አምስቱ የእስልምና ማዕዘናት

ትምህርት 5 ከ5

ሐጅ ምንድን ነው?

ከቁርኣን

إِنَّ أَوَّلَ بَيۡتٖ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِي بِبَكَّةَ مُبَارَكٗا وَهُدٗى لِّلۡعَٰلَمِينَ ﴿٩٦﴾ فِيهِ ءَايَٰتُۢ بَيِّنَٰتٞ مَّقَامُ إِبۡرَٰهِيمَۖ وَمَن دَخَلَهُۥ كَانَ ءَامِنٗاۗ وَلِلَّهِ عَلَى ٱلنَّاسِ حِجُّ ٱلۡبَيۡتِ مَنِ ٱسۡتَطَاعَ إِلَيۡهِ سَبِيلٗاۚ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ ٱلۡعَٰلَمِينَ ﴿٩٧﴾

ለሰዎች (የአላህ ማምለኪያ) መጀመሪያ የተኖረው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲኾን ያ በበካህ (በመካ) ያለው ነው፡፡ በውስጡ ግልጽ የኾኑ ተዓምራቶች የኢብራሒምም መቆሚያ አልለ፡፡ ወደ ውስጡ የገባ ሰው ጸጥተኛ ይኾናል፡፡ ለአላህ በሰዎች ላይ ወደርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው፡፡ የካደ ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡

Al-Imran 3:96-97በቁርኣን ውስጥ ያንብቡ

وَأَذِّن فِي ٱلنَّاسِ بِٱلۡحَجِّ يَأۡتُوكَ رِجَالٗا وَعَلَىٰ كُلِّ ضَامِرٖ يَأۡتِينَ مِن كُلِّ فَجٍّ عَمِيقٖ ﴿٢٧﴾

(አልነውም)፡- በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትዕዛዝ ጥራ፡፡ እግረኞች ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ ከሲታ ግመሎችም ሁሉ ላይ ሆነው ይመጡሃልና፡፡

Al-Hajj 22:27በቁርኣን ውስጥ ያንብቡ

ከሱና

ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው፡ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ ብሏል፦ "ግንኙነትና ፆታዊ ስሜትን የሚያነሳሱን ሳይፈፅምና ሳያምፅ ለአሏህ ሐጅ አድርጎ የተመለሰ ልክ እናቱ እንደወለደችው ቀን (ከወንጀል ንፁህ) ሆኖ ይመለሳል።"

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ነው። HadeethEnc.com
ማብራሪያ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ግንኙነትና ፆታዊ ስሜትን የሚያነሳሱን ያልፈፀመ - "ረፈሥ" የሚለው ቃል ፆታዊ ግንኙነትንም ይሁን መሳሳምና መተሻሸትን የመሰሉ የግንኙነት መንደርደሪያዎችን እንዲሁም ፀያፍ የቃል አጠቃቀምንም የሚያጠቃልል ቃል ነው። ወንጀልና ኃጢዓት በመፈፀም - ሳያምፅ ‐ ሐጅን ያከናወነ ያለውን ደረጃ ገለፁ። አመጽ ውስጥ ከሚካተቱት መካከል በኢሕራም ጊዜ የተከለከለን ማድረግ ይገኝበታል። በዚህ መልኩ ሐጅን ያከናወነ ሰው ልክ ህፃን ልጅ ከወንጀል የፀዳ ሆኖ እንደሚወለደው እርሱም ከወንጀሉ የተማረ ሆኖ ከሐጅ ይመለሳል።

ሁሉም ትምህርቶች