ከሶላት በኋላ የሚባሉ ዚክሮች (ከእያንዳንዱ ሶላት በኋላ)

ከፈርድ ሶላቶች በኋላ ሰላም ከተሰጠ በኋላ የሚባለው ዚክር።

1 አንድ ጊዜ

أَسْتَغْفِرُ اللَّهَ (٣)، اللَّهُمَّ أَنْتَ السَّلَامُ وَمِنْكَ السَّلَامُ، تَبَارَكْتَ يَا ذَا الْجَلَالِ وَالْإِكْرَامِ

ትርጉም እና ምንጭ

ከሠውባን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶላታቸውን ያጠናቀቁ ጊዜ ሶስት ጊዜ ኢስቲግፋር ያደርጉ (ምህረት ይጠይቁ) ነበር። እንዲህም ይሉ ነበር: 'አላሁመ አንተ አስሰላም ወሚንከ አስሰላም ተባረክተ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም' ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ ሰላም የሚገኘውም ካንተ ነው። የግርማና ክብር ባለቤት የሆንከው ጠራህ!) ወሊድ ለአውዛዒይ 'እንዴት ነው ኢስቲግፋር የሚደረገው? አልኩት' አለ። እሳቸውም 'አሰተግፊሩላህ አስተግፊሩላህ' በማለት ነው ብለው መለሱልኝ።' አለ።"

ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶላታቸውን ያጠናቀቁ ጊዜ "አስተግፊሩላህ አስተግፊሩላህ አስተግፊሩላህ" ይሉ ነበር።

ቀጥለውም ጌታቸውን "አላሁመ አንተ አስሰላም ወሚንከ አስሰላም ተባረክተ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም" (አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ ሰላም የሚገኘውም ካንተ ነው። የግርማና ክብር ባለቤት የሆንከው ጠራህ!) በማለት ጌታቸውን ያልቃሉ። አላህ በባህሪያቶቹ የተሟላና ሰላም ነው፤ ከሁሉም ጉድለትና ነውርም የጠራ ነው። ከዱንያና አኺራ ክፋት ሰላም የሚፈለገውም ከሌላ ሳይሆን ከርሱ ነው። እርሱ ጥራት ይገባውና በሁለቱም ዓለም መልካሙ የበዛ ፣ የልቅናና መልካም ባለቤት ነው።

ጥቅሞች

  • ከሶላት በኋላ ኢስቲግፋር ማለትና በርሱ ላይ መዘውተር እንደሚወደድ እንረዳለን።
  • አምልኮ ውስጥ የጎደለውን እንዲሞላ፣ አምልኮ ውስጥ ያሳነስነውን እንዲጠግን ኢስቲግፋር እንደሚወደድ እንረዳለን።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

2 አንድ ጊዜ

لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

ትርጉም እና ምንጭ

የሙጊራ ቢን ሹዕባ ጸሐፊ ከሆነው ወራድ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "ሙጊራ ቢን ሹዕባ ወደ ሙዐዊያህ የሚጻፍን እንዲህ የሚል ደብዳቤ አጻፈኝ: 'ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ እንዲህ ይሉ ነበር ‹ላኢላሀ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር፤ አላሁመ ላማኒዐ ሊማ አዕጦይተ ወላሙዕጢየ ሊማ መነዕተ ወላ የንፈዑ ዘልጀዲ ሚንከልጀድ› ትርጉሙም 'ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ብቸኛና ለርሱ አጋር የሌለው ነው። ንግስናም ምስጋናም ለርሱ ነው። እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነው። አላህ ሆይ! ለሰጠኸው ማንም ከልካይ የለውም። ለከለከልከውም ማንም ሰጪ የለውም። የክብር ባለቤትም ክብሩ ካንተ (ቅጣት) አያድንም።'"

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሁሉም ግዴታ ሶላት በኋላ "ላኢላሀ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር፤ አላሁመ ላማኒዐ ሊማ አዕጦይተ ወላ ሙዕጢየ ሊማ መነዕተ ወላየንፈዑ ዘልጀዲ ሚንከልጀድ" "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ብቸኛና ለርሱ አጋር የሌለው ነው። ንግስናም ምስጋናም ለርሱ ነው። እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነው። አላህ ሆይ! ለሰጠኸው ማንም ከልካይ የለውም። ለከለከልከውም ማንም ሰጪ የለውም። የክብር ባለቤትም ክብሩ ካንተ (ቅጣት) አያድንም።" ይሉ ነበር።

