ወደ መጸዳጃ ቤት ሲገቡ እና ሲወጡ ዱዓ

ወደ መጸዳጃ ቤት ከመግባት በፊት እና ከወጡ በኋላ የሚባለው።

1 አንድ ጊዜ

اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الخُبُثِ وَالخَبَائِثِ

ትርጉም እና ምንጭ

ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መፀዳጃ ቤት የገቡ ጊዜ 'አልላሁመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ኹብሢ ወልኸባኢሥ' ይሉ ነበር።" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! እኔ ከወንድ ሰይጣንና ከሴት ሰይጣናት በአንተ እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሽንት ወይም ከሰገራ ለመፀዳዳት ወደ ስፍራው መግባት የፈለጉ ጊዜ ከወንድ ሰይጣኖችና ከሴት ሰይጣናት ክፋት በአላህ ይጠበቁና ወደርሱም ይጠጉ ነበር። በተጨማሪ "አልኹብሢ ወልኸባኢሥ" የሚለው ቃል ክፋትና ነጃሳ ተብሎም ተተርጉሟል።

ጥቅሞች

  • መፀዳጃ ቤት መግባት በሚፈለግ ጊዜ ይህን ዱዓ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  • ሁሉም ፍጡራን በሁሉም ሁኔታዎቻቸው ላይ የሚያውካቸውን ወይም የሚጎዳቸውን ለመከላከል ወደ ጌታቸው ፈላጊዎች መሆናቸውን እንረዳለን።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

2 አንድ ጊዜ

غُفْرَانَكَ

ትርጉም እና ምንጭ

የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው፦ «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከመፀዳጃ ቤት የወጡ ጊዜ "ጉፍራነክ" ይሉ ነበር።» (ትርጉሙም "ምህረትህን እለምንሃለሁ" ማለት ነው።)

አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከመፀዳጃ ቤት ተፀዳድተው ሲወጡ አላህ ሆይ ምህረትህን እጠይቃለሁ ይሉ ነበር።

ጥቅሞች

  • ከመፀዳጃ ስፍራ ሲወጣ "ጉፍራነክ" ማለት እንደሚወደድ እንረዳለን።
  • ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሁሉም ሁኔታቸው ጌታቸውን ምህረት እንደሚጠይቁ እንረዳለን።
  • ከመፀዳጃ ቤት ሲወጣ ምህረትን የሚጠየቅበት ምክንያት አላህን ለብዙ ፀጋዎቹ ከማመስገን ስላጓደልን ሲሆን ከነዛም ፀጋዎቹ መካከል የሚያውከንን ነገር እንዲወጣ ማቅለሉ አንዱ ነው። በምፀዳዳበት ወቅት አንተን ከማውሳት ስለተጠመድኩ ምህረትህን እጠይቅሃለሁ ይባላልም ብለዋል።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

ጥያቄዎች

በዚህ ገጽ ላይ ምን አለ?

የመጸዳጃ ቤት ዱዓ: እያንዳንዳቸው በዐረብኛ፣ ከትርጉማቸው፣ ከመጡበት ሐዲስ፣ ከደረጃቸው እና ከማብራሪያ ጋር።

ትርጉሞቹ ከየት ናቸው?

ከHadeethEnc.com፣ የተተረጎሙ የነቢዩ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ። እያንዳንዱ ሐዲስ እነሱ እንዳሳተሙት፣ ከምንጩ እና ከደረጃው ጋር እንዲሁም ወደ ዋናው የሚወስድ ማስፈንጠሪያ ይዞ ይቀርባል።

የዕለት ማስታወሻ ማግኘት እችላለሁ?

አዎ። ለAndroid የሆነው ነፃው የQabas መተግበሪያ የጠዋት እና የማታ ዚክርን በየቀኑ ያስታውስዎታል፣ ተመሳሳይ ቆጣሪም አለው።