ዕዳ ለመክፈል ዱዓ

ከዕዳ ለመገላገል እና ለሐላል ሲሳይ ዱዓዎች።

1 አንድ ጊዜ

اللَّهُمَّ اكْفِنِي بِحَلاَلِكَ عَنْ حَرَامِكَ، وَأَغْنِنِي بِفَضْلِكَ عَمَّنْ سِوَاكَ

ትርጉም እና ምንጭ

ከዓሊይ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «አንድ ነፍሱን ገንዘብ ከፍሎ ነፃ ለማውጣት ከአለቃው ጋር የተዋዋለ ባሪያ ወደርሱ መጣና እንዲህ አለው: "እኔ ነፍሴን ከፍዬ ነፃ የማወጣበት ገንዘብ ስላቃተኝ አግዘኝ።" ዐሊይም እንዲህ አለ: "በአንተ ላይ የሲር ተራራን የሚያህል እዳ ቢኖርብህ እንኳ አላህ እንዲከፍልልህ የሚያደርግን የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ያስተማሩኝን ቃላቶች ላስተምርህን?" እንዲህ ብለዋል: ‹እንዲህ በል: አልላሁመክፊኒ ቢሐላሊከ ዐን ሐራሚክ፤ ወአግኒኒ ቢፈድሊከ ዓመን ሲዋክ›"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! በሐላልህ ከሐራምህ ጠብቀኝ፤ በችሮታህም ከአንተ ውጪ ካሉ አብቃቃኝ።" ማለት ነው።

ቲርሚዚ ዘግበውታል። ደረጃ: ሐሰን ነው።

ማብራሪያ

አንድ ከአለቃው ጋር ነፍሱን ለመግዛትና ነፃ ሊያወጣት ተስማምቶ የተፃፃፈ ነገር ግን ገንዘብ የሌለው ባሪያ ወደ አማኞች አዛዥ ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - መጣና እንዲህ አለ: "እኔ ያለብኝን ገንዘብ መክፈል አቅቶኛልና ገንዘቡን በመክፈል ላይ ወይም መፍትሄ የሚሆነኝን በማስተማርና በመጠቆም ላይ አግዘኝ።" የአማኞች አዛዥም እንዲህ አለው: "ጦይእ አካባቢ ውስጥ የሚገኘው የሲር ተራራን የሚያህል እዳ ቢኖርብህ እንኳ አላህ እዳህን ለሚገባው አካል በመክፈል ከመዋረድ እንድትድን የሚያደርግን የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ያስተማሩኝን ቃላቶች ላስተምርህን?" ቀጥሎ እንዲህ አለው: "እንዲህ በል (አልላሁመ ክፊኒ) አላህ ሆይ አርቀኝ፣ አዙረኝ (ቢሐላሊከ) በሐላልህ ተብቃቅቼ (ዐንሐራሚክ) ክልክልህ ላይ ከመውደቅ (ወአግኒኒ) አብቃቃኝ (ቢፈድሊከ) በቸርነትህ (ዐመንሲዋክ) ከአንተ ውጪ ካሉ ፍጡራን።

ጥቅሞች

  • ለጉዳያችን የእውቀትና የዲን ባለቤቶችን ሀሳባቸውን መጠየቅና ማማከር እንደሚገባ እንረዳለን።
  • የእውቀት ባለቤቶችና ወደ አላህ የሚጣሩ ዱዓቶች ምክራቸውን ለሚሰሙ ሰዎች በሚያጋጥማቸው ችግሮች መፍትሄ መጠቆምና ማቅናት ይገባቸዋል።
  • ነፍሱን ነፃ ለማውጣት የተፃፃፈን ባሪያ በማገዝ ላይ መነሳሳቱን ተመልክተናል።
  • ይህን ዱዓ በመማርና አላህን በዚህ ዱዓ በመጠየቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • ሐላል የሆነ ሪዝቅ ቢያንስ እንኳ ከብዙ የሐራም ገንዘብ የተሻለ ነው።
  • ከፍጡራን በአላህ መብቃቃት እንደሚገባ እንረዳለን።
  • ለጠያቂ የምትሰጠው የሌለህ ጊዜ መልካም መልስ በመመለስ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

