በአላህ የመጠበቅ ዱዓዎች

ነቢዩ ﷺ ከአላህ ጥበቃ የፈለጉባቸው ነገሮች።

1 አንድ ጊዜ

اللهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنْ زَوَالِ نِعْمَتِكَ، وَتَحَوُّلِ عَافِيَتِكَ، وَفُجَاءَةِ نِقْمَتِكَ، وَجَمِيعِ سَخَطِكَ

ትርጉም እና ምንጭ

ከዓብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዱዓ መካከል ይህ ዱዓ አንዱ ነበር: "አላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዘዋሊ ኒዕመቲክ፣ ወተሐውዉሊ ዓፊየቲክ፣ ወፉጃአቲ ኒቅመቲክ፣ ወጀሚዒ ሰኸጢክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ፀጋህ ከመወገዱ፣ ለኔ የሰጠኸኝ ደህንነት ከመቀልበስ፣ ከድንገተኛ መከራህ፣ ከአጠቃላይ ቁጣህ በአንተ እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።

ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአራት ነገሮች ተጠበቁ:

የመጀመሪያው: (አላህ ሆይ! ፀጋህ ከመወገዱ በአንተ እጠበቃለሁ!) ከሃይማኖታዊም ከአለማዊውም ፀጋህ መወገድ በአንተ እጠበቃለሁ፤ በእስልምና ላይ መፅናትንና ፀጋን የሚያስወግድ ከሆነ ወንጀል ላይ ከመውደቅም መራቅን እጠይቅሃለሁ።

ሁለተኛው: (ለኔ የሰጠኸኝ ደህንነት ከመቀልበስ) ወደ መከራ ከመለወጥ ማለት ነው። ዘውታሪ ደህንነትንና ከሁሉም በሽታዎችና ህመሞች ሰላም መሆንን እጠይቅሃለሁ።

ሶስተኛው: (ከድንገተኛ መከራህ) ከባድ አደጋ ወይም መዐት ማለት ነው። መከራና ቅጣት በድንገት የመጣ ወቅትና ለተውበትና ለመመለስ ጊዜ ከሌለ ለተፈተነበት ሰው መከራው ትልቅና አደገኛ ይሆናል።

አራተኛው: (ከአጠቃላይ ቁጣህ) ለቁጣህ የሚያስገድዱ ከሆኑ ምክንያቶች በአንተ እጠበቃለሁ፤ አንተ የተቆጣህበት ሰው በርግጥም ባዶ ቀረ ከሰረ ማለት ነው።

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጠቅላይ የሆኑ ቃላትን የተጠቀሙት የአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ቁጣ ምክንያቶች የሆኑትን ንግግሮች፣ ተግባሮችና እምነቶችን በሙሉ እንዲያጠቃልል ነው።

ጥቅሞች

  • ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደ አላህ ያላቸውን ፈላጊነት ያስረዳናል።
  • ይህቺ የተባረከች ዱዓ: ፀጋን ለማመስገን መገጠምንና ወንጀል ላይ ከመውደቅ ጥበቃን መፈለግን ሰብስባ ይዛለች። ወንጀል ላይ መውደቅ ፀጋን ታስወግዳለችና።
  • የአላህ ቁጣ ምክንያት ከሆኑ ስፍራዎች ለመራቅ መጣር እንደሚገባ እንረዳለን።
  • ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከድንገተኛ መከራ ተጠብቀዋል። ይህም አላህ ባሪያውን የቀጣው ጊዜ እራሱም መከላከል የማይችለውና ፍጡራን ባጠቃላይ ቢሰባሰቡለትም እንኳ የማይችሉት የሆነን መከራን ስለሚያሳርፍበት ነው።
  • ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ የሰጣቸው ደህንነት ከመቀልበስም ተጠብቀዋል። ይህም አላህ በደህንነቱ እርሳቸውን ከመረጣቸው የሁለቱንም አለም መልካም ተጎናፀፉ፤ የአላህ ደህንነት ከተቀለበሰ ደግሞ የሁለቱም ሀገር ጉዳት የሚደርስባቸው ስለሆነ ነው። የዚህ አለም ደህንነት ለዲንም ሆነ ለዱንያ መስተካከል ምክንያት ስለሆነ ነው።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

2 አንድ ጊዜ

اللهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْعَجْزِ وَالْكَسَلِ وَالْجُبْنِ وَالْبُخْلِ وَالْهَرَمِ وَعَذَابِ الْقَبْرِ، اللهُمَّ آتِ نَفْسِي تَقْوَاهَا، وَزَكِّهَا أَنْتَ خَيْرُ مَنْ زَكَّاهَا، أَنْتَ وَلِيُّهَا وَمَوْلَاهَا، اللهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنْ عِلْمٍ لَا يَنْفَعُ، وَمِنْ قَلْبٍ لَا يَخْشَعُ، وَمِنْ نَفْسٍ لَا تَشْبَعُ، وَمِنْ دَعْوَةٍ لَا يُسْتَجَابُ لَهَا