ማለትም: የተውሒድ ቃል በሆነችው "ላኢላሀ ኢለሏህ" አረጋግጣለሁም አምናለሁም። ትክክለኛዋን አምልኮም ለአላህ አፅንቼ ከርሱ ውጪ ካሉ አካላቶችም ውድቅ አደርጋታለሁ። ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም። እውነተኛውና የተሟላው ንግስና፣ የሰማያትና የምድር ባለቤቶችም ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ መሆኑን አረጋግጣለሁ። እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው። አላህ የወሰነው መስጠትም ይሁን መከልከል ማንም መላሽ የለውም። እርሱ ዘንድ የሀብት ባለቤት ሀብቱ አይጠቅመውም። ብቸኛ የሚጠቅመው መልካም ስራ ነው።

ጥቅሞች

  • ይህ ዚክር የተውሒድና የምስጋና ቃላቶችን የሰበሰበ ስለሆነ ከሶላቶች በኋላ ማለቱ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  • ሱናን ወደ መተግበርና ማሰራጨት መቻኮል እንደሚገባ እንረዳለን።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

3 አንድ ጊዜ

لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ، لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلَّا بِاللهِ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، ‌وَلَا ‌نَعْبُدُ ‌إِلَّا إِيَّاهُ، لَهُ النِّعْمَةُ وَلَهُ الْفَضْلُ وَلَهُ الثَّنَاءُ الْحَسَنُ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአቡ ዙበይር እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "ኢብኑ ዙበይር በሁሉም ሶላት ካሰላመተ በኃላ እንዲህ ይሉ ነበር። 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ፤ ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ ፤ ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወላነዕቡዱ ኢላ ኢያህ ለሁ አንኒዕመህ ወለሁልፈድል ወለሁ አሥሠናኡል ሐሰን፤ ላኢላሃ ኢለሏሁ ሙኽሊሲነ ለሁ ዲነ ወለው ከሪሃል ካፊሩን' አስከትለውም እንዲህ አሉ ' የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሁሉም ሶላቶች በኋላ እነዚህን ውዳሴዎች ይሉ ነበር።'"

ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሁሉንም ግዴታ ሶላት ካሰላመቱ በኋላ በዚህ ታላቅ ውዳሴ ያወድሱ ነበር። ትርጉሙም:

"ላኢላሃ ኢለሏህ" ማለትም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም።

"ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ" ማለትም አላህ በተመላኪነቱ፣ በጌትነቱ፣ በስሞቹና በባህሪያቶቹ ለሱ ተጋሪ የለውም።

"ለሁል ሙልክ" ማለትም ገደብ አልባ ሰፊና ጠቅላይ ንግስና የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ንግስና ለሱ ነው።

"ወለሁል ሐምድ" ማለትም ልቅ በሆነ ምሉእነት የሚገለፅ ፣ በደስታም ይሁን በችግር ወቅት በማንኛውም ሁኔታ በውዴታና በልቅና ምሉዕ በመሆኑ የሚመሰገን ነው።

"ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ማለትም ችሎታው በሁሉም መልኩ የሞላ አንዳችም የማይሳነው ማንኛውም ጉዳይ ለሱ የማያቅተው ነው።

"ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ" ማለት በአላህ እገዛ ቢሆን እንጂ ከአንድ ሁኔታ ወደ አንድ ሁኔታ መለወጥ የለም፤ አላህን ከመወንጀል እርሱን ወደማምለክ መለወጥም ሀይልም የለም። እርሱ አጋዥ ነውና፤ መመኪያም በርሱ ላይ ነው።

"ላኢላሃ ኢለሏህ ወላነዕቡዱ ኢላ ኢያህ" "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ከርሱ በስተቀርም አናመልክም።" የሚለው የአላህን ተመላኪነትና ሺርክን ውድቅ የማድረግን ሀሳብ የሚያጠናክር ነው። ከርሱ በስተቀርም አምልኮ የሚገባው የለም።

