ሰዎች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች

ትምህርት 5 ከ11

በእስልምና ሴቶች ምን መብቶች አሏቸው?

አጭሩ መልስ

በእስልምና ወንዶችና ሴቶች ከአንዲት ነፍስ የተገኙ ናቸው፤ በአላህ ዘንድም እኩል ናቸው፦ ያመነና መልካም የሠራ ማንኛውም ወንድ ወይም ሴት መልካም ሕይወትና ሙሉ ምንዳ ይሰጠዋል። እስልምና ለሴቶች ንብረት የማፍራት፣ ገቢ የማግኘት፣ የመውረስ፣ መህር (የጋብቻ ስጦታ) የመቀበልና ከጋብቻ በፊት ፈቃዳቸው የመጠየቅ መብት ሰጥቷል፤ ወንዶችንም ሴቶችን በደግነት እንዲይዙ ያዝዛል። ነቢዩ ሴትን ፈጽሞ መትተው አያውቁም።

በቀበስ የተጻፈና ከአል-ሙኽተሰር ፊ ተፍሲር አል-ቁርኣን አል-ከሪም፣ ተፍሲር ኢብኑ ከሢር እና የHadeethEnc.com ማብራሪያዎች ጋር የተመሳከረ።

ከቁርኣን

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱتَّقُواْ رَبَّكُمُ ٱلَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفۡسٖ وَٰحِدَةٖ وَخَلَقَ مِنۡهَا زَوۡجَهَا وَبَثَّ مِنۡهُمَا رِجَالٗا كَثِيرٗا وَنِسَآءٗۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ ٱلَّذِي تَسَآءَلُونَ بِهِۦ وَٱلۡأَرۡحَامَۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلَيۡكُمۡ رَقِيبٗا ﴿١﴾

እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአዳም) የፈጠራችሁን ከእርስዋም መቀናጆዋን (ሔዋንን) የፈጠረውን ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን (ጌታችሁን ፍሩ)፡፡ ያንንም በርሱ የምትጠያየቁበትን አላህንና ዝምድናዎችንም (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ፡፡ አላህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና፡፡

An-Nisa 4:1በቁርኣን ውስጥ ያንብቡ

مَنۡ عَمِلَ صَٰلِحٗا مِّن ذَكَرٍ أَوۡ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤۡمِنٞ فَلَنُحۡيِيَنَّهُۥ حَيَوٰةٗ طَيِّبَةٗۖ وَلَنَجۡزِيَنَّهُمۡ أَجۡرَهُم بِأَحۡسَنِ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ ﴿٩٧﴾

ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡፡

An-Nahl 16:97በቁርኣን ውስጥ ያንብቡ

إِنَّ ٱلۡمُسۡلِمِينَ وَٱلۡمُسۡلِمَٰتِ وَٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ وَٱلۡقَٰنِتِينَ وَٱلۡقَٰنِتَٰتِ وَٱلصَّٰدِقِينَ وَٱلصَّٰدِقَٰتِ وَٱلصَّٰبِرِينَ وَٱلصَّٰبِرَٰتِ وَٱلۡخَٰشِعِينَ وَٱلۡخَٰشِعَٰتِ وَٱلۡمُتَصَدِّقِينَ وَٱلۡمُتَصَدِّقَٰتِ وَٱلصَّٰٓئِمِينَ وَٱلصَّٰٓئِمَٰتِ وَٱلۡحَٰفِظِينَ فُرُوجَهُمۡ وَٱلۡحَٰفِظَٰتِ وَٱلذَّٰكِرِينَ ٱللَّهَ كَثِيرٗا وَٱلذَّٰكِرَٰتِ أَعَدَّ ٱللَّهُ لَهُم مَّغۡفِرَةٗ وَأَجۡرًا عَظِيمٗا ﴿٣٥﴾

ሙስሊሞች ወንዶችና ሙስሊሞች ሴቶች፣ ምእምናንና ምእምናትም፣ ታዛዦች ወንዶችና ታዛዦች ሴቶችም፣ እውነተኞች ወንዶችና እውነተኞች ሴቶችም፣ ታጋሾች ወንዶችና ታጋሾች ሴቶችም፣ አላህን ፈሪዎች ወንዶችና አላህን ፈሪዎች ሴቶችም፣ መጽዋቾች ወንዶችና መጽዋቾች ሴቶችም፣ ጿሚዎች ወንዶችና ጿሚዎች ሴቶችም፣ (ካልተፈቀደ ሥራ) ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች ወንዶችና ጠባቂ ሴቶችም፣ አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶችና አውሺዎች ሴቶችም፣ አላህ ለእነርሱ ምሕረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡

