ሱራ At-Tariq الطارق

ትርጉም: Amharic Translation - Muhammad Sadiq

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

وَٱلسَّمَآءِ وَٱلطَّارِقِ ١

በሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ፡፡

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا ٱلطَّارِقُ ٢

የሌሊት መጪውም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?

ٱلنَّجۡمُ ٱلثَّاقِبُ ٣

ጨለማን ቀዳጁ ኮከብ ነው፡፡

إِن كُلُّ نَفۡسٖ لَّمَّا عَلَيۡهَا حَافِظٞ ٤

ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡

فَلۡيَنظُرِ ٱلۡإِنسَٰنُ مِمَّ خُلِقَ ٥

ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡

خُلِقَ مِن مَّآءٖ دَافِقٖ ٦

ከተስፈንጣሪ ውሃ ተፈጠረ፡፡

يَخۡرُجُ مِنۢ بَيۡنِ ٱلصُّلۡبِ وَٱلتَّرَآئِبِ ٧

ከጀርባና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ (ውሃ)፡፡

إِنَّهُۥ عَلَىٰ رَجۡعِهِۦ لَقَادِرٞ ٨

እርሱ (አላህ) በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡

يَوۡمَ تُبۡلَى ٱلسَّرَآئِرُ ٩

ምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን፡፡

فَمَا لَهُۥ مِن قُوَّةٖ وَلَا نَاصِرٖ ١٠

ለእርሱም (ለሰው) ኀይልና ረዳት ምንም የለውም፡፡

وَٱلسَّمَآءِ ذَاتِ ٱلرَّجۡعِ ١١

የመመለስ ባለቤት በኾነችው ሰማይም እምላለሁ፡፡

وَٱلۡأَرۡضِ ذَاتِ ٱلصَّدۡعِ ١٢

(በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በኾነችው ምድርም፤

إِنَّهُۥ لَقَوۡلٞ فَصۡلٞ ١٣

እርሱ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ ቃል ነው፡፡

وَمَا هُوَ بِٱلۡهَزۡلِ ١٤

እርሱም ቀልድ አይደለም፡፡

إِنَّهُمۡ يَكِيدُونَ كَيۡدٗا ١٥

እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡

وَأَكِيدُ كَيۡدٗا ١٦

(እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡

فَمَهِّلِ ٱلۡكَٰفِرِينَ أَمۡهِلۡهُمۡ رُوَيۡدَۢا ١٧

ከሓዲዎችንም ቀን ስጣቸው፡፡ ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው፡፡

ጥያቄዎች

ሱራ At-Tariq ስንት አንቀጾች አሉት?

ሱራ At-Tariq 17 አንቀጾች አሉት። በቁርኣን ውስጥ ሱራ ቁጥር 86 ነው።

ሱራ At-Tariq የመካ ነው ወይስ የመዲና?

ሱራ At-Tariq የመካ ሱራ ነው።

ሱራ At-Tariq በየትኛው ጁዝ ውስጥ ነው?

ሱራ At-Tariq በጁዝ 30 ውስጥ ነው።

ሱራ At-Tariq ማዳመጥ እችላለሁ?

አዎ። በዚህ ገጽ አናት ላይ አጫውትን ይጫኑ፣ ወይም ከማንኛውም አንቀጽ ይጀምሩ። የQabas መተግበሪያም ያለ ኢንተርኔት ለማዳመጥ እንዲያወርዱት ያስችልዎታል።