ሰለዋት: በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድ

በነቢዩ ﷺ ላይ እንዴት ሰለዋት እንደሚወርድ እና ምንዳው።

1 አንድ ጊዜ

اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ

ትርጉም እና ምንጭ

ከዐብዱረሕማን ቢን አቢ ለይላ እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ከዕብ ቢን ዑጅራህ አገኘኝና እንዲህ አለኝ: 'ስጦታ ላበርክትልህን? ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደኛ መጡ። እኛም እንዲህ ብለን ጠየቅናቸው የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርሶ ላይ እንዴት ሰላምታ እንደምናቀርብ አውቀናል። በርሶ ላይ ሶላት የምናወርደውስ እንዴት ነው? እርሳቸውም፦ ‹አልላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊ ሙሐመዲን ከማ ሶለይተ ዓላ አሊ ኢብራሂመ ኢነከ ሐሚዱን መጂድ፤ አልላሁመ ባሪክ ዓላ ሙሐመዲን ወዓላ አሊ ሙሐመዲን ከማ ባረክተ ዓላ አሊ ኢብራሂመ ኢነከ ሐሚዱን መጂድ። በሉ› አሉን።'" (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ውዳሴህን ለኢብራሂምና ለቤተሰቦቻቸው እንዳወረድክላቸው ሁሉ ለሙሐመድና ለቤተሰቦቻቸው አውርድላቸው፤ አንተ ምስጉንና ኋያል (የላቅክ) ነህና፡፡አላህ ሆይ! ለኢብራሂምና ለቤተሰቦቻቸው ረድዔትን እንዳወረድክላቸው ሁሉ ለሙሐመድና ለቤተሰቦቻቸውም ረድዔትን አውርድላቸው፡፡ አንተ ምስጉንና ኋያል (የላቅክ) ነህና፡፡”)

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ሶሐቦች አትተሒያቱ ላይ "አስሰላሙ ዐለይከ አይዩሀ ነቢዩ ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱሁ… " በማለት በነቢዩ ላይ እንዴት ሰላምታ እንደሚቀርብ ካወቁ በኋላ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በርሳቸው ላይ ሶላት እንዴት እንደሚደረግ ጠየቁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በርሳቸው ላይ እንዴት ሶላት እንደሚያወርዱ ነገሯቸው። ትርጉሙም: "አልላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመዲን ወዓላ አሊ ሙሐመድ" ማለትም: አላህ ሆይ! በላይኛው አለም፤ በርሳቸው፣ እምነታቸውን በተከተሉና አማኝ በሆኑ ቅርብ ዘመዶቻቸውም ላይ በመልካም ትውስታ አወድሳቸው። "ከማ ሶለይተ ዓላ አሊ ኢብራሂም" በኢብራሂም (ዐለይሂ ሰላም) የአላህ ሰላም ይስፈንባቸውና ቤተሰቦች ‐ እነሱም ኢብራሂም፣ ኢስማዒል፣ ኢስሐቅ፣ ዝርያዎቻቸውና አማኝ ተከታዮቻቸው ‐ ላይ ችሮታህን እንደዋልከው በሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይም ችሮታህን ዋል። "ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ" ማለትም: በዛትህ፣ በባህሪትህ እና በድርጊቶችህ ምስጉን የሆንክ፤ በልቅናህ፣ በስልጣንህና በስጦታህ ሰፊ የሆንክ አንተው ነህ ማለት ነው። "አልላሁመ ባሪክ ዐላ ሙሐመዲን ወዓላ አሊ መሐመድ ከማ ባረክተ ዓላ አሊ ኢብራሂም" ማለትም ለነቢዩ ከመልካሙና ከክብር የላቀውን ስጣቸው፣ ጨምርላቸውም፣ አፅናላቸውም።