Al-Ahzab 33:35በቁርኣን ውስጥ ያንብቡ

لِّلرِّجَالِ نَصِيبٞ مِّمَّا تَرَكَ ٱلۡوَٰلِدَانِ وَٱلۡأَقۡرَبُونَ وَلِلنِّسَآءِ نَصِيبٞ مِّمَّا تَرَكَ ٱلۡوَٰلِدَانِ وَٱلۡأَقۡرَبُونَ مِمَّا قَلَّ مِنۡهُ أَوۡ كَثُرَۚ نَصِيبٗا مَّفۡرُوضٗا ﴿٧﴾

ለወንዶች ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ከተዉት (ንብረት) ፋንታ (ድርሻ) አላቸው፡፡ ለሴቶችም ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ከተዉት ከእርሱ ካነሰው ወይም ከበዛው ፋንታ አላቸው፡፡ የተወሰነ ድርሻ (ተደርጓል)፡፡

An-Nisa 4:7በቁርኣን ውስጥ ያንብቡ

وَءَاتُواْ ٱلنِّسَآءَ صَدُقَٰتِهِنَّ نِحۡلَةٗۚ فَإِن طِبۡنَ لَكُمۡ عَن شَيۡءٖ مِّنۡهُ نَفۡسٗا فَكُلُوهُ هَنِيٓـٔٗا مَّرِيٓـٔٗا ﴿٤﴾

ሴቶችንም መህሮቻቸውን በደስታ ስጡ፡፡ ለእናንተም ከእርሱ አንዳችን ነገር ነፍሶቻቸው ቢለግሱ መልካም ምስጉን ሲኾን ብሉት፡፡

An-Nisa 4:4በቁርኣን ውስጥ ያንብቡ

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا يَحِلُّ لَكُمۡ أَن تَرِثُواْ ٱلنِّسَآءَ كَرۡهٗاۖ وَلَا تَعۡضُلُوهُنَّ لِتَذۡهَبُواْ بِبَعۡضِ مَآ ءَاتَيۡتُمُوهُنَّ إِلَّآ أَن يَأۡتِينَ بِفَٰحِشَةٖ مُّبَيِّنَةٖۚ وَعَاشِرُوهُنَّ بِٱلۡمَعۡرُوفِۚ فَإِن كَرِهۡتُمُوهُنَّ فَعَسَىٰٓ أَن تَكۡرَهُواْ شَيۡـٔٗا وَيَجۡعَلَ ٱللَّهُ فِيهِ خَيۡرٗا كَثِيرٗا ﴿١٩﴾

እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! ሴቶችን ያስገደዳችሁ ኾናችሁ ልትወርሱና ግልጽን መጥፎ ሥራ ካልሠሩ በስተቀር ከሰጣችኋቸው ከፊሉን ልትወስዱ ልታጉላሏቸውም ለእናንተ አይፈቀድም፡፡ በመልካምም ተኗኗሩዋቸው፡፡ ብትጠሉዋቸውም (ታገሱ)፡፡ አንዳችን ነገር ብትጠሉ አላህም በእርሱ ውስጥ ብዙ ደግ ነገርን ሊያደርግ ይቻላልና፡፡

An-Nisa 4:19በቁርኣን ውስጥ ያንብቡ

ከሱና

የአማኞች እናትና የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለቤት ከሆነችው ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «ሁለት ሴት ልጆች ያሏት አንዲት ሴት ልትለምነኝ መጣች። እኔ ዘንድም ከአንድ ተምር ውጪ አላገኘችም። እርሱንም ስሰጣት ለሁለት ሴት ልጆቿ ሁለት ቦታ ከፋፍላ ሰጠች። ከዚያም ተነስታ ሄደች። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እኔ ዘንድ ሲገቡ ሁኔታውን ነገርኳቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: "ከእነዚህ ሴት ልጆች አንዳችን ሃላፊነት ወስዶ ለነርሱ መልካምን ላደረገ እነርሱ ለርሱ የእሳት ግርዶሽ ይሆኑለታል።"»

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ነው። HadeethEnc.com
ማብራሪያ

የአማኞች እናት የሆነችው ዓኢሻ (አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና) እንዲህ በማለት ተናገረች: ሁለት ሴት ልጆች ያሏት አንዲት ሴት እነርሱን ይዛ የሚበላ ነገር እንድትሰጣት ልትለምናት መጣች። ዓኢሻም ከአንድ ተምር ውጪ አላገኘችም። እርሱንም ስትሰጣት ለራሷ ምንም ሳትበላ ለሁለት ሴት ልጆቿ ሁለት ቦታ ከፋፍላ ሰጠች። ከዚያም ተነስታ ሄደች። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እርሷ ዘንድ ሲገቡ ሁኔታውን ነገረቻቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: "ከእነዚህ ሴት ልጆች አንዳችን ሃላፊነት ወስዶ ለነርሱ መልካምን ያደረገ፣ በስነስርዓት ያነፃቸው፣ ያለበሳቸውና በዚህም ላይ የታገሰ እነርሱ ለርሱ የእሳት ግርዶሽ ይሆኑለታል።"

ሁሉም ትምህርቶች