የማታ ዚክር (አዝካሩል መሳእ) ከትርጉሙ ጋር

በትክክለኛ ሐዲሶች እንደተዘገበው፣ ማታ ከዐስር ሶላት በኋላ እና እስከ ሌሊት የሚባሉ ዚክሮች።

1 3 ጊዜ

قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ ﴿١﴾ اللَّهُ الصَّمَدُ ﴿٢﴾ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ ﴿٣﴾ وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ ﴿٤﴾
قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ ﴿١﴾ مِن شَرِّ مَا خَلَقَ ﴿٢﴾ وَمِن شَرِّ غَاسِقٍ إِذَا وَقَبَ ﴿٣﴾ وَمِن شَرِّ النَّفَّاثَاتِ فِي الْعُقَدِ ﴿٤﴾ وَمِن شَرِّ حَاسِدٍ إِذَا حَسَدَ ﴿٥﴾
قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ النَّاسِ ﴿١﴾ مَلِكِ النَّاسِ ﴿٢﴾ إِلَهِ النَّاسِ ﴿٣﴾ مِن شَرِّ الْوَسْوَاسِ الْخَنَّاسِ ﴿٤﴾ الَّذِي يُوَسْوِسُ فِي صُدُورِ النَّاسِ ﴿٥﴾ مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ ﴿٦﴾

ትርጉም እና ምንጭ

ከዐብደላህ ቢን ኹበይብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "በዝናባማና በድቅድቅ ጨለማ ምሽት የአላህ መልክተኛን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እኛን እንዲያሰግዱን ፈልገን ወጣን። አገኘኋቸውና 'በል!' አሉኝ። ምንም አላልኩኝም። ቀጥለውም 'በል!' አሉኝ። ምንም አላልኩኝም። አሁንም 'በል!' አሉኝ። እኔም ምን ልበል? አልኳቸው። እርሳቸውም 'ሱረቱል ኢኽላስ እና ሁለቱን መጠበቂያዎች (ሱረቱል ፈለቅና ሱረቱን-ናስን) ስታመሽና ስታነጋ ሶስት ጊዜ ካልክ ለሁሉም ነገር ይበቁሃል።' አሉኝ።"

አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ታላቁ ሶሐባ ዐብደላህ ቢን ኹበይብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና በርካታ ዝናብ በሚዘንብበትና ድቅድቅ ጨለማ በነበረበት ምሽት የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲያሰግዷቸው ፈልገው እንደወጡና እንዳገኟቸው ተናገረ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ "በል!" ማለትም አንብብ! አሉት። እርሱም ምንም አላነበበም። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ንግግራቸውን ሲደጋግሙለት ዐብደላህም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ልቅራ?" አላቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ሱረቱል ኢኽላስን እና ሁለቱን መጠበቂያዎች ሱረቱል ፈለቅ እና ሱረቱ አን-ናስን በምሽት ወቅትና በንጋት ወቅት ሶስት ጊዜ ቅራ! ከሁሉም ክፋትና ጉዳት ይጠብቅሃል።" አሉት።

ጥቅሞች

  • ከሁሉም ክፋት መጠበቂያ ስለሆኑ ንጋትና ምሽት ላይ ሱረቱል ኢኽላስንና ሁለቱን መጠበቂያዎች መቅራት ይወደዳል።
  • የሱረቱል ኢኽላስንና ሁለቱ መጠበቂያዎችን መቅራት ትሩፋት እንረዳለን።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

2 አንድ ጊዜ

اللَّهُمَّ بِكَ أَمْسَيْنَا، وَبِكَ أَصْبَحْنَا، وَبِكَ نَحْيَا، وَبِكَ نَمُوتُ، وَإِلَيْكَ الْمَصِيرُ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና: እርሳቸው ያነጉ ጊዜ እንዲህ ይሉ ነበር "አልላሁመ ቢከ አስበሕና ወቢከ አምሰይና ወቢከ ነሕያ ወቢከ ነሙቱ ወኢለይከ ኑሹር" ትርጉሙም "አላህ ሆይ በአንተ አነጋን፣ በአንተም አመሸን፣ በአንተም ህያው እንሆናለን፣ በአንተም እንሞታለን፣ መቀስቀስም ወደ አንተ ነው።" ያመሹ ጊዜ ደግሞ እንዲህ ይሉ ነበር "አልላሁመ ቢከ አምሰይና ወቢከ አስበሕና ወቢከ ነሕያ ወቢከ ነሙቱ ወኢለይከ ኑሹር" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! በአንተ አመሸሁ፣ በአንተም አነጋሁ፣ በአንተም ህያው እንሆናለን፣ በአንተም እንሞታለን፣ መቀስቀስም ወደ አንተ ነው።" በሌላ ጊዜም እንዲህ ብለዋል "… ወኢለይከል መሲር" ትርጉሙም "… መመለሻም ወደ አንተ ነው።"

