْنَا أَنْتَ مَوْلَانَا فَانْصُرْنَا عَلَى الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ ﴿٢٨٦﴾

ትርጉም እና ምንጭ

ከአቢ መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "በምሽት ውስጥ የመጨረሻዎቹን የበቀራህ ምእራፍ ሁለት አንቀፆች የቀራ ሰው ይበቁታል።"

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በምሽት ውስጥ የበቀራህ ምእራፍ የመጨረሻዎቹን ሁለት አንቀፆች የቀራ ሰው አላህ መጥፎና ጎጂ ከሆኑ ነገሮች እንደሚበቃው ተናገሩ። ለሌሊት ሶላት ከመቆም ይበቁታል ማለት ነውም ተብሏል። ሌሎች ውዳሴዎችን ከማለት ይበቁታል ማለት ነውም ተብሏል። ለሌሊት ሶላት የሚቀራ ዝቅተኛው በቂ የቁርአን አንቀፆች ናቸውም ተብሏል። ከዚህም ውጪ ተብሏል። ምንአልባት ሁሉም ከላይ የተጠቀሱትን ትርጓሜዎችን ቃሉ ስለሚሰበስባቸው ሁሉም ትክክለኛ ትርጓሜ ሊሆኑ ይችላሉ።

ጥቅሞች

  • የሱረቱል በቀራህ የመጨረሻ አንቀፆች ትሩፋት መገለፁ። እሱም { አመነ አርረሱሉ …} ከሚለው የአላህ ንግግር እስከምእራፉ መጨረሻ ያለውን ነው።
  • የበቀራህ ምእራፍ መጨረሻዎች ምሽት ላይ ለሚቀራቸው ሰው ከጉዳት፣ ከመጥፎና ከሰይጣን ይከላከላሉ።
  • ምሽት የሚባለውም ፀሃይ ስትገባ ይጀምርና ጎህ ስትወጣ ይጠናቀቃል።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

3 3 ጊዜ

اللَّهُمَّ قِنِي عَذَابَكَ يَوْمَ تَبْعَثُ عِبَادَكَ

ትርጉም እና ምንጭ

ሑዘይፋህ ቢን አል'የማን -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንዳስተላለፉት: «ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- መተኛት የፈለጉ ጊዜ እጃቸውን ጭንቅላታቸው ስር ያኖሩ ነበር። ቀጥለውም እንዲህ ይሉ ነበር: "አልላሁመ ቂኒ ዐዛበከ የውመ ተጅመዑ አው ተብዐሡ ዒባደክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ባሮችህን በምትሰበስብበት ወይም በምትቀሰቅስበት ቀን ከቅጣትህ ጠብቀኝ።" ማለት ነው።

ቲርሚዚ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ለመተኛት ስፍራቸውን ሲይዙ ቀኝ እጃቸውን ይንተራሱና ቀኝ ጉንጫቸውን ቀኝ እጃቸው ላይ በማኖር እንዲህ ይሉ ነበር: "አልላሁመ ቂኒ ዐዛበክ" አላህ ሆይ! ጌታዬ ቅጣትህን ጠብቀኝ። "የውመ ተጅመዑ አው ተብዐሡ ዒባደክ" የሒሳብ ቀን የትንሳኤ ቀን ማለት ነው።