ትርጉም እና ምንጭ

ከዘይድ ቢን አርቀም - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «እኔ የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ይሉ ከነበሩት ውጪ አልልም። እርሳቸው እንዲህ ይሉ ነበር: "አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነልዐጅዚ ወልከሰሊ ወልጁብኒ ወልቡኽሊ ወልሀረሚ ወዐዛቢል ቀብር ፤ አልሏሁምመ አቲ ነፍሲ ተቅዋሃ ወዘክኪሃ አንተ ኸይሩ መን ዘክካሃ፤ አንተ ወሊይዩሃ ወመውላሃ፤ አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዒልሚን ላ የንፈዑ፤ ወሚን ቀልቢን ላ የኽሸዑ፤ ወሚን ነፍሲን ላ ተሽበዑ፤ ወሚን ደዕወቲን ላ ዩስተጃቡ ለሃ።" (ትርጉሙም፡ "አላህ ሆይ! እኔ ከስንፍና ፣ ከመታከት ፣ ከፈሪነት ፣ ከስስት ፣ ከመጃጀትና ከቀብር ቅጣት ባንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! ለነፍሴ ፍራቻዋን ስጣት፤ ነፍሴን ለማጥራት የተሻልከው አንተው ነህና ነፍሴን አጥራት፤ አንተ ረዳቷና ተቆጣጣሪዋ ነህና። አላህ ሆይ! እኔ ከማይጠቅም ዕውቀት፣ አንተን ከማይፈራ ልብ፣ ከማትጠግብ ነፍስ፣ ተቀባይነት ከሌላት ዱዓም ባንተ እጠበቃለሁ።")

ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ከነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዱዓ መካከል "አላህ ሆይ! እኔ በአንተ እጠበቃለሁ።" ወደ አንተ እጠጋለሁ። "ከስንፍና" የሚጠቅመኝን መዘየድ ከማልችልበት "ከመታከት" የመስራት ፍላጎትን ከማጣት፤ ሰነፍ ማለት መዘየድ የማይችል ሲሆን መታከት ማለት ደግሞ መስራት አለመፈለግ ማለት ነው። "ከፈሪነት" መስራት ለሚገባኝ ወደ ፊት ከመሄድ ከመቆጠብ፤ "ከስስታምነት" መስጠት ግዴታዬ ከሆነ ከመሰሰት "ከእርጅና" ሰውነትን የሚያደክም ከሆነ መጃጀት "ከቀብር ቅጣት" እና ለቀብር ቅጣት ከሚዳርጉ ምክንያቶች በአንተ እጠበቃለሁ። "አላህ ሆይ ለነፍሴ ፍራቻዋን ስጣት!" መልካምን ለመስራትና ወንጀልን ለመተው ግጠማት። "ነፍሴን ለማጥራት የተሻልከው አንተው ነህና ነፍሴን አጥራት" ከአንተ ውጪ ነፍሴን የሚያፀዳ አንድም የለምና ነፍሴን ከውዳቂና ርካሽ ስነምግባር አፅዳት። "አንተ ረዳቷና ተቆጣጣሪዋ ነህና።" የነፍሴን ጉዳይ የምትቆጣጠር፣ ጌታዋ፣ ባለቤቷና እርሷን የምትጣቅመው በአንተው ፀጋ ነውና። "አላህ ሆይ! እኔ ከማይጠቅም እውቀት በአንተ እጠበቃለሁ።" የኮኮብ እውቀት፣ የጥንቆላና የድግምት እውቀት አይነቱ ወይም ለመጪው አለም ከማይጠቅም እውቀት ወይም ከማይሰራበት እውቀት በአንተ እጠበቃለሁ። "አንተን ከማይፈራ ልብም በአንተ እጠበቃለሁ።" ለአንተ ከማይዋደቅ፣ ለአንተ የማይረጋ፣ አንተን በማውሳት ከማይረጋጋ ነፍስ በአንተ እጠበቃለሁ። "ከማትጠግብ ነፍስ" አላህ በሰጣትና ከለገሳት ጥሩና ሐላል ሲሳይ ከማትብቃቃ ነፍስ በአንተ እጠበቃለሁ። "ተቀባይነት ከሌላት" ተመላሽ ከሆነች "ዱዓም" በአንተ እጠበቃለሁ።"