رواه أبو داود والترمذي والنسائي في الكبرى وابن ماجه ደረጃ: ሐሰን ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በርሳቸው ላይ ንጋት የገባ ጊዜ (ይህም ጎህ ከመውጣቱ ጋር የቀኑ መጀመሪያ የሆነ ጊዜ ነው።) እንዲህ ይሉ ነበር:

(አላህ ሆይ! በአንተ አነጋን) በጥበቃህ ተከልለን፣ በፀጋህ ተሸፍነን፣ አንተን በማውሳት ተጠምደን፣ በስምህ ታግዘን፣ በመግጠምህ ተከበን፣ በብልሃትህና በሀይልህ ተንቀሳቃሽ ሆነን አነጋን ማለት ነው። (በአንተ አመሸን፣ በአንተ ህያው እንሆናለን፣ በአንተም እንሞታለን።) ይህ ማለት ምሽት ላይ ከማድረግ ጋር ቀደም ተብሎ እንደተብራራው እንዲህ ይላል: አላህ ሆይ ባንተ አምሽተናል፣ ህያው አድራጊ በሆነው ስምህ ህያው እንሆናለን። ህይወትን የሚነጥቅ በሚለው ስምህ እንሞታለን። (መቀስቀስም ወዳንተ ነው።) መቀስቀስ ከሞት በኋላ ነው፤ መለያየት ከመሰብሰብ በኋላ ነው። በሁሉም ወቅቶች ሁኔታችን በዚህ ሁኔታ ይቀጥላል። በተቀሩትም ሁኔታዎቼ ከአላህ አልላቀቅምም አልተወውምም።

ከዐስር በኋላ ምሽት የገባ ጊዜም (አላህ ሆይ! በአንተ አመሸሁ፣ በአንተም አነጋሁ፣ በአንተም ህያው እንሆናለን፣ በአንተም እንሞታለን፣ መመለስም ወደ አንተ ነው።) ይሉ ነበር። በዱንያም መመለሻዬ፣ በመጨረሻም መመለሻዬ ወደ አንተ ነው። ህያው የምታደርገኝም አንተው ነህ፤ የምትገድለኝም አንተው ነህ። ማለት ነው።

ጥቅሞች

  • በንጋትና ምሽት ወቅት ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በመከተል አኳያ ይህን ዱዓ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  • አንድ ባሪያ በሁሉም ሁኔታዎቹና ወቅቶቹ ወደ ጌታው ፈላጊ መሆኑን እንረዳለን።
  • ንጋት ላይ አዝካሮችን ለመቅራት በላጩ ወቅት የንጋቱን ጎህ ከወጣችበት ጀምሮ የቀኑ መጀመሪያ ላይ ፀሃይ እስክትወጣ ድረስ፤ የምሽቱን ከዓስር በኋላ ጀምሮ ፀሃይ ከመግባቷ በፊት ድረስ ያለው ወቅት ነው። ከዚህ በኋላ ቢለው ማለትም የንጋቱን ረፋዱ ከፍ ካለ በኋላ ቢለው ይበቃለታል። ከዙህር በኋላ ቢለውም ይበቃለታል። የምሽቱንም ከመግሪብ በኋላም ቢለው ይህ የዚክር ወቅት ስለሆነ ይበቃለታል።
  • "መቀስቀስም ወደ አንተ ነው።" የሚለው ንግግር ከንጋት ጋር የሚያገናኘው ይህ ቃል ሰዎች ከሞቱ በኋላና የትንሳኤ ቀን በሚቀሰቀሱ ጊዜ ያለውን ህያው መደረግና ትልቁን መቀስቀስ ስለሚያስታውሰው ነው። ከእንቅልፉ የሚነቃበት ይህ ቀንም ነፍሶች የሚመለሱበትና ሰዎች የሚበተኑበት፣ አላህ የፈጠረው አዲስ ንጋት የሚተነፍስበት አዲስ መቀስቀስና አዲስ ቀን ነው። ይህም አዲስ ንጋት በአደም ልጅ ላይ ምስክር እንዲሆን፣ ወቅቶቹና ሰአቶቹም የስራዎቻችን ድልብ የሚሆኑበት [ሌላ እድል] ነው።
  • "መመለስም ወደ አንተ ነው።" የሚለው ቃል የምሽት ዚክር ላይ ተስማሚ የሆነው፤ ሰዎች ከስራዎቻቸው፣ ለጥቅማቸውና ለኑሯቸው ከተበታተኑ በኋላ ወደ ቤታቸው በሚመለሱ ጊዜ ወደ የማደሪያቸው መጥተው ማረፍን ያዘወትራሉ። ይህም ወደ አላህ ተባረከ ወተዓላ መመለስን ያስታውሳል።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

