ከጥሩ ወይም ከመጥፎ ሕልም በኋላ ምን ይደረጋል

ከጥሩ ሕልም በኋላ እና ከሚያስፈራ ሕልም በኋላ የሚደረገው እና የሚባለው።

1 አንድ ጊዜ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአቡ ቀታዳህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "መልካም ህልም ከአላህ ነው። መጥፎ ህልም ከሸይጧን ነው። አንዳችሁ የሚፈራውን መጥፎ ህልም የተመለከተ ጊዜ ወደ ግራው ይትፋ፤ ከህልሙ ክፋትም በአላህ ይጠበቅ። ያኔ እርሷም አትጎዳውም።"»

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በእንቅልፍ የሚያስደስት መልካም ህልም መመልከት ከአላህ እንደሆነና የሚጠላውንና የሚያሳዝነውን ቅብዥር መመልከት ደግሞ ከሸይጧን እንደሆነ ተናገሩ።

የሚጠላውን ህልም የተመለከተ ሰው ወደ ግራው አቅጣጫ ይትፋ፤ ከህልሙ ክፋትም በአላህ ይጠበቅ። ቅብዥሩን ተከትሎ ከሚመጡ ጎጂዎች ሰላም ለመሆን የተጠቀሰውን ማድረግ አላህ ሰበብ ስላደረገው እርሷ አትጎዳውም።

ጥቅሞች

  • "ሩእያ" እና "ሑልም" የሚሉት ሁለት የዐረብኛ ቃላቶች የተኛ ሰው በእንቅልፉ የሚያየውን የሚገልፁ ቃላቶች ሲሆኑ ነገር ግን "ሩእያ" የሚለው ቃል በብዛት በህልሙ ለሚያየው መልካምና ጥሩ ነገር ሲውል፤ "ሑልም" የሚለው ቃል ደግሞ በብዛት በህልሙ ለሚያየው መጥፎና አስቀያሚ ነገር ይውላል። እያንዳንዱ ቃል ግን በሌላኛው ቦታ ላይ ሊውል ይችላል።
  • የህልም ክፍሎች: 1 - መልካም ህልም: ይህም የሚያያት ወይም የሚታይለት የሆነ እውነተኛና ከአላህ የሆነ ብስራት ነው። 2 - ቅዥት: ይህም ሰውዬው ነቅቶ ባለበት በውስጡ ሲያብሰለስለው የነበረውን ተኝቶ ማየቱ ነው። 3 - የሸይጧን ማሳዘኛና ማስፈራሪያ የሆነ፣ የአደምን ልጅ ለማስፈራራት ከርሱ የሆኑ ማስደንገጫዎች የሆነ ቅብዥር ነው።
  • መልካም ህልም ባየ ሰው ዙሪያ የተጠቀሱት ነጥቦች ሶስት ናቸው: አላህን ማመስገን፣ በህልሙ መደሰትና ስላየው ህልም መናገር ነው። ነገር ግን የሚናገረው ለሚጠላው ሳይሆን ለሚወደው ሰው ብቻ ነው።
  • የሚጠላውን ህልም ባየ ሰው አደብ ዙሪያ የተጠቀሱት ነጥቦች አምስት ነገሮች ናቸው: ከህልሙ ክፋትና ከሸይጧን ክፋት በአላህ መጠበቅ፤ ከእንቅልፉ በሚነቃ ጊዜ ወደ ግራው ዞሮ ሶስት ጊዜ መትፋት፤ ከመሰረቱ ለአንድም ሰው አለመንገር፤ ወደ መኝታው መመለስ ከፈለገ የነበረበትን ጎን ቀይሮ መዞር ነው። ይህን ካደረገ ህልሙም አይጎዳውም።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

2 አንድ ጊዜ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ የአላህ መልዕክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቷል፦ "አንዳችሁ የሚወደውን ህልም በተመለከተ ጊዜ እርሷ ከአላህ ናትና በርሷ ምክንያት አላህን ያመስግንም ለሌሎችም ያውራት፤ ከዚህ ውጪ የሚጠላውን ህልም የተመለከተ ጊዜ ደሞ እርሷ ከሸይጧን ናትና ከክፋቷ በአላህ ይጠበቅ፤ ለአንድም ሰው አያውራ። እርሷም አትጎዳውም።"

