ሱራ At-Tin التين

ትርጉም: Amharic Translation - Muhammad Sadiq

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

وَٱلتِّينِ وَٱلزَّيۡتُونِ ١

በበለስና በዘይት ወይራ እምላለሁ፡፡

وَطُورِ سِينِينَ ٢

በሲኒን ተራራም፤

وَهَٰذَا ٱلۡبَلَدِ ٱلۡأَمِينِ ٣

በዚህ በጸጥተኛው አገርም (እምላለሁ)፡፡

لَقَدۡ خَلَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ فِيٓ أَحۡسَنِ تَقۡوِيمٖ ٤

ሰውን በጣም በአማረ አቋም ላይ ፈጠርነው፡፡

ثُمَّ رَدَدۡنَٰهُ أَسۡفَلَ سَٰفِلِينَ ٥

ከዚያም (ከፊሉን) ከዝቅተኞች ሁሉ በታች አድርገን መለስነው፡፡

إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فَلَهُمۡ أَجۡرٌ غَيۡرُ مَمۡنُونٖ ٦

ግን እነዚያ ያመኑት መልካሞችንም የሠሩት ለእነርሱ ተቆራጭ ያልኾነ ምንዳ አልላቸው፡፡

فَمَا يُكَذِّبُكَ بَعۡدُ بِٱلدِّينِ ٧

ታዲያ ከዚህ በኋላ በፍርዱ ምን አስተባባይ አደረገህ?

أَلَيۡسَ ٱللَّهُ بِأَحۡكَمِ ٱلۡحَٰكِمِينَ ٨

አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ አይደለምን? (ነው)፡፡

ጥያቄዎች

ሱራ At-Tin ስንት አንቀጾች አሉት?

ሱራ At-Tin 8 አንቀጾች አሉት። በቁርኣን ውስጥ ሱራ ቁጥር 95 ነው።

ሱራ At-Tin የመካ ነው ወይስ የመዲና?

ሱራ At-Tin የመካ ሱራ ነው።

ሱራ At-Tin በየትኛው ጁዝ ውስጥ ነው?

ሱራ At-Tin በጁዝ 30 ውስጥ ነው።

ሱራ At-Tin ማዳመጥ እችላለሁ?

አዎ። በዚህ ገጽ አናት ላይ አጫውትን ይጫኑ፣ ወይም ከማንኛውም አንቀጽ ይጀምሩ። የQabas መተግበሪያም ያለ ኢንተርኔት ለማዳመጥ እንዲያወርዱት ያስችልዎታል።