أَسْأَلُ اللَّهَ الْعَظِيمَ رَبَّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ أَنْ يَشْفِيَكَ
ትርጉም እና ምንጭ
ከኢብኑ ዐባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ሞቱ ያልቀረበን በሽተኛ የጠየቀና እርሱ ዘንድ ሰባት ጊዜ "አስአሉሏሀል ዐዚም ረበል ዐርሺል ዐዚም አንየሽፊከ" ካለ አላህ ከዛ ካመመው በሽታ ያድነዋል።" ትርጉሙም "ታላቁ አላህን የታላቁን ዐርሽ ጌታ እንዲፈውስህ እጠይቃለሁ።" ማለት ነው።
አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንድም ሙስሊም የሞቱ ወቅት ያልቀረበበትን ሙስሊም በሽተኛ ሲጎበኝ: (ታላቁን አላህ እጠይቀዋለሁ።) በዛቱ፣ በባህሪያቱና በድርጊቶቹ (የታላቁን ዐርሽ ጌታ እንዲፈውስህ) እያለ ሰባት ጊዜ ዱዓ ካደረገለት አላህ ከዛ በሽታ ይፈውሰዋል በማለት ተናገሩ።
ጥቅሞች
- ለበሽተኛ ይህን ዱዓ ማለትና ሰባት ጊዜ መደጋገም እንደሚወደድ እንረዳለን።
- ይህ ዱዓ እርሱ ዘንድ የተባለበት በሽተኛ በእውነተኛና በትክክለኛ አላማ እስከተባለለት ድረስ ፈውሱ በአላህ ፈቃድ እንደሚረጋገጥለት እንረዳለን።
- ይህን ዱዓ በዝግታም ሆነ ድምፅን ከፍ አድርጎ ማለት ይፈቀዳል። ነገር ግን በሽተኛው እየሰማ ማለት ውስጡ ደስታን ስለሚከት (ስለሚፈጥር) በላጩና የተሻለው ነው።