ጥቅሞች

  • የዚህ የተባረከ ዱዓ ደረጃንና ነቢዩን -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በመከተል ይህንን አዘውትሮ ማለት እንደሚወደድ እንረዳለን።
  • በቀኝ ጎን መተኛት እንደሚወደድ እንረዳለን።
  • ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "አላህ ሆይ ከቅጣትህ ጠብቀኝ።" ከሚለው ንግግር የምንወስደው ትምህርት አስተዋይ የሆነ ሰው እንቅልፍን ሞትንና ከሞት በኋላ ያለውን መቀስቀስ ለማስታወሻነት ሊገለገልበት እንደሚገባ ነው።
  • የትንሳኤ ቀን ከአላህ ቅጣት መጠበቅ የሚገኘው በአላህ ችሮታና እዝነት ለመልካም ስራ በመገጠሙና አላህ ወንጀሉን በመማሩ ነው።
  • ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ለጌታቸውና ረዳታቸው ለአላህ የነበራቸውን መተናነስ እንመለከታለን።
  • በሐዲሡ ውስጥ (በቂያማ ቀን) መሰብሰብና መመለስ ተረጋግጧል። ሰዎች ወደ ጌታቸው በስራቸው ሊተሳሰባቸው ይመለሳሉ። መልካምን ያገኘ ሰው አላህን ያመስግን ከዛ ውጪ ያገኘ ሰው ግን ከነፍሱ ውጪ ማንንም አይውቀስ። ይህቺ በምድር የሚሰሯት ስራቸውን ነው አላህ ለነርሱ ጠብቆ የሚያቆይላቸው።
  • ሶሓቦች -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- ነቢዩ - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በእንቅልፋቸው ወቅት የነበራቸውን ሁኔታ እንኳ ሳይቀር ለመግለፅ እንደጣሩ እንረዳለን።
  • "ቀኝ እጃቸውን ከጉንጫቸው ስር አኖሩ።" ከሚለው ንግግርም እንደምንረዳው ማስረጃ በተቃራኒ መጠቀማቸውን ካስረዳው ውጪ የነቢዩ - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ተለምዷቸው በሁሉም ነገር ቀኝን እንደሚያስቀድሙ ነው።
  • በቀኝ ጎን እንቅልፍ መተኛት በዛ ሁኔታ ሲተኛ ቀልብ ስለማትረጋጋ ቶሎ ለመንቃት ያግዛል። ቀልብ ምቾት ኑሯት የምታርፈው በግራ አቅጣጫ ስትሆን ነው። ሰውዬው በግራ አቅጣጫ ሲተኛ ውስጣዊ አካላቱ ቀልቡ ላይ ስለምትደገፍ (ስለሚዘነበል) ቀልቡ ትጎዳለች።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

4 አንድ ጊዜ

سُبْحَانَ اللَّهِ (٣٣)، الْحَمْدُ لِلَّهِ (٣٣)، اللَّهُ أَكْبَرُ (٣٤)

ትርጉም እና ምንጭ

ከዓሊ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ፋጢማ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ በወፍጮ ምክንያት እጇ ላይ ስለሚያጋጥማት ጉዳይ ለማማከር መጣች። እርሳቸው ዘንድ ባሪያ እንደመጣም ወሬ ደረሳት። ቤት ስትሄድም አላገኘቻቸውምና ይህንን ለዓኢሻ አወሳችላት። እርሳቸው ሲመጡም ዓኢሻ ለርሳቸው ነገረቻቸው። ዓሊይ እንዲህ አለ: «መኝታችን ላይ ሆነን ሳለ መጡ። ለመነሳት ስንዘጋጅም "ባላችሁበት ሁኑ" አሉንና መጥተው የእግራቸው ቅዝቃዜን ሆዴ እስኪሰማው ድረስ በኔና በርሷ መካከል መጥተው ተቀመጡና እንዲህ አሉ: "ከጠየቃችሁት የተሻለን ነገር አልጠቁማችሁምን? መኝታ ስፍራችሁን የያዛችሁ ጊዜ ወይም ወደ መኝታችሁ ስፍራ የተጠጋችሁ ጊዜ ሰላሳ ሶስት ጊዜ 'ሱብሓነላህ' ሰላሳ ሶስት ጊዜ 'አልሐምዱሊላህ' ሰላሳ አራት ጊዜ ደግሞ 'አላሁ አክበር' በሉ። ይህም ለናንተ ከአገልጋይ የተሻለ ነው።"»

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሴት ልጅ የሆነችው ፋጢማ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና በወፍጮ ስትፈጭ እጇ ላይ ስለሚደርስባት ምልክት ለነቢዩ ስሞታ አቀረበች። ወደ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምርኮኛ የመጣ ጊዜ የቤት ስራን የሚተካላት ከነዚህ ምርኮኞች መካከል አንድ ሰራተኛ እንዲሰጧት ለመጠየቅም ወደርሳቸው ሄደች። ነገር ግን ቤት ውስጥ አላገኘቻቸውም። ዓኢሻን (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና ስለነበር ያገኘችው ለርሷ ነገረቻት። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቤታቸው ሲመጡም ፋጢማ ወደርሳቸው ሰራተኛን ልትጠይቃቸው መጥታ እንደነበር ነገረቻቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ፋጢማና ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ዘንድ ፍራሻቸው ላይ ለእንቅልፍ እየተዘጋጁ ሳለ ቤታቸው መጡ። ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሆዱ ላይ የነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የእግር ቅዝቃዜ እስኪሰማው ድረስ በመካከላቸው ተቀመጡ። እንዲህም አሏቸው: ሰራተኛን እንድሰጣችሁ ከጠየቃችሁኝ ይልቅ የተሻለውን ነገር አላስተምራችሁምን? እነርሱም: እንዴታ አሏቸው። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: ምሽት ላይ የእንቅልፋችሁን ስፍራ የያዛችሁ ጊዜ ሰላሳ አራት ጊዜ 'አላሁ አክበር' በሉ። ሰላሳ ሶስት ጊዜ 'ሱብሓነላህ' በሉ። ሰላሳ ሶስት ጊዜም 'አልሐምዱሊላህ' በሉ። እነዚህ ዚክሮች ለናንተ ከሰራተኛም የተሻሉ ናቸው።

