ትምህርት 10 ከ11
አላህ ችግርና መከራን ለምን ይፈቅዳል?
አጭሩ መልስ
ይህ ሕይወት ፈተና ነው። አላህ ማን ታጋሽና ማን መልካም ሠሪ እንደሆነ ለማሳየት ሰዎችን በችግርም በምቾትም ይፈትናል። ለአማኝ ምንም ሕመም በከንቱ አይቀርም፦ የእሾህ መውጋት እንኳ ከኃጢአቶቹ ከፊሉን ያብሳል፤ አላህም ለሚታገሱና ወደ እርሱ ለሚመለሱ ታላቅ ምንዳና እዝነትን ቃል ገብቷል። ቁርኣን ደግሞ ከችግር ጋር ምቾት እንዳለ ቃል ይገባል፤ ፍጹም ፍትሕም በመጪው ሕይወት ይጠብቃል።
በቀበስ የተጻፈና ከአል-ሙኽተሰር ፊ ተፍሲር አል-ቁርኣን አል-ከሪም፣ ተፍሲር ኢብኑ ከሢር እና የHadeethEnc.com ማብራሪያዎች ጋር የተመሳከረ።
ከቁርኣን
وَلَنَبۡلُوَنَّكُم بِشَيۡءٖ مِّنَ ٱلۡخَوۡفِ وَٱلۡجُوعِ وَنَقۡصٖ مِّنَ ٱلۡأَمۡوَٰلِ وَٱلۡأَنفُسِ وَٱلثَّمَرَٰتِۗ وَبَشِّرِ ٱلصَّٰبِرِينَ ﴿١٥٥﴾ ٱلَّذِينَ إِذَآ أَصَٰبَتۡهُم مُّصِيبَةٞ قَالُوٓاْ إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّآ إِلَيۡهِ رَٰجِعُونَ ﴿١٥٦﴾ أُوْلَٰٓئِكَ عَلَيۡهِمۡ صَلَوَٰتٞ مِّن رَّبِّهِمۡ وَرَحۡمَةٞۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُهۡتَدُونَ ﴿١٥٧﴾
ከፍርሃትና ከረኃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር፡፡ እነዚያን መከራ፤ በነካቻቸው ጊዜ «እኛ ለአላህ፤ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች» ነን የሚሉትን (አብስር)፡፡ እነዚያ በእነርሱ ላይ ከጌታቸው የኾኑ ምሕረቶች ችሮታም አልሉ፡፡ እነርሱም (ወደ እውነት) ተመሪዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡
أَحَسِبَ ٱلنَّاسُ أَن يُتۡرَكُوٓاْ أَن يَقُولُوٓاْ ءَامَنَّا وَهُمۡ لَا يُفۡتَنُونَ ﴿٢﴾ وَلَقَدۡ فَتَنَّا ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۖ فَلَيَعۡلَمَنَّ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ صَدَقُواْ وَلَيَعۡلَمَنَّ ٱلۡكَٰذِبِينَ ﴿٣﴾
ሰዎቹ አምነናል በማለታቸው ብቻ እነሱ ሳይፈተኑ የሚተው መኾናቸውን ጠረጠሩን? እነዚያንም ከእነሱ በፊት የነበሩትን በእርግጥ ፈትነናል፡፡ እነዚያንም እውነት የተናገሩትን አላህ በእርግጥ ያውቃል፡፡ ውሸታሞቹንም ያውቃል፡፡
فَإِنَّ مَعَ ٱلۡعُسۡرِ يُسۡرًا ﴿٥﴾ إِنَّ مَعَ ٱلۡعُسۡرِ يُسۡرٗا ﴿٦﴾
ከችግርም ጋር ምቾት አልለ፡፡ ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡
ከሱና
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይና አቡ ሁረይራህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አንድን ሙስሊም ድካም፣ በሽታ፣ ሀሳብ፣ ሀዘን፣ ጉዳት፣ ጭንቀት የምትወጋው አንዲት እሾክ እንኳ (በከንቱ) አታገኘውም አላህ በሷ ምክንያት ከወንጀሎቹ የሚምርለት ቢሆን እንጂ።"
ማብራሪያ
ሙስሊምን ከበሽታዎች ፣ ከጭንቀቶች፣ ከሀዘኖች፣ ከችግሮች፣ ከመከራዎች፣ ከመአቶች እንዲሁም ከፍርሀትና ረሀብ ቢደርስበት አንዲት እሾህ እንኳ ብትወጋውና ብታሳምመው ለርሱ ወንጀሎቹን ማስማሪያና ኃጢአቶቹን ማስሰረያ እንደሚሆንለት የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ።