ከሱና ሩቅያ: ለህመም እና ለፈውስ ዱዓዎች

ነቢዩ ﷺ የተጠቀሙባቸው እና ያስተማሯቸው የፈውስ ቃላት።

1 አንድ ጊዜ

بِاسْمِ اللهِ (٣)
أَعُوذُ بِاللهِ وَقُدْرَتِهِ مِنْ شَرِّ مَا أَجِدُ وَأُحَاذِرُ (٧)

ትርጉም እና ምንጭ

ከዑሥማን ቢን አቢልዓስ አሥሠቀፊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እርሱ ከሰለመ ጊዜ ጀምሮ ሰውነቱ ውስጥ ስለሚሰማው ህመም ለአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አማከረ። የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለርሱ እንዲህ አሉት: «እጅህን የሚያምህ ሰውነት ላይ አድርግና ሶስት ጊዜ "ቢስሚላህ" በል። ሰባት ጊዜ ደግሞ "አዑዙ ቢላሂ ወቁድረቲሂ ሚንሸሪ ማአጂዱ ወኡሓዚሩ" በል።» አሉት።" ትርጉሙም "ከሚሰማኝ ህመምና ከምፈራው አደጋ ክፋት በአላህና በችሎታው እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።

ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ዑሥማን ቢን አቢልዓስን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሊገድለው የቀረበ የሆነ በሽታ አጋጥሞት ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሊጠይቁት መጡ። አላህ ያረፈበትን በሽታ እንዲያስወግድለት የሚያደርግ ዱዓንም አስተማሩት። ይሀውም የሚያመው ስፍራ ላይ እጁን በማድረግ ሶስት ጊዜ (ቢስሚላህ) ማለት ቀጥሎም ሰባት ጊዜ ይህንን ማለት (አዑዙ) እጠጋለሁ፣ እጠበቃለሁ (ከሚሰማኝ ክፋት በአላህና በችሎታው) አሁን ላይ ከሚያመኝ ህመም ማለት ነው። (ከምፈራው) ለወደፊት ከሚያገኘኝና ከምፈራው ሀዘንና ፍርሃት ወይም ይህ በሽታ ከመቀጠሉና ህመሙ በሰውነቴ ውስጥ ከመሰራጨቱ በአላህ እጠበቃለሁ ማለት ነው።

ጥቅሞች

  • ሐዲሡ ውስጥ እንደመጣው የሰው ልጅ ራሱ ላይ ሩቃ መቅራቱ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  • ማማረርና መቃወም በሌለበት መልኩ ህመምን ለሌሎች መንገር ከተወኩልና ትእግስት ጋር አይጋጭም።
  • ዱዓ ሰበቦችን ከመጠቀም መካከል አንዱ ነው። ስለዚህም በተነገሩን ቃላቶቹና በቁጥሮቹ ላይ ብቻ መወሰን ይገባል።
  • ይህ ዱዓ ለሁሉም የሰውነት ህመም ይሆናል።
  • ይህን ዱዓ ሩቃ በሚያደርግበት ወቅት እጅን የሚያመው ስፍራ ላይ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

2 አንድ ጊዜ

بِاسْمِ اللهِ أَرْقِيكَ، مِنْ كُلِّ شَيْءٍ يُؤْذِيكَ، مِنْ شَرِّ كُلِّ نَفْسٍ أَوْ عَيْنِ حَاسِدٍ، اللهُ يَشْفِيكَ بِاسْمِ اللهِ أَرْقِيكَ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአቡ ሰዒድ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «ጂብሪል ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ መጣና እንዲህ አላቸው: "ሙሐመድ ሆይ! አመመህ እንዴ?" እርሳቸውም "አዎ" አሉ። እርሱም: "ቢስሚላሂ አርቂክ ሚን ኩሊ ሸይኢን ዩእዚክ ሚን ሸሪ ኩሊ ነፍሲን አው ዐይኒን ሓሲዲን አላሁ የሽፊክ ቢስሚላሂ አርቂክ" (ትርጉሙም: በአላህ ስም እጠብቅሃለሁ። ከሁሉም ከሚያውክህ ነገር ፣ ከሁሉም ክፉ ነፍስ ወይም ምቀኛ አይን አላህ እንዲፈውስህ በአላህ ስም እጠብቅሃለሁ።) አላቸው።»

ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

መልአኩ ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም ወደ ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በመምጣት ጠየቃቸው: "ሙሐመድ ሆይ! በህመም ተጠቃህን?" እርሳቸውም: "አዎ" አሉ። ጂብሪልም ነቢዩን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ በማለት ጥበቃ አደረገላቸው: "ቢስሚላሂ" በአላህ ስም ታግዤ "አርቂከ" እጠብቅሃለሁ። "ሚን ኩሊ ሸይኢን ዩእዚከ" ትንሽም ሆነ ትልቅ ከሚያውክህ ነገር ሁሉ እጠብቅሃለሁ። "ሚን ሸሪ ኩሊ ነፍሲን አው ዓይኒን ሓሲድ" ከሁሉም ክፉ ነፍስ ወይም ምቀኛ አይን እንዳያገኝህ እጠብቅሃለሁ። "አሏሁ የሽፊከ" አላህ ከሁሉም በሽታ እንዲፈውስህና እንዲጠብቅህ "ቢስሚላሂ አርቂከ" በአላህ ስም እጠብቅሃለሁ። ("ቢስሚላሂ አርቂክ" የሚለውን) ሁለቴ የደጋገመውና በርሱ ጀምሮ በርሱ ያጠናቀቀው ከአላህ ውጪ ማንም እንደማይጠቅም ለመጠቆም ነው።

ጥቅሞች

  • በማማረርና በመበሳጨት መልኩ ሳይሆን ያለበትን ተጨባጭ ሁኔታ ለመግለፅ መታመምን መናገር ይፈቀዳል።
  • ሩቅያህ (በማነብነብ መታከም) በሚከተሉት መስፈርቶች ይፈቀዳል። 1 - በቁርአን ወይም አላህን በማውሳትና ሸሪዓዊ በሆኑ ዱዓዎች መሆን ይገባዋል። 2 - በዐረብኛ ቋንቋ ወይም ሌላ ቋንቋም ቢሆን ትርጉሙ በሚታወቅ መሆን አለበት። 3 - ሩቃው በራሱ ምንም እንደማይፈይድ ማመን ይገባል። ሩቃው ከመዳኛ ሰበቦች መካከል አንዱ ሰበብ ብቻ ነው። በአላህ ፈቃድ ካልሆነ በቀርም ምንም ተፅዕኖ አያሳድርም። 4 - ከሺርክ ወይም ከሐራም ወይም ከቢድዓ ወይም ወደነዚህ ከሚያደርሱ ነገሮች የራቀ መሆን አለበት።
  • የሰው ዓይን እንደሚጎዳ መረጋገጡን እንመለከታለን። የሰው ዓይን ጎጂነቱ እውነት ነው። ለሰው ዓይን ህመም በሩቃ መታከም ተገቢ ነው።
  • ሐዲሡ ላይ በተጠቀሰው የሩቃ ሕክምና መጠቀም ተወዳጅ እንደሆነ እንረዳለን።
  • ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንደማንኛውም ሰው ናቸው። ሌሎች የሚያጋጥማቸው በሽታዎች እርሳቸውንም ያጋጥማቸዋል።
  • አላህ ለነቢዩ ያለውን ጥበቃና እንክብካቤ፣ ለዚህም ጥበቃ መልአክቶቹን እንደመደበላቸው እንረዳለን።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

ጥያቄዎች

በዚህ ገጽ ላይ ምን አለ?

ከሱና ሩቅያ: እያንዳንዳቸው በዐረብኛ፣ ከትርጉማቸው፣ ከመጡበት ሐዲስ፣ ከደረጃቸው እና ከማብራሪያ ጋር።

ትርጉሞቹ ከየት ናቸው?

ከHadeethEnc.com፣ የተተረጎሙ የነቢዩ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ። እያንዳንዱ ሐዲስ እነሱ እንዳሳተሙት፣ ከምንጩ እና ከደረጃው ጋር እንዲሁም ወደ ዋናው የሚወስድ ማስፈንጠሪያ ይዞ ይቀርባል።

የዕለት ማስታወሻ ማግኘት እችላለሁ?

አዎ። ለAndroid የሆነው ነፃው የQabas መተግበሪያ የጠዋት እና የማታ ዚክርን በየቀኑ ያስታውስዎታል፣ ተመሳሳይ ቆጣሪም አለው።