ለጭንቀት፣ ለስጋት እና ለሐዘን ዱዓ

ነቢዩ ﷺ በችግር ጊዜ ያደረጓቸው እና ለጭንቀትና ለሐዘን ያስተማሯቸው ዱዓዎች።

1 አንድ ጊዜ

لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ الْعَظِيمُ الْحَلِيمُ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ رَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَرَبُّ الْأَرْضِ وَرَبُّ الْعَرْشِ الْكَرِيمِ

ትርጉም እና ምንጭ

ከኢብኑ ዓባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በችግር ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር "ላኢላሃ ኢለሏህ አልዐዚሙል ሐሊም፣ ላኢላሃ ኢለሏሁ ረቡል ዐርሺል ዐዚም፣ ላኢላሃ ኢለሏሁ ረቡስ-ሰማዋቲ ወረቡል አርዲ ወረቡል ዐርሺል ከሪም" (ትርጉሙም፡ "ከታላቁና ቻይ ከሆነው አላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ከታላቁ ዐርሽ ጌታ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ከሰማያት ጌታ፣ ከምድር ጌታ፣ ከተከበረው ዐርሽ ጌታ አላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም።" ማለት ነው።)

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ችግርና ጭንቀት በርሳቸው ላይ በሚበረታ ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር፡ "ላኢላሃ ኢለሏህ" ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። "ታላቅ በሆነው" ክብሩ፣ በማንነቱ፣ በባህሪውና በድርጊቱ ነገሩ የላቀ፤ "ቻይ" ወንጀለኛን በመቅጣት የማይቸኩል ይልቁንም የሚያዘገይ፤ መቅጣት እየቻለ ይቅር የሚል፤ በሁሉም ነገር ላይም ቻይ የሆነ ነው። "ከታላቁ ዐርሽ ጌታ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም።" የታላቁ ዐርሽ ፈጣሪ ነው። "የሰማያትና የምድር ጌታ ከሆነው አላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም።" የሰማያትና ምድር ፈጣሪ፤ በውስጣቸው ያለውን ነገር ሁሉ የፈጠረ፤ ባለቤቱ፣ አስተካካዩና እንደፈለገው የሚያስተናብረው ነው። "የተከበረው ዐርሽ ጌታ" የተከበረውን ዐርሽ የፈጠረ ነው።

ጥቅሞች

  • መከራና ችግር ሲያጋጥም በዱዓ ወደ አላህ መዋደቅ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  • በችግር ወቅት በዚህ ዚክር ዱዓ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  • የበላይ የሆነው አላህ በላዩ ላይ ከፍ ያለበት የአርረሕማን ዐርሽ ከፍጡራን ባጠቃላይ ከፍ ያለ፤ ትልቁና ግዙፉ ፍጡር ነው። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እርሱ ትልቅና የተከበረ መሆኑን ገልፀዋል።
  • ሰማይና ምድር ተለይተው የተጠቀሱበት ምክንያት ከሚታዩ ፍጡሮች ባጠቃላይ ትላልቆቹ ስለሆኑ ነው።
  • ጢቢይ እንዲህ ብለዋል: "ይህንን ውዳሴ አላህን በጌትነቱ አውስተው የጀመሩት ችግሩ እንዲወገድ ተስማሚው ስም ስለሆነ ነው። የጌታነት ማንነቱ ችግርን ማስወገድ ያስፈርዳልና። እዚህ ውዳሴ ውስጥ ተውሒድን ያካተተችው፣ የበላይነቱን (ግርማውን) የማጥሪያ መሰረት የሆነችው ላኢላሃ ኢለሏህም አለች፤ የችሎታውን ምሉዕነት የምትገልፀው ልቅናውን ታመላክታለች፤ "አልሒልም" ዕውቀቱን የምትጠቁመው ቻይነቱን (እያወቀና እየቻለም አለመቅጣቱ) ትገልፃለች። ምክንያቱም የማያውቅ አካል ቻይነት "ሒልም" እና ቸርነት አለው ተብሎ አይታሰብምና። እነዚህ ሁለቱ ባህሪያት ደሞ የመከበሪያ ባህሪያቶች መሰረት ናቸው።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