ጥቅሞች

  • በነዚህ የተባረኩ ዚክሮች ላይ መዘውተር እንደሚወደድ እንረዳለን። በሌላ ቦታ እንደተላለፈው ዓሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ይህን ነቢያዊ ምክር የ"ሲፊን ምሽት" እለት እንኳ አልተዋትም።
  • ይህ ዚክር በምሽት እንቅልፍ ላይ ካልሆነ በቀር አይባልም። ሙስሊም ላይ በሙዓዝ ቢን ሹዕባ የተዘገበው ቃል "ምሽት ላይ መኝታ ስፍራችሁን የያዛችሁ ጊዜ" በሚል ቃል ነው የተዘገበው።
  • አንድ ሙስሊም በመጀመሪያው የምሽት ክፍል እነዚህን ዚክሮች የረሳ ጊዜ ከዚያም በመጨረሻው የምሽት ወቅት አስታውሶ ቢላቸው ችግር የለውም። ይህን ሐዲሥ ያወራው ዓሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና የ "ሲፊን ምሽት" ላይ በመጀመሪያው ምሽት ይህን ዚክር ማለት እንደረሳና ከዚያም ከሱብሒ በፊት አስታውሶ እንዳለው ተናግሯል።
  • ሙሀለብ እንዲህ ብለዋል: «እዚህ ሐዲሥ ውስጥ አንድ ሰው ለራሱ ከዱንያ ይልቅ መጪውን አለም ማስቀደም ላይ ነፍሱን እንደሚገፋፋው ሁሉ ቤተሰቡንም የሚችሉት በሆነ ነገር ላይ መገፋፋት እንደሚገባው እንማርበታለን።»
  • ኢብኑ ሐጀር አልዐስቀላኒ እንዲህ ብለዋል: «በነዚህ ዚክሮች ላይ የዘወተረ ሰው ስራ ቢበዛበትም አይጎዳም። ድካም እንኳን ቢሰማው ውጥረት አይሆንበትም።»
  • ዐይኒ እንዲህ ብለዋል: «የተሻለ ነው የተባለው: ወይ ዚክሮቹ ተያያዥነታቸው አኺራዊ ሲሆን ሰራተኛ ግን ተያያዥነቱ ዱንያዊ ስለሆነ ሊሆን ይችላል። አኺራዊ የሆነ ደሞ የተሻለና ቀሪ ነውና። ወይም ደግሞ ከፍላጎቷ ጋር የተያያዘም ሊሆንም ይችላል። ይህም በነዚህ ዚክሮች አማካይነት ሰራተኛ ሊሰራላት ከሚችለው የበለጠ መስራት የምትችልበትን ሀይል ታገኛለች ማለት ነው።»

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

ጥያቄዎች

በዚህ ገጽ ላይ ምን አለ?

የእንቅልፍ ዱዓ: እያንዳንዳቸው በዐረብኛ፣ ከትርጉማቸው፣ ከመጡበት ሐዲስ፣ ከደረጃቸው እና ከማብራሪያ ጋር።

ትርጉሞቹ ከየት ናቸው?

ከHadeethEnc.com፣ የተተረጎሙ የነቢዩ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ። እያንዳንዱ ሐዲስ እነሱ እንዳሳተሙት፣ ከምንጩ እና ከደረጃው ጋር እንዲሁም ወደ ዋናው የሚወስድ ማስፈንጠሪያ ይዞ ይቀርባል።

ቆጣሪው እንዴት ይሠራል?

ከዚክሩ ስር ያለውን ቆጣሪ ይንኩ፣ እስከ ዜሮ ወደ ኋላ ይቆጥራል። በዚህ ገጽ ላይ ብቻ ይሠራል፣ ምንም ነገር አይቀመጥም።

የዕለት ማስታወሻ ማግኘት እችላለሁ?

አዎ። ለAndroid የሆነው ነፃው የQabas መተግበሪያ የጠዋት እና የማታ ዚክርን በየቀኑ ያስታውስዎታል፣ ተመሳሳይ ቆጣሪም አለው።