ረመዳን 2027

የሚጠበቀው ቀን

ሰኞ 8 ፌብሩዋሪ 2027

1 ረመዳን 1448 ዓ.ሂ.

እስከ ሰኞ 8 ማርች 2027

ቀኖቹ የሳዑዲ ዓረቢያን የኡሙል ቁራ ካላንደር ይከተላሉ። ወሩ በአካባቢው የጨረቃ መታየት በሚጀምርበት ቦታ ቀኑ አንድ ቀን ሊቀድም ወይም ሊዘገይ ይችላል።

ረመዳን የሂጅሪ ካላንደር ዘጠነኛው ወር እና የግዴታ ጾም ወር ነው። ሙስሊሞች ለ29 ወይም ለ30 ቀናት በየቀኑ ከጎህ እስከ ፀሐይ መጥለቅ ይጾማሉ። ቁርኣን መውረድ የጀመረውም በዚህ ወር ነው።

ከቁርኣን እና ከሱና

ሐዲስ

عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: «مَنْ صَامَ رَمَضَانَ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ»
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "(ግዴታነቱን) አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ አስቦ የረመዳንን ወር የፆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይማርለታል።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። · ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የረመዳንን ወር በአላህ አምኖ፣ በፆም ግዴታነትና አላህ ለፆመኞች ያዘጋጀውን የደለበ ምንዳና አጅር እውነት ብሎ እንዲሁም ፆሙም ለይዩልኝና ይስሙልኝ ሳይሆን የአላህን ፊት ፈልጎበት የፆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉን እንደሚማር ነገሩን።

በHadeethEnc.com ያንብቡ

عن أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «تَسَحَّرُوا، فَإِنَّ فِي السَّحُورِ بَرَكَةً».
ከአነስ ቢን ማሊክ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ሰሑር ተመገቡ! በሰሑር ውስጥ በረከት አለ።"»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። · ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በሰሑር ጉዳይ አነሳሱ። እርሱም ለጾም ዝግጅት ሌሊቱ መጨረሻ ላይ መመገብ ነው። በሌሊቱ መጨረሻ ወቅት ለሰሑርና ለዱዓእ መቆም (በረከት) - ማለትም ብዙ ምንዳና አጅር - ያስገኛል። ለጾም ያነቃቃል፤ ክብደቱንም ያቀላል።

በHadeethEnc.com ያንብቡ

عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رضي الله عنهما قَالَ: كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَجْوَدَ النَّاسِ، وَكَانَ أَجْوَدُ مَا يَكُونُ فِي رَمَضَانَ حِينَ يَلْقَاهُ جِبْرِيلُ، وَكَانَ يَلْقَاهُ فِي كُلِّ لَيْلَةٍ مِنْ رَمَضَانَ فَيُدَارِسُهُ القُرْآنَ، فَلَرَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَجْوَدُ بِالخَيْرِ مِنَ الرِّيحِ المُرْسَلَةِ.
ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰዎች ሁሉ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ። እጅግ በጣም ቸር የሚሆኑትም ጂብሪል በሚያገኛቸው ወቅት በረመዷን ነበር። በረመዷን ውስጥም በየሁሉም ምሽት ያገኛቸውና ቁርአን ያስተምራቸው ነበር። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአውሎ ንፋስም የበለጠ በመልካም ነገር ላይ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። · ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰዎች ሁሉ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ። ለሚገባው የሚገባውን በመስጠት ቸርነታቸው የሚበዛውም በረመዷን ወር ነበር። የቸርነታቸው መጨመር ምክንያትም ሁለት ነገሮች ናቸው: የመጀመሪያው: ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም ማግኘታቸው ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ: ቁርአንን መማማራቸው ነው። ማለትም ከቀልባቸው በሽምደዳ መቅራታቸው ማለት ነው። ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም በርሳቸው ላይ የወረደውን ቁርአን ባጠቃላይ ያስተምራቸዋል። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጅግ ቸር፣ አብዝቶ ሰጪ፣ መልካም ተግባሪና አላህ በዝናብና በእዝነት ከሚልካት መልካም ንፋስ የበለጠ ለፍጡራን ፈጥኖ ደራሽ ነበሩ።

በHadeethEnc.com ያንብቡ

ይህንም ይመልከቱ

ሌሎች ዓመታት

ሌሎች በዓላት

ጥያቄዎች

ረመዳን 2027 መቼ ነው?

ረመዳን 2027 ሰኞ 8 ፌብሩዋሪ 2027 እንደሚጀምር ይጠበቃል። ይህም በኡሙል ቁራ ካላንደር 1 ረመዳን 1448 ዓ.ሂ. ነው።

የረመዳን ቀን የተረጋገጠ ነው?

አዲስ ጨረቃ እስኪታይ ድረስ አይረጋገጥም። ብዙ አገሮች የወሩን መግቢያ የሚያውጁት ከአንድ ቀን በፊት ምሽት ላይ ነው፣ ስለዚህ ቀኑ በአንድ ቀን ሊለወጥ ይችላል።

ረመዳን ስንት ቀን ነው?

ረመዳን 29 ወይም 30 ቀናት አሉት። የሸዋል ጨረቃ ሲታይ ያበቃል፣ በማግሥቱም ዒድ አል ፈጥር ነው።