3 አንድ ጊዜ

اللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ خَلَقْتَنِي وَأَنَا عَبْدُكَ وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ أَبُوءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَيَّ وَأَبُوءُ لَكَ بِذَنْبِي فَاغْفِرْ لِي فَإِنَّهُ لَا يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا أَنْتَ

ትርጉም እና ምንጭ

ከሸዳድ ቢን አውስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የምህረት አጠያየቅ (የኢስቲግፋር) አለቃ 'አልላሁመ አንተ ረቢ ላ ኢላሃ ኢላ አንተ፣ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱክ፣ ወአነ ዓላ ዐህዲከ ወወዕዲከ ማስተጦዕቱ፣ አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማ ሶነዕቱ፣ አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፣ ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ ፈግፊር ሊ፣ ፈኢነሁ ላየግፊሩዝ-ዙኑበ ኢላ አንተ።' ማለትህ ነው።'" እንዲህም ብለዋል "በርሷ አምኖ ቀን ላይ ያላትና በዛው ቀን ከማምሸቱ በፊት የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ባለቤቶች ነው። በርሷ አምኖ ምሽት ላይ ያላትና ከማንጋቱ በፊት የሞተ ሰውም እርሱ ከጀነት ባለቤቶች ነው።" (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ፈጥረሀኛል እኔም ባሪያህ ነኝ፣ እኔ በቻልኩት መጠን በቃል ኪዳንህ ላይ እገኛለሁ፤ ከሰራሁት ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ፣ በኔ ላይ የዋልከውን ፀጋ አረጋግጣለሁ፣ ወንጀሌንም ላንተ አረጋግጣለሁና ማረኝ! እነሆ ካንተ በቀር ወንጀሎችን የሚምር የለምና።)

