ከምግብ በኋላ የሚባል ዱዓ

ምግብ ሲጠናቀቅ የሚባለው የአላህ ምስጋና።

1 አንድ ጊዜ

الحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي أَطْعَمَنِي هَذَا وَرَزَقَنِيهِ مِنْ غَيْرِ حَوْلٍ مِنِّي وَلاَ قُوَّةٍ

ትርጉም እና ምንጭ

ሰህል ቢን ሙዓዝ ቢን አነስ ከአባቱ እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ምግብ በልቶ ‹አልሐምዱ ሊላሂለዚ አጥዐመኒ ሀዛ ወረዘቀኒሂ ሚን ገይሪ ሐውሊን ሚንኒ ወላቁውዋህ› ያለ ሰው ያሳለፈው ወንጀል ለርሱ ይማርለታል።"» ትርጉሙም "ያለኔ ኃይልና ብልሃት ይህንን ላበላኝና ለለገሰኝ አላህ ምስጋና የተገባው ነው።" ማለት ነው።

አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል። ደረጃ: ሐሰን ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ምግብ የበላን ሰው አላህን እንዲያመሰግንና ምግብን በማምጣቱም በመብላቱም በአላህና በእገዛው ካልሆነ በቀር ለኔ ምንም አቅም የለኝም እንዲልም አነሳሱ። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህንን የተናገረ ሰው ላሳለፈው ትናንሽ ወንጀሎቹ የአላህን ምህረት ለማግኘት የተገባ እንደሆነ አበሰሩ።

ጥቅሞች

  • የምግብ መጨረሻ ላይ አላህን ማመስገን እንደሚወደድ እንረዳለን።
  • አላህ ለባሮቹ ሲሳይን መለገሱን፣ የሲሳይን ምክንያት ለነርሱ ማግራቱንና በዚህም የወንጀላቸው መማሪያን ማድረጉን ስናይ የአላህን በባሮቹ ላይ ያለውን ትልቅ ትሩፋት መብራራቱን እንረዳለን።
  • የባሮች ጉዳይ ባጠቃላይ ከአላህ ነው እንጂ በነርሱ ኃይልና ብልሃት አይደለም። የትኛውም ባሪያ ግን ሰበቦችን በመስራት የታዘዘ ነው።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

2 አንድ ጊዜ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብሏል: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ 'አላህ ባሪያው ምግብን በልቶ እንዲያመሰግነው ወይም መጠጥን ጠጥቶ እንዲያመሰግነው ይወዳል።'"

ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

አንድ ባሪያ ጌታውን በቸረውና ባጣቀመው ፀጋዎቹ ምክንያት ማመስገኑ የአላህ ውዴታን ከሚያገኝባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ ስለሆነ ምግብ በልቶም "አልሐምዱሊላህ" ማለት ፤ የሚጠጣም ጠጥቶ "አልሐምዱሊላህ" ማለት እንደሚገባው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ገለፁ።

ጥቅሞች

  • አላህ ሲሳይን ችሮን በምስጋናችን መደሰቱ የርሱን ችሮታ እንረዳለን።
  • የአላህ ውዴታ ከመብላትና መጠጣት በኋላ ማመስገንን በመሰለ ትንሽ ምክንያት እንኳ እንደሚገኝ እንረዳለን።
  • ከምግብና መጠጥ ስነስርአቶች መካከል ከበሉና ከጠጡ በኋላ አላህን ማመስገን አንዱ ነው።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

ጥያቄዎች

በዚህ ገጽ ላይ ምን አለ?

ከምግብ በኋላ ዱዓ: እያንዳንዳቸው በዐረብኛ፣ ከትርጉማቸው፣ ከመጡበት ሐዲስ፣ ከደረጃቸው እና ከማብራሪያ ጋር።

ትርጉሞቹ ከየት ናቸው?

ከHadeethEnc.com፣ የተተረጎሙ የነቢዩ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ። እያንዳንዱ ሐዲስ እነሱ እንዳሳተሙት፣ ከምንጩ እና ከደረጃው ጋር እንዲሁም ወደ ዋናው የሚወስድ ማስፈንጠሪያ ይዞ ይቀርባል።

የዕለት ማስታወሻ ማግኘት እችላለሁ?

አዎ። ለAndroid የሆነው ነፃው የQabas መተግበሪያ የጠዋት እና የማታ ዚክርን በየቀኑ ያስታውስዎታል፣ ተመሳሳይ ቆጣሪም አለው።