"ለሁ አንኒዕመህ ወለሁል ፈድል" (ፀጋ የርሱ ነው። ችሮታም የርሱ ነው።) እርሱ የፀጋዎች ባለቤትና የሚፈጥር ነው። ለፈለገው ባሮቹም የሚቸረው እሱ ነው።

"ወለሁ አሥሠናኡል ሐሰን" በሁለመናው፣ በባህሪያቶቹ፣ በድርጊቶቹ፣ በፀጋዎቹ ሁሉ መልካም ውዳሴዎች ለርሱ የተገባ ነው።

"ላኢላሃ ኢለሏህ ሙኽሊሲነ ለሁ ዲን" (አምልኮን ለርሱ ያጠራን ስንሆን ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም።) ማለትም በአላህ አምልኮ ያለምንም ይዩልኝና ይስሙልኝ ብቸኛ ያደረግነው ስንሆን ነው የምናመልከው።

"ከሀዲያን ቢጠሉ እንኳ" ማለትም ከሀዲያን ቢጠሉ እንኳ አላህን በመነጠልና በማምለክ ላይ እንፀናለን።

ጥቅሞች

  • ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ በዚህ ውዳሴ ላይ መዘውተር እንደሚወደድ እንረዳለን።
  • አንድ ሙስሊም ከሀዲያን ቢጠሉ እንኳ በእምነቱ ከፍ ያለ ስሜት ሊሰማውና የእምነቱን መገለጫዎች ይፋ ማድረግ ይገባዋል።
  • ሐዲሥ ውስጥ "ከሶላት በኋላ" የምትለዋ ቃል ስትመጣ ሐዲሡ ውስጥ የተጠቀሰው ውዳሴ ከሆነ ካሰላመተ በኃላ መሆኑ ዱዓእ ከሆነ ደግሞ ሶላት ውስጥ ከማሰላመቱ በፊት መሆኑ መሰረት ነው።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

4 አንድ ጊዜ

سُبْحَانَ اللَّهِ (٣٣)، الْحَمْدُ لِلَّهِ (٣٣)، اللَّهُ أَكْبَرُ (٣٣)، لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: «ከሁሉም (ግዴታ) ሶላት በኋላ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አላህን ያጠራ (ሱብሓነሏህ) ያለ፤ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አላህን ያመሰገነ (አልሐምዱ ሊላህ) ያለ፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ተክቢራ (አላሁ አክበር) ያለ፤ ይህም በድምሩ ዘጠና ዘጠኝ ሲሆን መቶ መሙያውንም "ላኢላሃ ኢለላሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ፣ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ያለ ሰው ወንጀሉ የባህር አረፋ አምሳያ ቢደርስ እንኳ ይማራል።»

ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ግዴታ ሶላቶች ከተጠናቀቁ በኋላ እነዚህን ያለ ሰው የሚያገኘውን ምንዳ ገለፁ:

ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ሱብሓነላህ": ይህም አላህን ከጉድለቶች ሁሉ ማጥራት ነው።

ሰላሳ ሶስት ጊዜ "አልሐምዱ ሊላህ": ይህም አላህን ከመውደድና ከማላቅ ጋር በምሉዕ ባህሪያቱ ማወደስ ነው።

ሰላሳ ሶስት ጊዜ "አላሁ አክበር": ማለት ይህም አላህ ከሁሉም ነገር እጅግ የላቀ ነው ማለት ነው።

መቶ መሙያውንም "ላኢላሃ ኢለላሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ፣ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ያለ ሰው ‐ ትርጉሙም፦ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። ብቸኛና አጋር የለውም። ጥራት የተገባው አላህ በምሉዕ ንግስና የተለየና ከርሱ ውጪ ያሉት የማይገባቸውን ውዳሴና ሙገሳ ከውዴታና ልቅና ጋር የተገባው ነው። እርሱም ምንም የማይሳነው ቻይ ነው።