ቡኻሪ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ምህረት የሚጠየቅበት የተለያዩ ቃላቶች እንዳሉና በላጩና ትልቁ አንድ ባሪያ እንዲህ ብሎ መጠየቁ እንደሆነ ተናገሩ: "አልላሁመ አንተ ረቢ ላ ኢላሃ ኢላ አንተ፣ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱክ፣ ወአነ ዓላ ዐህዲከ ወወዕዲከ ማስተጦዕቱ፣ አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማ ሶነዕቱ፣ አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፣ ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ ፈግፊር ሊ፣ ፈኢነሁ ላየግፊሩዝ-ዙኑበ ኢላ አንተ።" (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ፈጥረህኛል እኔም ባሪያህ ነኝ፣ እኔ በቻልኩት መጠን በቃል ኪዳንህ ላይ እገኛለሁ፤ ከሰራሁት ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ፣ በኔ ላይ የዋልከውን ፀጋ አረጋግጣለሁ፣ ወንጀሌንም ላንተ አረጋግጣለሁና ማረኝ! እነሆ ካንተ በቀር ወንጀሎችን የሚምር የለምና።) በቅድሚያ ባሪያው የአላህን ብቸኝነት ያረጋግጣል። አላህ ፈጣሪው፣ ምንም አጋር ሳይኖረው የሚያመልከው መሆኑን፤ ጥራት ለተገባው አላህ የገባውን በርሱ የማመንና ለርሱ ታዛዥ የመሆንን ቃልኪዳን በአቅሙ ልክ እንደሚወጣ ያረጋግጣል። በአቅሙ ልክ ቃሉን እንደሚወጣ የሚያረጋግጠውም አንድ ባሪያ ምንም ያክል በአምልኮ ላይ ቢቆም አላህ ያዘዘውን ሁሉ መፈፀም ስለማይችል ነው። ለተዋለለት ፀጋ የሚገባውን ምስጋናም ማቅረብ አይችልም። ወደ አላህም ይጠጋል፣ በርሱም ይጠበቃል፣ ባሪያ ከሰራው ክፋት መጠበቂያው አላህ ነውና። አላህ ለርሱ የዋለለትን ፀጋም በታዛዥነት ለርሱ ያረጋግጣል፤ እውቅናንም ይሰጣል። ወደ ነፍሱ በመመለስም ወንጀሉና ኃጢአቱን ያረጋግጣል፤ ያምናልም። በዚህ መልኩ ወደ አላህ ከተቃረበ በኋላ ጌታው እንዲምረው፣ ወንጀሎቹን እንዲሸሽግለት፣ በይቅር ባይነቱ፣ በችሮታውና እዝነቱ ከወንጀሎቹ እንዲጠብቀውም ዱዓ ያደርጋል። ምክንያቱም ከአላህ በቀርም ወንጀሎችን የሚምር የለምና። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህቺ ዱዓ ከንጋትና ምሽት ውዳሴዎች መካከል መሆኗንና በቀኑ መጀመሪያ ፀሀይ ከወጣችበት ጊዜ አንስቶ ወደ መግቢያዋ ዘንበል እስክትል ድረስ ባለው ወቅት ላይ በእርግጠኝነት፣ መልዕክቷን በማሰብ አምኖባት ካለ በኃላ የሞተ ሰው ጀነት የሚገባ መሆኑን ተናገሩ። በምሽትም ወቅት እርሱም ፀሀይ ከገባችበት አንስቶ ጎህ እስኪወጣ ድረስ ያለ ሰውና ከመንጋቱም በፊት የሞተ ጀነት ይገባል።

ጥቅሞች

  • ምህረትን የመጠየቂያ ቃላቶች የተለያዩ ሲሆኑ ከፊሉም ከከፊሉ ይበላለጣል።
  • አንድ ባሪያ በዚህ ዱዓ አላህን ለመለመን መጓጓት ይገባዋል። ምክንያቱም የምህረት አጠያየቅ (የኢስቲግፋር) አለቃ ነውና።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

4 3 ጊዜ

بِسْمِ اللَّهِ الَّذِي لَا يَضُرُّ مَعَ اسْمِهِ شَيْءٌ فِي الْأَرْضِ وَلَا فِي السَّمَاءِ وَهُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአባን ቢን ዑሥማን እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዑሥማን ቢን ዐፋን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ሲሉ ሰማሁዋቸው: "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰማሁዋቸው: ‹ሶስት ጊዜ 'ቢስሚላሂለዚ ላየዱሩ መዐስሚሂ ሸይኡን ፊልአርዲ ወላፊስሰማእ ወሁወስ'ሰሚዑል ዐሊም' (ትርጉሙም: በዚያ ከስሙ ጋር በምድርም ይሁን በሰማይ ምንም ነገር የማይጎዳ በሆነው እንዲሁም ሰሚና አዋቂ በሆነው አላህ ስም።) ያለ ሰው እስኪነጋ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም። በሚያነጋ ጊዜም ሶስት ጊዜ ያላት ሰው እስኪያመሽ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም።› አባን ቢን ዑሥማንን የግማሽ አካል ሽባነት አገኘውና ከርሱ ይሄን ሐዲሥ የሰማው ሰውዬም አተኩሮ ተመለከተው። አባንም ለርሱ እንዲህ አለው: እንደዚ አተኩረህ የምታየኝ ምን ሆነው ነህ? በአላህ እምላለሁ! በዑሥማን ላይ ምንም አልዋሸሁም! ዑሥማንም በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ምንም አልዋሸም። ነገር ግን ዛሬ የደረሰብኝ ነገር የደረሰው ተቆጥቼ ስለነበር ይህን ዚክር ማለት ረስቼ ስለነበር ነው።"»

አቡዳወድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁሉ ቀን ጎህ ከቀደደ በኋላ ንጋት ላይና ፀሀይ ከመግባቷ በፊት ደግሞ ሁሌ ምሽት ላይ ሶስት ጊዜ ይህንን ዚክር ያለ ሰው:(ቢስሚላሂ) በአላህ ስም ከሁሉም ጎጂ ነገር እጠበቃለሁም እታገዛለሁም። (ያ ስሙን ከማውሳት ጋር) ምንም ያህል ቢተልቅ (አንዳችም የማይጎዳው) (በምድርም ውስጥ) ከምድር የሚወጡ በሆኑ መከራዎችም (በሰማይ ውስጥም) ከሰማይ የሚወርዱ በሆኑ መከራዎችም (እርሱ ንግግራችንን ሰሚ) ሁኔታችንንም (አዋቂ ነው።) የምንጎዳ አይደለንም።

በሚያመሽ ወቅት የተናገራት እስኪያነጋ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም። በሚያነጋ ወቅት የተናገራት ደግሞ እስኪያመሽ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም።

ሐዲሡን ያወራው አባን ቢን ዑስማንን በወቅቱ የሰውነቱ ግማሽ ሽባ የመሆን በሽታ አጋጥሞት ስለነበር ከርሱ ይሄን ሐዲሥ የሰማው ሰውዬም በግርምት አይን ተመለከተው። አባንም ለሰውዬው እንዲህ አለው "እንደዚህ የምትመለከተኝ ምን ሆነህ ነው? በአላህ እምላለሁ! በዑሥማንም ላይ አልዋሸሁም። ዑሥማንም በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ አልዋሸም። ነገር ግን ይህ በሽታ ባጋጠመኝ እለት አላህ እንድለው አልወሰነልኝም ነበር። የሚያስቆጣ ነገር አጋጠመኝና እነዚህን የተጠቀሱ ቃላቶች ማለትን ዘነጋሁኝ።"

ጥቅሞች

  • ሰውዬው በአላህ ፍቃድ ከድንገተኛ መከራ ወይም ከመከረኛ ጦስ ወይም ከመሳሰሉት የተጠበቀ እንዲሆን ንጋት ላይና ምሽት ላይ እነዚህን ዚክሮች ማለት እንደሚወደድ እንረዳለን።
  • የመጀመሪያዎቹ ቀደምቶች በአላህ ላይ ያላቸው እርግጠኝነትና የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በተናገሩት ላይ ያላቸው እምነት ጠንካራ መሆኑን እንረዳለን።
  • ዚክር በንጋትና በምሽት ላይ የመገደቡ ካሉት ጥቅሞች መካከል ከሙስሊም ላይ ዝንጉነትን መቁረጥና ዘውትር እርሱ የአላህ ባሪያ መሆኑን እንዲያስታውስ ማድረግ ይገኝበታል።
  • አላህን የሚያወሳው ሰው ካለው ኢኽላስና የቂን (እርግጠኝነት) ጋር ባለው ኢማን፣ መተናነስና ልቡን እንደማቅረቡ ልክ የዚክሩ ተፅዕኖም የተረጋገጠ ይሆናል።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

5 አንድ ጊዜ

اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي دِينِي وَدُنْيَايَ وَأَهْلِي وَمَالِي، اللَّهُمَّ اسْتُرْ عَوْرَاتِي، وَآمِنْ رَوْعَاتِي، اللَّهُمَّ احْفَظْنِي مِنْ بَيْنِ يَدَيَّ، وَمِنْ خَلْفِي، وَعَنْ يَمِينِي، وَعَنْ شِمَالِي، وَمِنْ فَوْقِي، وَأَعُوذُ بِعَظَمَتِكَ أَنْ أُغْتَالَ مِنْ تَحْتِي

