ትምህርት 1 ከ3
እንዴት ውዱእ አደርጋለሁ?
ከቁርኣን
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا قُمۡتُمۡ إِلَى ٱلصَّلَوٰةِ فَٱغۡسِلُواْ وُجُوهَكُمۡ وَأَيۡدِيَكُمۡ إِلَى ٱلۡمَرَافِقِ وَٱمۡسَحُواْ بِرُءُوسِكُمۡ وَأَرۡجُلَكُمۡ إِلَى ٱلۡكَعۡبَيۡنِۚ وَإِن كُنتُمۡ جُنُبٗا فَٱطَّهَّرُواْۚ وَإِن كُنتُم مَّرۡضَىٰٓ أَوۡ عَلَىٰ سَفَرٍ أَوۡ جَآءَ أَحَدٞ مِّنكُم مِّنَ ٱلۡغَآئِطِ أَوۡ لَٰمَسۡتُمُ ٱلنِّسَآءَ فَلَمۡ تَجِدُواْ مَآءٗ فَتَيَمَّمُواْ صَعِيدٗا طَيِّبٗا فَٱمۡسَحُواْ بِوُجُوهِكُمۡ وَأَيۡدِيكُم مِّنۡهُۚ مَا يُرِيدُ ٱللَّهُ لِيَجۡعَلَ عَلَيۡكُم مِّنۡ حَرَجٖ وَلَٰكِن يُرِيدُ لِيُطَهِّرَكُمۡ وَلِيُتِمَّ نِعۡمَتَهُۥ عَلَيۡكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ ﴿٦﴾
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወደ ሶላት በቆማችሁ (ለመቆም ባሰባችሁ) ጊዜ ፊቶቻችሁን፣ እጆቻችሁንም እስከ ክርኖች እጠቡ፡፡ ራሶቻችሁንም (በውሃ) አብሱ፡፡ እግሮቻችሁንም እስከ ቁርጭምጭሚቶች (እጠቡ)፡፡ (ሴት ጋር በመገናኘት ወይም በሌላ ምክንያት) ጀናባ ብትኾኑ (ገላችሁን) ታጠቡ፡፡ በሽተኞች ወይም በጉዞ ላይ ብትኾኑም ወይም ከእናንተ አንዳችሁ ከዓይነ ምድር ቢመጣ ወይም ሴቶችን ብትነካኩና ውሃን ባታገኙ ንጹሕን የምድር ገጽ አስቡ ፡፡ ከሱም ፊቶቻችሁንና እጆቻችሁን አብሱ፡፡ አላህ በእናንተ ላይ ምንም ችግር ሊያደርግ አይሻም፡፡ ግን ታመሰግኑ ዘንድ ሊያጠራችሁና ጸጋውን በእናንተ ላይ ሊሞላ ይሻል፡፡
ከሱና
በዑሥማን ነፃ የወጣ የሆነው ሑምራን እንዳስተላለፈው እሱ "ዑሥማንን የውዱእ እቃ እንዲያመጡላቸው ሲጣሩ አየ። (የውዱእ እቃ ሲቀርብላቸውም) ከእቃው ውሀ በእጆቻቸው ላይ አፈሰሱ። እያፈሰሱም ሶስት ጊዜ አጠቧቸው። ከዚያም ቀኝ እጃቸውን በውዱእ እቃ ውስጥ አስገብተው ውሀ ዘገኑና በዚያው ተጉመጠመጡ አፍንጫቸው ውስጥም ውሀውን አስገብተው ድጋሚ አስወጡ። ከዚያም ፊታቸውን ሶስት ጊዜ፣ ሁለት እጆቻቸውንም እስከ ክርኖቻቸው ሶስት ጊዜ አጠቡ። ከዚያም ጭንቅላታቸውን አበሱ። ከዚያም ሁለት እግሮቻቸውን ሶስት ጊዜ አጠቡ። ከዚያም እንዲህ አሉ 'ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በዚህ መልኩ ውዱእ ሲያደርጉ ተመልክቻቸዋለሁ። ከዚያም 'እኔ እንዳደረጉት አይነት ዉዱእ አድርጎ ከዚያም ነፍሱን ምንም በሃሳብ ሳያደፈርስ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው ያሳለፈው ወንጀሉ ተምሮለታል።' አሉ።'"
ማብራሪያ
ዑሥማን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ አደራረግ እጅግ በጣም የተብራራ እንዲሆን ተግባራዊ በሆነ መንገድ አስተማሩ። በውዱእ እቃ ውሀ እንዲያመጡላቸው ጠየቁ። ቀጥሎም በእጆቻቸው ላይ ሶስት ጊዜ አፈሰሱ። ከዚያም ቀኝ እጃቸውን እቃ ውስጥ ከተው ውሀ በማውጣት ውሀውን አፋቸው ውስጥ ከተው ካመላለሱ በኋላ ተፉት። ቀጥሎም ውሀውን ወደ አፍንጫቸው ውስጥ ከሳቡ በኋላ መልሰው አወጡት። ከዚያም ፊታቸውን ሶስት ጊዜ አጠቡ። ከዚያም እጃቸውን ከክርናቸው ጋር ሶስት ጊዜ አጠቡ። ከዚያም እጃቸውን አርጥበው ጭንቅላታቸው ላይ አንድ ጊዜ አበሱ። ከዚያም ሁለት እግሮቻቸውን ከቁርጭምጭሚታቸው ጋር ሶስት ጊዜ አጠቡ።
ዑሥማን (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- ዉዱአቸውን ባጠናቀቁ ጊዜ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በዚህ መልኩ ዉዱእ ሲያደርጉ እንደተመለከቱና በዚህ መልኩ ዉዱእ አድርጎ ልቡንም ጌታው ዘንድ ጥዶ በተመስጦ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው አላህ በዚህ የተሟላ ዉዱእና የጠራ ሶላት ምክንያት ያለፈውን ወንጀሉ በመማር እንደሚመነዳው እንዳበሰሯቸው ነገሯቸው።