በመከራ እና በማጣት ጊዜ ዱዓ (ኢና ሊላሂ)

አንድ ነገር ሲያጡ ወይም መከራ ሲደርስ የሚባለው እና ለሐዘንተኞች የማጽናኛ ቃላት።

1 አንድ ጊዜ

إِنَّا لِلهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ، اللَّهُمَّ أْجُرْنِي فِي مُصِيبَتِي، وَأَخْلِفْ لِي خَيْرًا مِنْهَا

ትርጉም እና ምንጭ

ከአማኞች እናት ከኡሙ ሰለማ ረዺየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "አንድም መከራ አጋጥሞት አላህ እንዳዘዘው ‹{ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን} [አልበቀራ:156] አልላሁመእጁርኒ ፊ ሙሲበቲ፣ ወአኽሊፍ ሊ ኸይረን ሚንሃ› የሚል ሙስሊም የለም አላህ ከዛ የተሻለ ነገር ቢተካለት እንጂ።"» ኡሙ ሰለማ እንዲህ አለች: "አቡ ሰለማ የሞተ ጊዜ እንዲህ አልኩኝ: ከአቡ ሰለማ የተሻለ ሙስሊም ከቶ ማን አለና?! ወደ አላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በቅድሚያ የተሰደደ ቤተሰብ ነው። ከዚያም ይህንን ዱዓ አልኩኝ። አላህም ለኔ የአላህን መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ተካልኝ።" ትርጉሙም ({እኛ ለአላህ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን።} [አልበቀራ:156] አላህ ሆይ በመከራዬ ምንዳን ስጠኝ። ከደረሰበኝ መከራ የተሻለንም ተካልኝ።) ማለት ነው።

ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

የአማኞች እናት ኡሙ ሰለማ ረዲየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - አንድ ጊዜ ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ እንደሰማች አወሳች: አንድም መከራ የሚደርስበትና አላህ ለርሱ የመረጠለትን ይህንን ውዳሴ የሚል ሙስሊም የለም: {ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን} [አልበቀራ:156] ትርጉሙም {እኛ ለአላህ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን።} (አላሁመእጁርኒ) አላህ ሆይ! በደረሰበኝ መከራ የትእግስቴን ምንዳ ስጠኝ! (ፊ ሙሲበቲ) (ወአኽሊፍ ሊ ኸይረን ሚንሃ) ከርሱ የተሻለንም ለኔ ተካልኝ አይልም አላህ ለርሱ ከደረሰበት መከራ የተሻለን ቢለውጥለት እንጂ። ኡሙ ሰለማ እንዲህ አለች: አቡ ሰለማ የሞተ ጊዜ እንዲህ አልኩኝ: "ከአቡ ሰለማ የተሻለ ሙስሊም ከቶ ማን አለ? ወደ አላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በቅድሚያ የተሰደደ ቤተሰብ ነው። ከዚያም ግን አላህ አግዞኝ ይህንን ውዳሴ ተናገርኩት። አላህም ለኔ ከአቡ ሰለማ የተሻሉትን የአላህን መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ተካልኝ።"

ጥቅሞች

  • መከራ በሚያጋጥም ወቅት ባለመበሰጫጨትና ትእግስት በማድረግ መታዘዙን እንረዳለን።
  • መከራ በሚያጋጥም ወቅት አላህ ዘንድ ምትኩ ስላለ ዱዓእ በማድረግ ወደ አላህ መዞር እንደሚገባ እንረዳለን።
  • አንድ አማኝ የነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ትእዛዝ ጥበቡ ባይታየው እንኳ የርሳቸውን ትእዛዝ መፈፀም አስፈላጊነቱን እንረዳለን።
  • የተሟላ መልካም የሚባለው አንድ አማኝ የነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ትእዛዝ ሲተገብር ነው።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

ጥያቄዎች

በዚህ ገጽ ላይ ምን አለ?

የመከራ ዱዓ: እያንዳንዳቸው በዐረብኛ፣ ከትርጉማቸው፣ ከመጡበት ሐዲስ፣ ከደረጃቸው እና ከማብራሪያ ጋር።

ትርጉሞቹ ከየት ናቸው?

ከHadeethEnc.com፣ የተተረጎሙ የነቢዩ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ። እያንዳንዱ ሐዲስ እነሱ እንዳሳተሙት፣ ከምንጩ እና ከደረጃው ጋር እንዲሁም ወደ ዋናው የሚወስድ ማስፈንጠሪያ ይዞ ይቀርባል።

የዕለት ማስታወሻ ማግኘት እችላለሁ?

አዎ። ለAndroid የሆነው ነፃው የQabas መተግበሪያ የጠዋት እና የማታ ዚክርን በየቀኑ ያስታውስዎታል፣ ተመሳሳይ ቆጣሪም አለው።