ትርጉም እና ምንጭ

ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሚያመሹና በሚያነጉ ጊዜ እነዚህን ዱዓዎች ከማድረግ አይተዉም ነበር። "አላሁመ ኢኒ አስአሉከልዓፊያተ ፊድ-ዱንያ ወልአኺረቲ፣ አላሁመ ኢኒ አስአሉከል ዐፍወ ወልዓፊየተ ፊ ዲኒ ወዱንያየ ወአህሊ ወማሊ፣ አላሁም ስቱር ዐውረቲ -አው ዓውራቲ- ወአሚን ረውዓቲ፣ አሏሁም ሕፈዝኒ ሚን በይኒ የደየ፣ ወሚን ኸልፊ፣ ወዓን የሚኒ፣ ወዓን ሺማሊ፣ ወሚን ፈውቂ፣ ወአዑዙ ቢአዞመቲክ 'አን ኡግታለ ሚን ተሕቲ"» ትርጉሙም (አላህ ሆይ! በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፤ አላህ ሆይ በዱንያዬ፣ በመጪው አለሜ፣ በቤተሰቤና ገንዘቤ ይቅርታህንና ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፤ አላህ ሆይ ነውሬን ወይም ነውሮቼን ሸሽግልኝ፣ ከፍርሃቴም ደህንነትን ስጠኝ፤ አላህ ሆይ! ከፊት ለፊቴም፣ ከኋላዬም፣ ከቀኜም፣ ከግራዬም፣ ከበላዬም ጠብቀኝ! ከበታቼ ድንገታዊ ጥቃት ከሚደርስብኝም በልቅናህ እጠበቃለሁ።) ማለት ነው።

አቡዳውድ፣ ነሳኢ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሲመሽና ሲነጋ እነዚህን ዱዓዎች ከማድረግ አይተዉም ነበር።

(አላሁመ ኢኒ አስአሉከል ዓፊየተ) አላህ ሆይ! ከአለማዊ በሽታዎች፣ መከራዎችና ችግሮች፣ ከዲናዊ ፈተናዎችና ዝንባሌዎች ሰላም መሆንን (ፊድዱንያ ወልአኺረተ) በቅርቡም ሆነ በመጪው አለም እጠይቅሃለሁ።

(አልላሁመ ኢኒ አስአሉከል ዐፍው) አላህ ሆይ! ወንጀሎቼን ማበስ፣ ይቅር ማለትህን (ወልዓፊየተ) ከነውር መፅዳትን (ፊዲኒ) በሃይማኖቴ ከሽርክ፣ ከቢድዓና ከወንጀሎች፤ (ወዱንያየ) በዓለማዊ ህይወቴ ደግሞ ከመከራዎች፣ ከሚያውክና ከክፋቶች (ወአህሊ) በቤተሰቤ ላይ በባለቤቴ፣ በልጆቼና ቅርብ ዘመዶቼ (ወማሊ) በገንዘቤና በስራዬ ላይ ደህና መሆንን እጠይቅሃለሁ።

(አልላሁመስቱር ዐውራቲ) አላህ ሆይ! እኔ ላይ ያሉትን ነውሮች፣ ጉድለቶች፣ እንከኖችን ሸሽገኝ፤ ወንጀሌንም አብስ። (ወአሚን ረውዓቲ) ድንጋጤዬንና ፍርሃቴን ደህንነት ስጠው።

(አልላሁመሕፈዝኒ) አላህ ሆይ! የሚያውኩኝንና መከራዎችን ከኔ አስወግድልኝ። (ሚን በይኒ የደየ፣ ወሚን ኸልፊ፣ ወዓን የሚኒ፣ ወዓን ሺማሊ፣ ወሚን ፈውቂ) (ከፊት ለፊቴም፣ ከኋላዬም፣ ከቀኜም፣ ከግራዬም፣ ከበላዬም) በዚህም አላህ ከሁሉም አቅጣጫዎች እንዲጠብቃቸው ጠየቁ። መከራዎችና መአቶች ወደ ሰው የሚመጡትና የሚዞሩት ከነዚህ አቅጣጫዎች መካከል በአንዱ ነውና።

(ወአዑዙ ቢዐዞመቲከ አንኡግታል) በድንገት ከመያዝና ተዘናግቼ ከምጠፋ በልቅናህ እጠበቃለሁ። (ሚንተሕቲ) በመሬት መደርመስ ከመጥፋትም ባንተ እጠበቃለሁ።