2 አንድ ጊዜ

اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنْ غَلَبَةِ الدَّيْنِ، وَغَلَبَةِ الْعَدُوِّ، وَشَمَاتَةِ الْأَعْدَاءِ

ትርጉም እና ምንጭ

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በነዚህ ቃላቶች ዱዓ ያደርጉ ነበር: "አላህ ሆይ! እኔ በእዳ ከመሸነፍ፣ በጠላት ከመሸነፍና የጠላቶች ደስታ ምንጭ ከመሆን ባንተ እጠበቃለሁ።"

ነሳኢና አሕመድ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከነዚህ ጉዳዮች ጥበቃን ፈለጉ:

የመጀመሪያው: (አላህ ሆይ! እኔ በአንተ እጠበቃለሁ) በሌላ በማንም ሳይሆን (በእዳ ከመሸነፍ) ከእዳ ጭንቀት፣ ችግር፤ እዳውን በመክፈልና በመዝጋት ያንተን እገዛ እጠይቅሃለሁ።

ሁለተኛው: (በጠላት ከመሸነፍ) በኔ ላይ ጠላት የበላይ ከመሆንብኝና ከሚቆጣጠረኝ፤ የርሱን ጉዳት መከላከልና በርሱ ላይ ድል መቀናጀትን እጠይቅሃለሁ።

ሶስተኛው: (የጠላቶች የደስታ ምንጭ ከመሆን) ሙስሊሞችን በሚያገኛቸው መከራና ችግር ደስተኛ ከመሆናቸው በአንተ እጠበቃለሁ ማለት ነው።

ጥቅሞች

  • ከእዳና ከመሳሰሉት ከአምልኮ ከሚያጠምዱና ጭንቀትን ከሚያመጡ ነገሮች ሁሉ በአላህ በመጠበቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • ዕዳ በጥቅሉ ችግር የለውም። ችግር ያለው እዳ መክፈያ በሌለው ሰው ላይ ነው። በእዳ የሚሸነፈውም ይህ ነው።
  • የሰው ልጅ ጠላትን የሚያስደስትበትንና የሚነወርበትን ነገሮች መራቅ ይገባዋል።
  • ከሀዲዎች ለአማኞች ያላቸውን ጠላትነትና አማኞች ላይ መከራ መድረሱ የደስታቸው ምንጭ መሆኑ መገለፁን እንረዳለን።
  • የሰው ልጅ ከደረሰበት መከራ የበለጠ ጠላቶች በመከራው መደሰታቸውን ግልፅ ማድረጋቸው የበለጠ ይጎዳል።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

ጥያቄዎች

በዚህ ገጽ ላይ ምን አለ?

የዕዳ ዱዓ: እያንዳንዳቸው በዐረብኛ፣ ከትርጉማቸው፣ ከመጡበት ሐዲስ፣ ከደረጃቸው እና ከማብራሪያ ጋር።

ትርጉሞቹ ከየት ናቸው?

ከHadeethEnc.com፣ የተተረጎሙ የነቢዩ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ። እያንዳንዱ ሐዲስ እነሱ እንዳሳተሙት፣ ከምንጩ እና ከደረጃው ጋር እንዲሁም ወደ ዋናው የሚወስድ ማስፈንጠሪያ ይዞ ይቀርባል።

የዕለት ማስታወሻ ማግኘት እችላለሁ?

አዎ። ለAndroid የሆነው ነፃው የQabas መተግበሪያ የጠዋት እና የማታ ዚክርን በየቀኑ ያስታውስዎታል፣ ተመሳሳይ ቆጣሪም አለው።