እነዚህን ቃላት ያለ ሰው ወንጀሉ ባህር በሚናወጥና በሚላተም ሰአት ከላይ በሚሆነው ነጭ አረፋ ልክ ቢበዛ ራሱ ትማራለችም ትሰረዛለችም።

ጥቅሞች

  • ከግዴታ ሶላቶች በኋላ ይህን ዚክር ማለት ተወዳጅ እንደሆነ እንረዳለን።
  • ይህ ዚክር ለወንጀል መማር ምክንያት ነው።
  • የአላህን ትልቁን ችሮታ፣ እዝነትና ምህረት እንረዳለን።
  • ይህ ዚክር ወንጀሎችን ለማስማር ምክንያት ነው። የተፈለገውም: ትናንሽ ወንጀሎችን ማስማር ነው፤ ትላልቅ ወንጀሎች ግን ከተውበት በቀር ምንም አያስምራቸውም።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

5 አንድ ጊዜ

ትርጉም እና ምንጭ

ከከዕብ ቢን ዑጅራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡ "ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ አስከትሎ የሚላቸው ወይም የሚተገበራቸው የማይከስርባቸው ቃላት: ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ተስቢሕ" (ሱብሐነሏህ)፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ተሕሚድ" (አልሐምዱ ሊላህ)፣ ሰላሳ አራት ጊዜ "ተክቢራ" (አላሁ አክበር) ማለት ናቸው።"

ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተናገራቸው የማይከስርበትንና የማይፀፀትበትን ዚክር ተናገሩ። እንደውም በቃላቶቹ ምንዳ የሚያገኝባቸው ናቸው። ከፊሉ ከከፊሉ በኋላ የሚባሉ ሲሆኑ ከግዴታ ሶላት በኋላ ነው የሚባሉት። እነርሱም:

"ሱብሐነላህ"ን ሰላሳ ሶስት ጊዜ ማለት። ማለትም አላህን ከሁሉም ጉድለት ማጥራት ነው።

"አልሐምዱሊላህ"ን ሰላሳ ሶስት ጊዜ ማለት ነው። ይህም አላህን ከመውደድና ከማላቅ ጋር በተሟላ ምሉዕነት መግለፅ ነው።

"አላሁ አክበር"ን ሰላሳ አራት ጊዜ ማለት ነው። አላህ ከሁሉም ነገር ታላቅና የላቀ ነውና።

ጥቅሞች

  • የ"ተስቢሕ"፣ የ"ተሕሚድ"ና የ"ተክቢር"ን ትሩፋት እንረዳለን። እነርሱም ቀሪ የሆኑ መልካም ስራዎች ናቸው።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

6 አንድ ጊዜ

اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ لَا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ مَنْ ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِنْدَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يُحِيطُونَ بِشَيْءٍ مِنْ عِلْمِهِ إِلَّا بِمَا شَاءَ وَسِعَ كُرْسِيُّهُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَلَا يَئُودُهُ حِفْظُهُمَا وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአቡ ኡማማ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ከሁሉም ግዴታ ሶላት በኋላ አየተል ኩርሲይን የቀራ ሰው ጀነት ለመግባት ከሞት በቀር ምንም አይከለክለውም።"»

رواه النسائي في الكبرى ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ግዴታ ሶላት ከተጠናቀቀ በኋላ አየቱል ኩርሲይን የቀራ ሰው ከሞት በቀር ጀነት ለመግባት ምንም እንደማይከለክለው ተናገሩ። ይህቺም አንቀጽ በበቀራ ምእራፍ ውስጥ የምትገኝ ሲሆን እርሷም ይህቺ የአላህ ቃል ናት: ትርጉሟ: {አላህ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው። ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም። በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው። ያ እርሱ ዘንድ በፍቃዱ ቢሆን እንጂ የሚያማልደው ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል። በሻውም ነገር እንጂ ከእውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም። (አያውቁም)። መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ። ጥበቃቸውም አያቅተውም። እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው።} [አልበቀራህ: 255]

ጥቅሞች

  • ይህቺ ታላቅ አንቀፅ የአላህን ውብ ስሞችና የላቁ ባህሪያቱን በማካተቷ ያላትን ትሩፋት እንረዳለን።
  • ይህቺን ታላቅ አንቀፅ ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ መቅራት ተወዳጅ መሆኑን እንረዳለን።
  • መልካም ስራዎች ጀነት ለመግባት ሰበብ እንደሆኑ እንረዳለን።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