ጥቅሞች

  • ቀደምት አበው እውቀታዊ ቁምነገሮችን እንደ ስጦታ ይሰጣጡ እንደነበር እንረዳለን።
  • ሶላት ላይ በመጨረሻው ተሸሁድ ወቅት በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ ሶላት ማውረድ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  • ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባልደረቦቻቸውን በርሳቸው ላይ እንዴት ሶላትና ሰላም እንደሚያወርዱ ማስተማራቸውን እንረዳለን።
  • ይህ የሶለዋት ይዘት በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ የተሟላው የሶለዋት ይዘት ነው።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

2 አንድ ጊዜ

ትርጉም እና ምንጭ

ከሑሰይን ቢን ዐሊይ ቢን አቢጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ስስታም ማለት እርሱ ዘንድ ተወስቼ በኔ ላይ ሶላት ያላወረደ ነው።"»

رواه الترمذي والنسائي في الكبرى وأحمد ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የርሳቸውን ስም ወይም ቅጥያ ስም ወይም ባህሪያቸውን በሚሰማ ወቅት እርሳቸው ላይ ሶላት ማውረድ የተወን ሰው አስጠነቀቁ። እንዲህም አሉ: ስስታምነቱ የተሟላ ስስታም ማለት እርሱ ዘንድ ተወስቼ ሶለዋት ያላወረደብኝ ነው። ይህም የሆነው ከሚከተሉት ጉዳዮች አንፃር ነው:

የመጀመሪያው: ሶለዋት በማውረዱ ምክንያት ትንሽም ይሁን ብዙ የማይከስርበት፣ ገንዘብ የማያወጣበት፣ ጉልበቱን የማያፈስበት በሆነ ነገር ላይ መሰሰት ስለሆነ፤

ሁለተኛው: በአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ሶለዋት ባለማውረዱ በርሳቸው ላይ ሶላት የማውረድን ምንዳ በነፍሱ ላይ ስለሳሳና ስለነፈጋት ነው። በርሳቸው ላይ ሶለዋት ባለማውረዱ ትእዛዝን ለመተግበርና ምንዳን ለማግኘት ሊፈፅመው ግዴታ የሆነበትን ሐቅ ከመፈፀም ታቅቧልም ሰስቷልም።

ሶስተኛው: በርሳቸው ላይ ሶለዋት ማውረድ የተወሰነውን የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሐቅ መወጣት ነው። ያስተማሩን፣ ያቀኑን፣ ወደ አላህ ተባረከ ወተዓላ የጠሩን፣ ይህንን ወሕይና ሸሪዓ ይዘው የመጡልን እርሳቸው ናቸው። ከአላህ ተባረከ ወተዓላ በኋላ የመመራታችን ምክንያት እርሳቸው ናቸው። በርሳቸው ላይ ሶለዋት ያላወረደ ሰው በርግጥም በነፍሱ ላይም ስስታም ሆኗል። ለነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ካላቸው ሐቆች መካከል በትንሹ ሐቅ እንኳ ስስታም ሆኗል።

ጥቅሞች

  • በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ሶለዋት ማውረድን መተው የስስታምነት ቁንጮ ነው።
  • በማንኛውም ወቅት በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ሶለዋት ማውረድ በላጭ ከሆኑ አምልኮዎችና መቃረቢያዎች መካከል ነው። እርሳቸው በሚወሱበት ወቅት ደሞ በላጭነቱ ጠንከር ይላል።
  • ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ሶለዋት ሲያወርድ ሶለዋትና ሰላምን ሰብስቦ ይበል። በአንዱ ላይ ብቻ አይቆጠብ። (ሶለላሁ ዐለይሂ) ብቻ ወይም (ዐለይሂ ሰላም) ብቻ አይበል።»
  • {አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ ሶላትን ያወርዳሉ።} በሚለው የአላህ ቃል ዙሪያ አቡል ዐሊያህ እንዲህ ብለዋል: «አላህ በነቢዩ ላይ ሶለዋት አወረደ ማለት እርሳቸውን ማወደሱ ነው። ሶለዋት ከመላእክትና ከሰው ሲሆን ደግሞ ዱዓእ ነው።»
  • ሐሊሚይ እንዲህ ብለዋል: (አላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመድ) የሚለው ትርጉም አላህ ሆይ! በዱንያ መወሳታቸውን ከፍ በማድረግ፣ ሃይማኖታቸውን የበላይ በማድረግ፣ ሸሪዓቸውን ዘውታሪ በማድረግ አላቃቸው። በመጪው አለም ደግሞ ለኡመታቸው አማላጅ በማድረግ፣ ምንዳቸውንና አጅራቸውን በማተለቅ፣ ለመጀመሪያውም ሆነ ለመጨረሻው ፍጡር በምስጉኑ ስፍራ ደረጃቸውን በመግለፅ፣ አላህ ፊት ምስክር ከሆኑ ቅርቦች ባጠቃላይ በማስቀደም አላቃቸው ማለት ነው።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