ቡኻሪ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የሚያስደስት መልካም ህልም ማየት ከአላህ እንደሆነ ተናገሩ። በርሱም ላይ አላህን እንዲያመሰግንና ስለርሱም እንዲናገር ጠቆሙ። የሚጠላውንና የሚያሳዝነውን ህልም ያየ ጊዜ ደግሞ ከሸይጧን ነውና ከክፋቱ በአላህ እንዲጠበቅና ለአንድም ሰው እንዳያወራም ጠቆሙ። ህልምን ተከትሎ ከሚመጡ ጎጂ ነገሮች ሰላም ለመሆን ከላይ የተጠቀሰውን ማድረግ አላህ ሰበብ ስላደረገው ምንም አይጎዳውም።

ጥቅሞች

  • የህልም ክፍሎች: 1- መልካም ህልም: ይህም እውነተኛ የሆነ ህልምና ለሚያየው ወይም ለታየለት ሰው ከአላህ የሆነ ብስራት ነው። 2- በውስጡ ያወራው: ይህም ሰውዬው በነቃበት ወቅት ለነፍሱ ያወራው ነው። 3- ሸይጧን የአደም ልጆችን ለማሳዘን የሚያሳያቸው የሸይጣን ማሳዘኛ፣ ማስፈራሪያና ማስደንገጫ የሆነ ህልም ነው።
  • መልካም ህልም ባየ ሰው ዙሪያ የተጠቀሱት ነጥቦች ሶስት ናቸው: አላህን ማመስገን፣ በህልሙ መደሰትና ስላየው ህልም መናገር ናቸው። ነገር ግን የሚናገረው ለሚጠላው ሳይሆን ለሚወደው ሰው ብቻ ነው።
  • የሚጠላውን ህልም ባየ ሰው አደብ ዙሪያ የተጠቀሱ ነጥቦች አምስት ነገሮች ናቸው: ከህልሙ ክፋትና ከሸይጧን ክፋት በአላህ መጠበቅ፣ ከእንቅልፉ በሚነቃ ጊዜ ወደ ግራው ዞሮ ሶስት ጊዜ መትፋት፣ ከመሰረቱ ለማንም ሰው አለመንገር፣ ወደ መኝታው መመለስ ከፈለገ የነበረበትን ጎን ቀይሮ መዞር ነው። ህልሙም አይጎዳውም።
  • ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «መልካም ህልም ሲያይ ለማይወደው ሰው ያለመናገሩ ጥበብ መልካም ህልሙን ለማይወደው ሰው ሲናገር በጥላቻ ወይም በምቀኝነት ምክንያት በማያስደስተው ነገር ይፈታለትና በፈታለት መልኩም ሊከሰት ስለሚችል ነው። ወይም ያ የማይወደው ሰው በሰማው መልካም ህልም ትካዜና ብስጭቱ ሊቻኮልበት ስለሚችል ነው። ስለዚህም በዚህ ምክንያት ለማይወደው ሰው ማውራትን እንዲተው ታዘዘ።»
  • የአላህ ፀጋዎች በሚከሰቱና ችሮታዎች በሚታደሱ ወቅት ማመስገን እንደሚገባና ይህም እንዲዘወትር ማድረጊያ አንዱ ሰበብ መሆኑን እንረዳለን።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

ጥያቄዎች

በዚህ ገጽ ላይ ምን አለ?

ከመጥፎ ሕልም በኋላ ዱዓ: እያንዳንዳቸው በዐረብኛ፣ ከትርጉማቸው፣ ከመጡበት ሐዲስ፣ ከደረጃቸው እና ከማብራሪያ ጋር።

ትርጉሞቹ ከየት ናቸው?

ከHadeethEnc.com፣ የተተረጎሙ የነቢዩ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ። እያንዳንዱ ሐዲስ እነሱ እንዳሳተሙት፣ ከምንጩ እና ከደረጃው ጋር እንዲሁም ወደ ዋናው የሚወስድ ማስፈንጠሪያ ይዞ ይቀርባል።

የዕለት ማስታወሻ ማግኘት እችላለሁ?

አዎ። ለAndroid የሆነው ነፃው የQabas መተግበሪያ የጠዋት እና የማታ ዚክርን በየቀኑ ያስታውስዎታል፣ ተመሳሳይ ቆጣሪም አለው።