7 አንድ ጊዜ

اللَّهُمَّ أَعِنِّي عَلَى ذِكْرِكَ، وَشُكْرِكَ، وَحُسْنِ عِبَادَتِكَ

ትርጉም እና ምንጭ

ከሙዓዝ ቢን ጀበል (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ : «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጄን ያዙኝና እንዲህ አሉኝ: "ሙዓዝ ሆይ! ወላሂ እኔ እወድሃለሁ።" እንዲህም አሉ "ሙዓዝ ሆይ! ከየሁሉም ሶላት መጠናቀቂያ ላይ 'አልላሁመ አዒንኒ ዓላ ዚክሪከ፣ ወሹክሪከ፣ ወሑስኒ ዒባደቲክ' ማለትን እንዳትተው አደራ እልሃለሁ።" አሉኝ።» ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ በማመስገንና አምልኮህን በማሳመር ላይ አግዘኝ።) ማለት ነው።

رواه أبو داود والنسائي وأحمد ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሙዓዝን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እጅ ያዙና ለርሱ እንዲህ አሉት: በአላህ እምልልሃለሁ እኔ እወድሃለሁ። ሙዓዝ ሆይ! በየሁሉም ሶላት መጨረሻ ላይ ይህን ማለት እንዳትተው አደራ እልሃለሁ። "አሏሁመ አዒኒ ዐላ ዚክሪከ" (አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት አግዘኝ) ወደ አምልኮ የሚያቃርበኝ በሆነ ንግግርና ተግባር ሁሉ አግዘኝ። "ወሹክሪከ" ፀጋን በማግኘትና መከራን በማስወገድም (አንተን ለማመስገን) አግዘኝ። ለአላህ ስራን በማጥራትና ነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመከተል (አምልኮህን በማሳመርም) አግዘኝ።

ጥቅሞች

  • ሰውን ለአላህ ብለን እንደምንወደው መንገር የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።
  • በየሁሉም ግዴታና ሱንና ሶላቶች መጨረሻ ላይ ይህን ዱዓ ማድረግ መወደዱን እንረዳለን።
  • በነዚህ ጥቂት የዱዓ ቃላት ውስጥ ዱንያዊም አኺራዊም ፍላጎቶች አሉ።
  • ለአላህ ብሎ ከመውደድ ጥቅሞች መካከል በእውነት ላይ አደራ መባባል፣ መመካከር፣ በበጎና አላህን በመፍራት ላይ መተጋገዝ ይገኛሉ።
  • ጢቢይ እንዲህ ብለዋል: "አላህን ማውሳት የልብ መስፋት መግቢያ ነው። አላህን ማመስገን ደግሞ ተቀባይነት ላለው ፀጋ የሚያዳርስ ነው። አምልኮን ከማሳመር ተፈላጊው ጉዳይ ከአላህ ከሚያዘናጉ ነገሮች መለያየቱ ነው።"

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

ጥያቄዎች

በዚህ ገጽ ላይ ምን አለ?

ከሶላት በኋላ ዚክር: እያንዳንዳቸው በዐረብኛ፣ ከትርጉማቸው፣ ከመጡበት ሐዲስ፣ ከደረጃቸው እና ከማብራሪያ ጋር።

ትርጉሞቹ ከየት ናቸው?

ከHadeethEnc.com፣ የተተረጎሙ የነቢዩ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ። እያንዳንዱ ሐዲስ እነሱ እንዳሳተሙት፣ ከምንጩ እና ከደረጃው ጋር እንዲሁም ወደ ዋናው የሚወስድ ማስፈንጠሪያ ይዞ ይቀርባል።

የዕለት ማስታወሻ ማግኘት እችላለሁ?

አዎ። ለAndroid የሆነው ነፃው የQabas መተግበሪያ የጠዋት እና የማታ ዚክርን በየቀኑ ያስታውስዎታል፣ ተመሳሳይ ቆጣሪም አለው።