ሱራ Al-Balad البلد

ትርጉም: Amharic Translation - Muhammad Sadiq

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

لَآ أُقۡسِمُ بِهَٰذَا ٱلۡبَلَدِ ١

በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡

وَأَنتَ حِلُّۢ بِهَٰذَا ٱلۡبَلَدِ ٢

አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡

وَوَالِدٖ وَمَا وَلَدَ ٣

በወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡

لَقَدۡ خَلَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ فِي كَبَدٍ ٤

ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡

أَيَحۡسَبُ أَن لَّن يَقۡدِرَ عَلَيۡهِ أَحَدٞ ٥

በእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን?

يَقُولُ أَهۡلَكۡتُ مَالٗا لُّبَدًا ٦

«ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ» ይላል፡፡

أَيَحۡسَبُ أَن لَّمۡ يَرَهُۥٓ أَحَدٌ ٧

አንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን?

أَلَمۡ نَجۡعَل لَّهُۥ عَيۡنَيۡنِ ٨

ለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን?

وَلِسَانٗا وَشَفَتَيۡنِ ٩

ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡

وَهَدَيۡنَٰهُ ٱلنَّجۡدَيۡنِ ١٠

ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን?

فَلَا ٱقۡتَحَمَ ٱلۡعَقَبَةَ ١١

ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا ٱلۡعَقَبَةُ ١٢

ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?

فَكُّ رَقَبَةٍ ١٣

(እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡

أَوۡ إِطۡعَٰمٞ فِي يَوۡمٖ ذِي مَسۡغَبَةٖ ١٤

ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡

يَتِيمٗا ذَا مَقۡرَبَةٍ ١٥

የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤

أَوۡ مِسۡكِينٗا ذَا مَتۡرَبَةٖ ١٦

ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡

ثُمَّ كَانَ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَتَوَاصَوۡاْ بِٱلصَّبۡرِ وَتَوَاصَوۡاْ بِٱلۡمَرۡحَمَةِ ١٧

ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች ጋር መሆን ነው፡፡

أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَيۡمَنَةِ ١٨

እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡

وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِنَا هُمۡ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَشۡـَٔمَةِ ١٩

እነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡

عَلَيۡهِمۡ نَارٞ مُّؤۡصَدَةُۢ ٢٠

በእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡

ጥያቄዎች

ሱራ Al-Balad ስንት አንቀጾች አሉት?

ሱራ Al-Balad 20 አንቀጾች አሉት። በቁርኣን ውስጥ ሱራ ቁጥር 90 ነው።

ሱራ Al-Balad የመካ ነው ወይስ የመዲና?

ሱራ Al-Balad የመካ ሱራ ነው።

ሱራ Al-Balad በየትኛው ጁዝ ውስጥ ነው?

ሱራ Al-Balad በጁዝ 30 ውስጥ ነው።

ሱራ Al-Balad ማዳመጥ እችላለሁ?

አዎ። በዚህ ገጽ አናት ላይ አጫውትን ይጫኑ፣ ወይም ከማንኛውም አንቀጽ ይጀምሩ። የQabas መተግበሪያም ያለ ኢንተርኔት ለማዳመጥ እንዲያወርዱት ያስችልዎታል።