ጥቅሞች

  • መልክተኛውን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በመከተል እነዚህን ቃላቶች መጠባበቅ እንደሚገባ እንረዳለን።
  • የሰው ልጅ የሃይማኖቱን ደህንነት አላህን እንዲጠይቅ እንደታዘዘው ሁሉ ለዓለማዊ ጉዳዩም እንዲጠይቅ ታዟል።
  • ጢቢይ እንዲህ ብለዋል: «ስድስቱን አቅጣጫዎች ማጠቃለላቸው የመከራዎች መምጣት በነርሱ በኩል ስለሆነ ነው። የታች አቅጣጫን አበክረው የጠቀሱት ከታች የሚመጣ መከራ አዋራጅ ስለሆነ ነው።»
  • ንጋት ላይ አዝካሮችን ለመቅራት በላጩ ወቅት: ጎህ ከወጣ ጀምሮ የቀኑ መጀመሪያ ላይ ፀሃይ እስክትወጣ ድረስና ከዐስር በኋላ ፀሃይ እስክትገባ ድረስ ነው። ከዚህ በኋላም ቢል ማለትም ረፋዱ ከፍ ካለ በኋላም ቢል ይበቃለታል። ከዙህር በኋላም ቢል ይበቃለታል። ከመግሪብ በኋላም ቢል ይበቃለታል። ይህም የዚክር ወቅት ነውና።
  • ዚክሩ መባል ያለበት በተለየ ወቅት እንደሆነ ማስረጃ ከጠቆመ የሱረቱል በቀራ መጨረሻ ሁለት አንቀጾችን ምሽት ላይ መቅራትን ይመስል ፀሃይ ከገባ በኋላ ምሽት ላይ ነው የሚፈፀመው።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

6 አንድ ጊዜ

آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنْزِلَ إِلَيْهِ مِنْ رَبِّهِ وَالْمُؤْمِنُونَ كُلٌّ آمَنَ بِاللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِنْ رُسُلِهِ وَقَالُوا سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا غُفْرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيْكَ الْمَصِيرُ ﴿٢٨٥﴾ لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا لَهَا مَا كَسَبَتْ وَعَلَيْهَا مَا اكْتَسَبَتْ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَا إِنْ نَسِينَا أَوْ أَخْطَأْنَا رَبَّنَا وَلَا تَحْمِلْ عَلَيْنَا إِصْرًا كَمَا حَمَلْتَهُ عَلَى الَّذِينَ مِنْ قَبْلِنَا رَبَّنَا وَلَا تُحَمِّلْنَا مَا لَا طَاقَةَ لَنَا بِهِ وَاعْفُ عَنَّا وَاغْفِرْ لَنَا وَارْحَمْنَا أَنْتَ مَوْلَانَا فَانْصُرْنَا عَلَى الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ ﴿٢٨٦﴾

ትርጉም እና ምንጭ

ከአቢ መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "በምሽት ውስጥ የመጨረሻዎቹን የበቀራህ ምእራፍ ሁለት አንቀፆች የቀራ ሰው ይበቁታል።"

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በምሽት ውስጥ የበቀራህ ምእራፍ የመጨረሻዎቹን ሁለት አንቀፆች የቀራ ሰው አላህ መጥፎና ጎጂ ከሆኑ ነገሮች እንደሚበቃው ተናገሩ። ለሌሊት ሶላት ከመቆም ይበቁታል ማለት ነውም ተብሏል። ሌሎች ውዳሴዎችን ከማለት ይበቁታል ማለት ነውም ተብሏል። ለሌሊት ሶላት የሚቀራ ዝቅተኛው በቂ የቁርአን አንቀፆች ናቸውም ተብሏል። ከዚህም ውጪ ተብሏል። ምንአልባት ሁሉም ከላይ የተጠቀሱትን ትርጓሜዎችን ቃሉ ስለሚሰበስባቸው ሁሉም ትክክለኛ ትርጓሜ ሊሆኑ ይችላሉ።

ጥቅሞች

  • የሱረቱል በቀራህ የመጨረሻ አንቀፆች ትሩፋት መገለፁ። እሱም { አመነ አርረሱሉ …} ከሚለው የአላህ ንግግር እስከምእራፉ መጨረሻ ያለውን ነው።
  • የበቀራህ ምእራፍ መጨረሻዎች ምሽት ላይ ለሚቀራቸው ሰው ከጉዳት፣ ከመጥፎና ከሰይጣን ይከላከላሉ።
  • ምሽት የሚባለውም ፀሃይ ስትገባ ይጀምርና ጎህ ስትወጣ ይጠናቀቃል።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

7 10 ጊዜ

لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአቡ አዩብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "አስር ጊዜ 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር' ያለ ሰው ከኢስማዒል ዘሮች የሆኑ አራት ነፍሶችን ነፃ እንዳወጣ ይቆጠርለታል።"

