ሱራ Ad-Duha الضحى

ትርጉም: Amharic Translation - Muhammad Sadiq

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

وَٱلضُّحَىٰ ١

በረፋዱ እምላለሁ፡፡

وَٱلَّيۡلِ إِذَا سَجَىٰ ٢

በሌሊቱም ጸጥ ባለ ጊዜ፤

مَا وَدَّعَكَ رَبُّكَ وَمَا قَلَىٰ ٣

ጌታህ አላሰናበተህም፤ አልጠላህምም፡፡

وَلَلۡأٓخِرَةُ خَيۡرٞ لَّكَ مِنَ ٱلۡأُولَىٰ ٤

መጨረሻይቱም (ዓለም) ከመጀመሪያይቱ ይልቅ ላንተ በላጭ ናት፡፡

وَلَسَوۡفَ يُعۡطِيكَ رَبُّكَ فَتَرۡضَىٰٓ ٥

ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡

أَلَمۡ يَجِدۡكَ يَتِيمٗا فَـَٔاوَىٰ ٦

የቲም ኾነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)፡፡

وَوَجَدَكَ ضَآلّٗا فَهَدَىٰ ٧

የሳትክም ኾነህ አገኘህ መራህም፡፡

وَوَجَدَكَ عَآئِلٗا فَأَغۡنَىٰ ٨

ድኻም ኾነህ አገኘህ፤ አከበረህም፡፡

فَأَمَّا ٱلۡيَتِيمَ فَلَا تَقۡهَرۡ ٩

የቲምንማ አትጨቁን፡፡

وَأَمَّا ٱلسَّآئِلَ فَلَا تَنۡهَرۡ ١٠

ለማኝንም አትገላምጥ፡፡

وَأَمَّا بِنِعۡمَةِ رَبِّكَ فَحَدِّثۡ ١١

በጌታህም ጸጋ አውራ፤ (ግለጻት)፡፡

ጥያቄዎች

ሱራ Ad-Duha ስንት አንቀጾች አሉት?

ሱራ Ad-Duha 11 አንቀጾች አሉት። በቁርኣን ውስጥ ሱራ ቁጥር 93 ነው።

ሱራ Ad-Duha የመካ ነው ወይስ የመዲና?

ሱራ Ad-Duha የመካ ሱራ ነው።

ሱራ Ad-Duha በየትኛው ጁዝ ውስጥ ነው?

ሱራ Ad-Duha በጁዝ 30 ውስጥ ነው።

ሱራ Ad-Duha ማዳመጥ እችላለሁ?

አዎ። በዚህ ገጽ አናት ላይ አጫውትን ይጫኑ፣ ወይም ከማንኛውም አንቀጽ ይጀምሩ። የQabas መተግበሪያም ያለ ኢንተርኔት ለማዳመጥ እንዲያወርዱት ያስችልዎታል።