የሐጅ እና የዑምራ ተልቢያ

ሐጃጁ ኢሕራም ከገባበት ጊዜ ጀምሮ የሚደጋግማቸው ቃላት።

1 አንድ ጊዜ

لَبَّيْكَ اللهُمَّ، لَبَّيْكَ، لَبَّيْكَ لَا شَرِيكَ لَكَ لَبَّيْكَ، إِنَّ الْحَمْدَ وَالنِّعْمَةَ لَكَ وَالْمُلْكَ لَا شَرِيكَ لَكَ

ትርጉም እና ምንጭ

ከዐብደላህ ቢን ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ተልቢያቸው "ለበይከ አልላሁምመ ለበይክ፣ ለበይከ ላ ሸሪከ ለከ ለበይክ፣ ኢነልሐምደ ወንኒዕመተ ለከ ወልሙልክ ላ ሸሪከ ለክ" (አላህ ሆይ! ደግሜ ደጋግሜ ለጥሪህ አቤት እላለሁ፤ ምንም ተጋሪ የለህም። ምስጋና ፀጋና ንግስና ለአንተ ብቻ ነው፤ ምንም ተጋሪ የለህም።) የሚል ነበር። ዐብደላህ ቢን ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እዚህ ላይ "ለበይከ ለበይከ ወሰዕደይክ፣ ወልኸይሩ ቢየደይክ፣ ለበይከ ወርረግባኡ ኢለይከ ወልዐመል" (ጥሪህን ተቀብያለሁ፣ ለጥሪህ ምላሽ እሰጣለሁ፣ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ነው፤ ምኞትና ተግባር ወደ አንተ ይመራል።) የሚለውን ይጨምሩ ነበር።»

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ደረጃ: ሶሒሕ ነው።

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ወደ ሐጅ ወይም ዑምራ ተግባር መግባት ሲፈልጉ ይሉት የነበረው ተልቢያ እንዲህ ብለው ነበር: (ለበይከ አልላሁመ ለበይክ) አላህ ሆይ! ወደ ጠራኸን ተውሒድ፣ ስራን ለአላህ ማጥራት፣ ለሐጅና ለሌሎችም አምልኮዎች ቁርጠኛ የሆነ መቀበልን ደጋግሜ ተቀብያለሁ። (ለበይከ ላ ሸሪከ ለከ ለበይክ) አንተ ብቻ ነህ አምልኮ የሚገባህ፣ በጌትነትህ፣ በተመላኪነትህና በስሞችህና በባህሪያቶችህም አጋር የለህም። (ኢነል ሐምደ) ምስጋናና ውዳሴ ላንተ ነው የሚገባህ። (ወንኒዕመተ) ፀጋም (ለከ) ከአንተ ነው። አንተው ነህ የምትሰጠን። በሁሉም ሁኔታዎች የምታስተናብረው አንተ ነህ። (ወልሙልኩ) ንግስናም ያንተ ነው። (ላሸሪከ ለክ) የሚጋራህ የሌለ ሁሉም ያንተ ብቻ ነው። ኢብኑ ዑመር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እዚህ ተልቢያ ላይ ይህን ይጨምሩ ነበር፡ (ለበይከ ለበይከ ወሰዕደይክ) ደጋግሜ ጥሪህን እቀበላለሁ፤ አስደስተኝ። (ወልኸይሩ ቢየደይክ) ሁሉም መልካም የሚገኘው በችሮታህ ነው። (ለበይከ ወርረግባኡ ኢለይክ) ልመናና ፍላጎታችንም የምንፈልገው መልካም ነገርም በእጅህ ወደሆንከው ወዳንተ ነው። (ወልዐመሉ) ስራም ለአንተ ነው። አምልኮ የሚገባው ለአንተ ብቻ ነው።

ጥቅሞች

  • ሐጅና ዑምራ ላይ ተልቢያ የተደነገገ መሆኑንና አፅንዖት የተሰጠው መሆኑን እንረዳለን። ተክቢራ የሶላት መገለጫ እንደሆነው ሁሉ ተልቢያም በሐጅና ዑምራ ወቅት ልዩ መገለጫው ነው።
  • ኢብኑል ሙኒር እንዲህ ብለዋል: "ተልቢያ መደንገጉ አላህ ባሮቹን ምን ያህል እንዳከበረ ያስገነዝበናል። ይህም ወደ ቤቱ ጉብኝት ማድረጋቸው በአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ጥሪ እንደሆነ ስለሚጠቁም ነው።"
  • በላጩ ተልቢያ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ያደረጉትን ተልቢያ ማለት ነው። ቢጨምርም ግን ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ያፀደቁት ስለሆነ ችግር የለውም። ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሚዛናዊው መንገድ ነው። ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የመጣውን ለብቻው ይልና ከሶሐባ የመጣን ወይም ቦታው ላይ የሚመጥን በራሱ ማለት የሚፈልገውን ለማለት የፈለገ ጊዜ ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከመጣው ጋር በማይቀላቀል መልኩ ለብቻው ይለዋል። ይህ ተልቢያ ተሸሁድ ላይ ከመጣው ዱዓ ጋር ይመሳሰላል። ነቢዩ በተሸሁድ ዱዓ ዙሪያ እንዲህ ብለዋል፡ "ከዚያም የሻውን ዱዓና ውዳሴ ይምረጥ።" ማለትም ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የመጣውን ከጨረሰ በኋላ ነው።"
  • በተልቢያ ድምፅን ከፍ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን። ይህም ለወንድ ነው። ሴት ከሆነች ግን ፈተናን ስለሚያሰጋ ድምጿን ዝግ ታደርጋለች።

በHadeethEnc.com ላይ ያንብቡ

ጥያቄዎች

በዚህ ገጽ ላይ ምን አለ?

ተልቢያ: እያንዳንዳቸው በዐረብኛ፣ ከትርጉማቸው፣ ከመጡበት ሐዲስ፣ ከደረጃቸው እና ከማብራሪያ ጋር።

ትርጉሞቹ ከየት ናቸው?

ከHadeethEnc.com፣ የተተረጎሙ የነቢዩ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ። እያንዳንዱ ሐዲስ እነሱ እንዳሳተሙት፣ ከምንጩ እና ከደረጃው ጋር እንዲሁም ወደ ዋናው የሚወስድ ማስፈንጠሪያ ይዞ ይቀርባል።

የዕለት ማስታወሻ ማግኘት እችላለሁ?

አዎ። ለAndroid የሆነው ነፃው የQabas መተግበሪያ የጠዋት እና የማታ ዚክርን በየቀኑ ያስታውስዎታል፣ ተመሳሳይ ቆጣሪም አለው።