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

በዚህ ሐዲሥ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደሚነግሩን ይህንን ውዳሴ ያለ፦ "ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ትርጉሙም: "ከአላህ ውጪ በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፤ ብቸኛና ለሱ አጋር የለውም፤ ጥራት የተገባው አላህ በምሉዕ ንግስና የተለየ ነው፤ ከሱ ውጪ ያሉት የማይገባቸውን ውዳሴና ሙገሳ ከውዴታና ልቅና ጋር በብቸኝነት የተገባው ነው ፤ እርሱም አንዳችም የማያቅተው ቻይ ነው።" ማለት ነው። ይህንን ታላቅ ውዳሴም በቀን አስር ጊዜ የደጋገመም ሰው በነርሱ ላይ የአላህ ሶላትና ሰላም ይስፈንና የኢብራሂም ልጅ ከሆኑት ከኢስማዒል ዘሮች አራት ባሮችን ከባርነት ነፃ እንዳወጣ ሰው ምንዳ አምሳያ ለርሱ ይኖረዋል። የኢስማዒል ዐለይሂ ሰላም ዘሮች የተለዩትም እነርሱ ከሌሎች የላቁ ስለሆኑ ነው።

ጥቅሞች

  • የዚህ ውዳሴ ትሩፋት አላህን በተመላኪነት፣ በንግስና፣ በምስጋናና በተሟላ ችሎታ መነጠልን ያካተተ ነው።
  • ይህንን ውዳሴ አከታትሎም ሆነ በተለያየ ቆይታ ያለ ሰው የዚህን ውዳሴ ምንዳ እንደሚያገኝ እንረዳለን።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

8 100 ጊዜ

سُبْحَانَ اللَّهِ وَبِحَمْدِهِ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ሱብሓነላሂ ወቢሐምዲሂ "ጥራት ምስጋና ለአላህ ይገባው።" ያለ ሰው (የወንጀሉ ብዛት) የባህር ዓረፋ አምሳያ ቢሆን እንኳ ወንጀሉ ይታበስለታል።"

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ "ሱብሓነሏሂ ወቢሐምዲሂ" (ጥራት ምስጋና ለአላህ ይገባው።) ያለ ሰው ባህር በሚናወጥ ወቅት ከላዩ እንደሚንጣለለው ነጭ አረፋ አምሳያ ወንጀሉ የበዛ ቢሆን እንኳ ወንጀሉ ይማራል ይታበሳል ብለው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።

ጥቅሞች

  • ይህን ምንዳ የሚያገኘው በቀን ውስጥ አከታትሎም ይሁን በተለያየ ጊዜ እነዚህን ቃላት ያለ ሰው ነው።
  • ተስቢሕ ማለት: - አላህን ከጉድለት ማጥራት ሲሆን ፤ ሐምድ ማለት ደግሞ አላህን ከመውደድና ከማላቅ ጋር በምሉዕነት መግለፅ ነው።
  • በሐዲሡ ወንጀልን ማስማር ከሚለው የተፈለገበት ትናንሽ ወንጀሎችን ብቻ ነው። ትላልቅ ወንጀሎች ግን የግድ ተውበት ያስፈልጋቸዋል።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

ጥያቄዎች

በዚህ ገጽ ላይ ምን አለ?

የማታ ዚክር: እያንዳንዳቸው በዐረብኛ፣ ከትርጉማቸው፣ ከመጡበት ሐዲስ፣ ከደረጃቸው እና ከማብራሪያ ጋር።

ትርጉሞቹ ከየት ናቸው?

ከHadeethEnc.com፣ የተተረጎሙ የነቢዩ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ። እያንዳንዱ ሐዲስ እነሱ እንዳሳተሙት፣ ከምንጩ እና ከደረጃው ጋር እንዲሁም ወደ ዋናው የሚወስድ ማስፈንጠሪያ ይዞ ይቀርባል።

ቆጣሪው እንዴት ይሠራል?

ከዚክሩ ስር ያለውን ቆጣሪ ይንኩ፣ እስከ ዜሮ ወደ ኋላ ይቆጥራል። በዚህ ገጽ ላይ ብቻ ይሠራል፣ ምንም ነገር አይቀመጥም።

የዕለት ማስታወሻ ማግኘት እችላለሁ?

አዎ። ለAndroid የሆነው ነፃው የQabas መተግበሪያ የጠዋት እና የማታ ዚክርን በየቀኑ ያስታውስዎታል፣ ተመሳሳይ ቆጣሪም አለው።