ጥቅሞች

  • ሐዲሡ ውስጥ ከተጠቀሱት እነዚህ ነገሮች መጠበቅ ተወዳጅ እንደሆነ እንረዳለን።
  • አላህን በመፍራትና እውቀትን በማሰራጨትና በእውቀት በመስራት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • ጠቃሚ እውቀት ማለት ነፍስን የሚያጠራ የአላህን ፍራቻ ነፍስ ውስጥ የሚፈጥርና ከነፍሱ ተነስታ ወደ ሁሉም አካላቶቹ የሚሄድን የአላህ ፍራቻ የሚያስገኝ ነው።
  • የሚተናነስ ልብ ማለት የሚፈራ፣ የአላህ ስም ሲወሳ የምትርበተበት ከዚያም የምትረጋጋና የምትለዝብ ቀልብ ናት።
  • ለዱንያ መጓጓትና ከስሜቶቿና ከጥፍጥናዋ አለመጥገብ መወገዙን እንረዳለን። ስለዚህም ለዱንያ ጥቅም እጅግ የምትጓጓና የምትስገበገብ ነፍስ ለሰውየው የጠላቶች ጠላት ናት። ስለዚህም ነው የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከርሷ የተጠበቁት።
  • ሰውዬው ዱዓን ተመላሽ ከሚያደርጉና ተቀባይነትን ከሚያሳጡ ምክንያቶች ሊርቅ ይገባዋል።
  • ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥና ይህን የመሰሉ ቤት የሚመቱ ዱዓዎች ዑለሞች ለተናገሩት ማስረጃ ነው። እርሱም: ዱዓን ቤት በሚመቱ ንግግሮች ማድረግ የተወገዘው ያለ አቅሙ ቃላት ለመምረጥ ሲጥር ነው። ቃላት መረጣ መተናነስን፣ መዋደቅንና ስራን ለአላህ ማጥራትን ያስወግዳል። ከመዋደቅ፣ ፈላጊነትን ከማሳየትና በባዶ ልብ ዱዓ ከማድረግ ያዘናጋል። ነገር ግን ያለመጣጣር፣ የተሟላ አንደበተ ርቱዕ ለመሆን አይምሮን ሳያስጨንቁና የመሳሰሉትን ሳያደርጉ ወይም በሐዲሥ ውስጥ ተጠቅሶ የተሸመደደን ቤት የሚመታ ዱዓ ማለት ችግር የለውም። እንደውም የተሻለ ነው።"

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

3 አንድ ጊዜ

اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنْ مُنْكَرَاتِ الأَخْلاَقِ وَالأَعْمَالِ وَالأَهْوَاءِ

ትርጉም እና ምንጭ

ከቁጥባህ ቢን ማሊክ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ይሉ ነበር: "አላህ ሆይ! እኔ ከመጥፎ ስነ ምግባራት፣ ከመጥፎ ስራዎችና ከመጥፎ ዝንባሌዎች በአንተ እጠበቃላሁ።"»

ቲርሚዚ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ከነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና -ዱዓዎች መካከል: (አልላሁመ ኢኒ አዑዙ) አላህ ሆይ! እኔ ወደ አንተ እጠጋለሁ፣ ጥበቃህን እፈልጋለሁ። (ቢከ) ሌላውን ትቼ በአንተ ብቻ (ሚን ሙንከራቲ) አላህና መልክተኛው ከከለከሉት ፀያፍ (አልአኽላቅ) እንደ ምቀኝነት፣ ጥላቻና ኩራት ካሉ ስነ ምግባራት (ወልአዕማል) እንደመሳደብና መዝለፍ ካሉ ፀያፍ ተግባራት (ወልአህዋእ) ሸሪዓን ከሚፃረሩ ነፍስ የሚመኛቸው ከሆኑ ዝንባሌዎች (ባንተ እጠበቃለሁ) ማለት ነው።

ጥቅሞች

  • የዚህን ዱዓ ደረጃና ተወዳጅነት እንረዳለን።
  • አማኝ የሆነ ሰው ውግዝ ስነምግባራትንና መጥፎ ተግባራትን ለመራቅ ይጥራል። ዝንባሌውን ከመከተልና ስሜት ላይ ከመውደቅም ይጠነቀቃል።
  • ስነምግባር፣ ስራዎችና ዝንባሌዎች ወደ መጥፎና ጥሩ ለሁለት እንደሚከፈሉ እንረዳለን።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

ጥያቄዎች

በዚህ ገጽ ላይ ምን አለ?

የመጠበቂያ ዱዓዎች: እያንዳንዳቸው በዐረብኛ፣ ከትርጉማቸው፣ ከመጡበት ሐዲስ፣ ከደረጃቸው እና ከማብራሪያ ጋር።

ትርጉሞቹ ከየት ናቸው?

ከHadeethEnc.com፣ የተተረጎሙ የነቢዩ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ። እያንዳንዱ ሐዲስ እነሱ እንዳሳተሙት፣ ከምንጩ እና ከደረጃው ጋር እንዲሁም ወደ ዋናው የሚወስድ ማስፈንጠሪያ ይዞ ይቀርባል።

የዕለት ማስታወሻ ማግኘት እችላለሁ?

አዎ። ለAndroid የሆነው ነፃው የQabas መተግበሪያ የጠዋት እና የማታ ዚክርን በየቀኑ ያስታውስዎታል፣ ተመሳሳይ ቆጣሪም አለው።