ሱራ Al-'Alaq العلق

ትርጉም: Amharic Translation - Muhammad Sadiq

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ٱقۡرَأۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلَّذِي خَلَقَ ١

አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡1

خَلَقَ ٱلۡإِنسَٰنَ مِنۡ عَلَقٍ ٢

ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡

ٱقۡرَأۡ وَرَبُّكَ ٱلۡأَكۡرَمُ ٣

አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤

ٱلَّذِي عَلَّمَ بِٱلۡقَلَمِ ٤

ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡

عَلَّمَ ٱلۡإِنسَٰنَ مَا لَمۡ يَعۡلَمۡ ٥

ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡

كَلَّآ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ لَيَطۡغَىٰٓ ٦

በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡

أَن رَّءَاهُ ٱسۡتَغۡنَىٰٓ ٧

ራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡

إِنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ ٱلرُّجۡعَىٰٓ ٨

መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡

أَرَءَيۡتَ ٱلَّذِي يَنۡهَىٰ ٩

አየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡

عَبۡدًا إِذَا صَلَّىٰٓ ١٠

ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤

أَرَءَيۡتَ إِن كَانَ عَلَى ٱلۡهُدَىٰٓ ١١

አየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤

أَوۡ أَمَرَ بِٱلتَّقۡوَىٰٓ ١٢

ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤

أَرَءَيۡتَ إِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰٓ ١٣

አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤

أَلَمۡ يَعۡلَم بِأَنَّ ٱللَّهَ يَرَىٰ ١٤

አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን?

كَلَّا لَئِن لَّمۡ يَنتَهِ لَنَسۡفَعَۢا بِٱلنَّاصِيَةِ ١٥

ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡

نَاصِيَةٖ كَٰذِبَةٍ خَاطِئَةٖ ١٦

ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡

فَلۡيَدۡعُ نَادِيَهُۥ ١٧

ሸንጎውንም ይጥራ፡፡

سَنَدۡعُ ٱلزَّبَانِيَةَ ١٨

(እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡

كَلَّا لَا تُطِعۡهُ وَٱسۡجُدۡۤ وَٱقۡتَرِب۩ ١٩

ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡ 1

የግርጌ ማስታወሻ ቁጥሮች ወደ አንቀጹ ገጽ ይወስዳሉ፤ የተርጓሚው ማስታወሻዎች እዚያ ይታያሉ።

ታዋቂ አንቀጾች

ጥያቄዎች

ሱራ Al-'Alaq ስንት አንቀጾች አሉት?

ሱራ Al-'Alaq 19 አንቀጾች አሉት። በቁርኣን ውስጥ ሱራ ቁጥር 96 ነው።

ሱራ Al-'Alaq የመካ ነው ወይስ የመዲና?

ሱራ Al-'Alaq የመካ ሱራ ነው።

ሱራ Al-'Alaq በየትኛው ጁዝ ውስጥ ነው?

ሱራ Al-'Alaq በጁዝ 30 ውስጥ ነው።

ሱራ Al-'Alaq ማዳመጥ እችላለሁ?

አዎ። በዚህ ገጽ አናት ላይ አጫውትን ይጫኑ፣ ወይም ከማንኛውም አንቀጽ ይጀምሩ። የQabas መተግበሪያም ያለ ኢንተርኔት ለማዳመጥ እንዲያወርዱት ያስችልዎታል።