3 አንድ ጊዜ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "እርሱ ዘንድ ስሜ ተወስቶ በኔ ላይ ሶላት ያላወረደ ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ፤ ረመዷንን አግኝቶ ከዚያም ከመማሩ በፊት የወጣበት ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ፤ ወላጆቹን እርጅና ላይ አግኝቶ ጀነት ያላስገቡት ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ።"

ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶስት አይነት ሰዎችን በውርደትና ክስረት አፍንጫቸው በአፈር እንዲታሽ ረገሟቸው: የመጀመሪያው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እርሱ ዘንድ ተወስተው በርሳቸው ላይ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ወይም እርሱን የመሰለ ውዳሴ በማለት በርሳቸው ላይ ሶላት ያላወረደ ሰው ነው። ሁለተኛው: የረመዷንን ወር አግኝቶ ከዚያም አምልኮን በአግባቡ ባለመፈፀሙ ምክንያት ከመማሩ በፊት ወሩ የተጠናቀቀበት ሰው ነው። ሶስተኛው: በእርጅና ወቅት ወላጆቹን አግኝቶ የነርሱን ሐቅ ባለመወጣቱና ሐቃቸውን በማጓደሉ ምክንያት ጀነት ለመግባቱ ሰበብ ያልሆኑለት ሰው ነው።

ጥቅሞች

  • ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "ዋናው ፍሬ ሃሳብ እያንዳንዱ እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሱት አካላት እድሉን ቢጠቀምበት ኖሮ ትልቅ መልካም የሆነን እድል የሚያገኝበት ነገር ነበረው። እድሉን በሚያመልጠው ልክ ማጓደሉ ግን ለክስረትና ለውርደት ዳረገው።"
  • የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ስም በተወሳ ቁጥር በርሳቸው ላይ ሶላት በማውረድ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • በረመዷን ወር ለአምልኮ በመዘጋጀትና በመታገል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • ለወላጆች በጎ በማድረግና በመንከባከብ መታገል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። በተለይ ባረጁ ወቅት የበለጠ መታገል ተገቢ ነው።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

ጥያቄዎች

በዚህ ገጽ ላይ ምን አለ?

በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋት: እያንዳንዳቸው በዐረብኛ፣ ከትርጉማቸው፣ ከመጡበት ሐዲስ፣ ከደረጃቸው እና ከማብራሪያ ጋር።

ትርጉሞቹ ከየት ናቸው?

ከHadeethEnc.com፣ የተተረጎሙ የነቢዩ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ። እያንዳንዱ ሐዲስ እነሱ እንዳሳተሙት፣ ከምንጩ እና ከደረጃው ጋር እንዲሁም ወደ ዋናው የሚወስድ ማስፈንጠሪያ ይዞ ይቀርባል።

የዕለት ማስታወሻ ማግኘት እችላለሁ?

አዎ። ለAndroid የሆነው ነፃው የQabas መተግበሪያ የጠዋት እና የማታ ዚክርን በየቀኑ ያስታውስዎታል፣ ተመሳሳይ ቆጣሪም አለው።