2 አንድ ጊዜ

اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنْ غَلَبَةِ الدَّيْنِ، وَغَلَبَةِ الْعَدُوِّ، وَشَمَاتَةِ الْأَعْدَاءِ

ትርጉም እና ምንጭ

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በነዚህ ቃላቶች ዱዓ ያደርጉ ነበር: "አላህ ሆይ! እኔ በእዳ ከመሸነፍ፣ በጠላት ከመሸነፍና የጠላቶች ደስታ ምንጭ ከመሆን ባንተ እጠበቃለሁ።"

ነሳኢና አሕመድ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከነዚህ ጉዳዮች ጥበቃን ፈለጉ:

የመጀመሪያው: (አላህ ሆይ! እኔ በአንተ እጠበቃለሁ) በሌላ በማንም ሳይሆን (በእዳ ከመሸነፍ) ከእዳ ጭንቀት፣ ችግር፤ እዳውን በመክፈልና በመዝጋት ያንተን እገዛ እጠይቅሃለሁ።

ሁለተኛው: (በጠላት ከመሸነፍ) በኔ ላይ ጠላት የበላይ ከመሆንብኝና ከሚቆጣጠረኝ፤ የርሱን ጉዳት መከላከልና በርሱ ላይ ድል መቀናጀትን እጠይቅሃለሁ።

ሶስተኛው: (የጠላቶች የደስታ ምንጭ ከመሆን) ሙስሊሞችን በሚያገኛቸው መከራና ችግር ደስተኛ ከመሆናቸው በአንተ እጠበቃለሁ ማለት ነው።

ጥቅሞች

  • ከእዳና ከመሳሰሉት ከአምልኮ ከሚያጠምዱና ጭንቀትን ከሚያመጡ ነገሮች ሁሉ በአላህ በመጠበቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • ዕዳ በጥቅሉ ችግር የለውም። ችግር ያለው እዳ መክፈያ በሌለው ሰው ላይ ነው። በእዳ የሚሸነፈውም ይህ ነው።
  • የሰው ልጅ ጠላትን የሚያስደስትበትንና የሚነወርበትን ነገሮች መራቅ ይገባዋል።
  • ከሀዲዎች ለአማኞች ያላቸውን ጠላትነትና አማኞች ላይ መከራ መድረሱ የደስታቸው ምንጭ መሆኑ መገለፁን እንረዳለን።
  • የሰው ልጅ ከደረሰበት መከራ የበለጠ ጠላቶች በመከራው መደሰታቸውን ግልፅ ማድረጋቸው የበለጠ ይጎዳል።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

ጥያቄዎች

በዚህ ገጽ ላይ ምን አለ?

የጭንቀት ዱዓ: እያንዳንዳቸው በዐረብኛ፣ ከትርጉማቸው፣ ከመጡበት ሐዲስ፣ ከደረጃቸው እና ከማብራሪያ ጋር።

ትርጉሞቹ ከየት ናቸው?

ከHadeethEnc.com፣ የተተረጎሙ የነቢዩ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ። እያንዳንዱ ሐዲስ እነሱ እንዳሳተሙት፣ ከምንጩ እና ከደረጃው ጋር እንዲሁም ወደ ዋናው የሚወስድ ማስፈንጠሪያ ይዞ ይቀርባል።

የዕለት ማስታወሻ ማግኘት እችላለሁ?

አዎ። ለAndroid የሆነው ነፃው የQabas መተግበሪያ የጠዋት እና የማታ ዚክርን በየቀኑ ያስታውስዎታል፣ ተመሳሳይ ቆጣሪም አለው።